2021-05-17 22:08:16
ቁረዓን ክርስቲያን አረገኝ!!!
የቀድሞ የእስላም ኢማም አስደናቂ ምስክርነት
-114 ምዕራፍ 6666 ቁጥሮች አሉት
-መሀመድ 4 ቦታ ላይ ይገኛል
-እየሱስ 25 ቦታ ላይ ይገኛል
-ቁራን ከመሀመድ በላይ ለምን እየሱስ ላይ ትኩረት አደረገ?ጥያቄ ፈጠረብኝ ይላል
ስለ እየሱስ ሱራ 3÷45-55 ላይ ሲናገር እነዚህን ጭብጦች እናገኛለን
1 Word of God የእግዚአብሔር ቃል /ካሊመቱላህ
2 Sprit of God የእግዚአብሔር መንፈስ/ሩሁላህ
3 Jesus Christ እየሱስ ክርስቶስ/ኢስ አል መሲህ
በተጨማሪ ቁርአን ስለ እየሱስ ሲናገር
-እየሱስ በሁለተኛ ቀኑ ተናግሮአል
-በጭቃ ወፍ ሰርቶአል
-አይን አብርቶአል ደዌዎችን ፈውሶአል
-የሞተ ሰው አስነስቶአል
-አልሞተም እንደገናም ተመልሶ ይመጣል
መሀመድ ግን እንኳን የሞተ ሊያስነሳ ቀርቶ እራሱም ሞቶአል፡፡ስለዚህ በሁለቱ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ
ስለዚህ አንድ ቀን Arabic College ከ10 ዓመት በላይ ወዳስተማረኝ መምህሬ ጋ ሄጄ ጥያቄ ጠየኩት
አኔ፡-"እግዚአብሔር አፅናፍ አለምን እንዴት ነው የፈጠረው?"
እሱ:-አለምን እግዚአብሔር የፈጠረው "በቃሉ" ነው
አለኝ
እኔ:-ስለዚህ ቃል ፈጣሪ ነው ማለት ነው፡፡እየሱስ ደሞ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ቁርዐን ይናገራል፡፡ብዬ መለስኩለት
እሱ:-ቃል ፈጣሪም ፍጡርም አይደለም ውጣልኝ ብሎ ገፈተረኝ፡፡
አኔም:-መልሼ ለዚህ ነዋ ቃል የእግዚአብሔር ልጅ ነው የሚሉት ክርስቲያኞች አልኩት
እሱ፡- ቃል የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ የእግዚአብሔር ሚስትን አሳየኝ ምክንያቱም ያለሚስት ልጅ የለም፡፡ አለኝ
እኔ:-ይህን ጊዜ ከቁርዐን አንድ ክፍል አሳየሁት እግዚአብሔር ያለ ዐይን ያያል ያለ ጆሮ ይሰማል ተብሎ ተጽፎአልና ያለሚስት ልጅ ሊኖረው ይችላል አልኩት ብዙም ተከራከርን፡፡
ስለዚህ ቁራን ሱራ 10÷94 ላይ በዚህ በሠጠውክ ቁራን ላይ ጥያቄ ካለህ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን አንብብ ወይም ጠይቅ ይላል
በመቀጠል መጽሐፍ ቅዱስን አነበብኩኝ ማንም ስለእየሱስ አልመሰከረልኝም እራሱ ቁራን ክርስቲያን አረገኝ፡፡
@Grace_Worship
6.0K views19:08