Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙር አትቀይር! እግዚአብሔር ለዘላለም ይቅር እንዳለህ የማይሰማህ ከሆነ፣ በአንዳንድ ድካሞችህ | Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

መዝሙር አትቀይር!

እግዚአብሔር ለዘላለም ይቅር እንዳለህ የማይሰማህ ከሆነ፣ በአንዳንድ ድካሞችህ ይቅርታውን የሚሰርዝብህ መስሎ ከታየህ፣ ቀድሞውኑ በማን ይቅር እንዳለህ አልገባህም! እግዚአብሔር በራስህ ብቃት ሳይሆን በክርስቶስ ይቅር እንዳለህ አስታውስ!.

ዘማሪው ዳዊት የእግዚአብሔርን ምሕረት አስቦ "ምሕረቱ ለዘላለም ነው" ብሎ ዘመረ። አንተስ? ከገባህ እንደዚህ ዘምር!. ካልገባህ ግን ዝም በል እንጂ መዝሙር አትቀይር!

"ምሕረቱ ለቀናት ነው! ምሕረቱ ለሳምንት ነው! ምሕረቱ ለወር ነው! ምሕረቱ ለዓመት ነው! ምሕረቱ እስከማጠፋ ነው!" እያልህ የራስህን መዝሙር አትድረስ!

እንደ ቃሉ ዘምር! ቃሉ ❝እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥❞ ይላል። (ዕብ.10:12) ስለዚህ ሥራው ተሠርቶ አብቅቷል! መዝሙርህ በክርስቶስ ከተሰራው እንጂ ከሥራህ አይነሳ!

ቃሉ ❝ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውን ደግሜ አላስብም ይላል።❞ ብሏል። (ዕብ.10:17)። "ደግሜ አላስብም" ይህ ለአብ ፊደል አይደለም!  በደላችንን ልጁ ላይ ከቆጠረ በኋላ ነው፤ "ደግሜ አላስብም" ያለው። ኃጢአታችን አንድ ጊዜ ኢየሱስ ላይ ስላሰበው እኛ ላይ ደግሞ አያስበውም።

ስለዚህ መዝሙርህ እንደ ቃሉ ይሁን። ስሜትህን ሳይሆን ቃሉን ዘምር!!

ኤፍሬም ተምትም
Grace Minister @
The #Way #Reformation #Ministry

ለሌሎች አካፍሉ፦
ቀጣዩን ሊንክ ለ10 ሰዎች በመላክ አገልግሉ!

#Grace #Commission
https://t.me/gracecom
https://t.me/gracecom