Get Mystery Box with random crypto!

💯

የቴሌግራም ቻናል አርማ goodnessprevails_eth — 💯 G
የቴሌግራም ቻናል አርማ goodnessprevails_eth — 💯
የሰርጥ አድራሻ: @goodnessprevails_eth
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 136
የሰርጥ መግለጫ

🙏💯👍 #Facebook_telegram_tiktok
https://t.me/Goodnessprevails_ETH
https://www.facebook.com/Goodnessprevails.ETH
https://vm.tiktok.com/ZMLv338SY/
“በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።”
— መዝሙር 4፥7

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-23 07:46:49 #የንጉሡ ልደት ዛሬ ሐምሌ 16 ቀን 1884 ዓ.ም ከራስ መኮንን ወልደሚካኤልና ከወ/ሮ የሺእመቤት ዓሊ ጋምቾ ከሐረር ከተማ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኤጀርሳ ጎሮ በተባለች ቦታ ልጅ ተፈሪ ተወለዱ፡፡

አባታቸው የአፄ ምኒልክ የአክስት ልጅ ናቸው፡፡ እናታቸው ወ/ሮ የሺእመቤት ዓሊ ከተፈሪ በፊት ስድስት ልጆች ወልደው የነበረ ቢሆንም፤ሁሉም እንደተወለዱ ሞተውባቸዋል፡፡

አሁንም ሰባተኛውን ልጅ ተፈሪን
ለመውለድ ሁለት ወራት ቀርቶኛል ብለው ሲያስሱ ድንገት በከባድ ምጥ ይያዙና ፈጣኑ ተፈሪ በተረገዙ በሰባተኛው ወር ይወለዳሉ፡፡

ልጅ ተፈሪ እንደተወለዱ ቤተዘመድ “እናቱ ካዩት እንዳተለመደው ይሞታል” በማለት ህፃኑን እናቱ ሳያዩት ይዘውት ይሄዳሉ፡፡

ይህ ክስተት በባህላዊ አገላለፅ “ሾተላይ” የሚባል ሲሆን፤ ሰው ላይ ሊኖር የሚችለው ኃይለኛ የዓይን ጨረር ሌላ ሰው ላይ ሲያርፍ እስከሞት
የሚያደርስ ጉዳት እንደሚያስከትል ይታመናል፡፡

በሳይንሳዊ ገለፃ ደግሞ የእናት ወይም የኣባት የደም አይነት RH Negative ሆኖ የሌላኛው RH Positive ይሆንና የሁለቱ ወላጆች ደም ሳይጣጣም ሲቀር የሚከሰት ችግር ተደርጎ ይገለፃል፡፡

በዚህ ምክንያት ህፃኑ ተፈሪ ከእናቱ ወዲያው መለየት ነበረበትና ከወላጆቹ ቤት ወጥቶ ዘመድ ቤት ማደግ ይጀምራል፡፡ እናቱ የህፃኑን ሁኔታ በመልዕክት ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ፤ በድጋሚ አርግዘው ነበርና ከ20 ወራት በኋላ መጋቢት 6 ቀን 1886 ዓ.ም በዚሁ በወሊድ ምክንያትህይወታቸው አለፈ፡፡

[ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ደግሞ በመጻፋቸው ከዚህ የተለየ ይጽፋሉ] ልጅ ተፈሪ የእናትን ጣዕም ሳያውቀው ቀረ፡፡ ከህፃንነቱ ጀምሮ የአጎቱ የደጃዝማች ብሩ ሓይለማርያም ባለቤት ወ/ሮ ትሰሜ አባይርጋ ከእምሩና ከልጃቸው ጋር አሳደጉት፡፡

በዚያም ሳሉ አባታቸው ራስ መኮንን የፈረንሣይኛ ትምህርት እንዲማሩ መምህር ቀጠሩላቸውና ልጅ ተፈሪ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ አደጉ፡፡

በ10 ዓመታቸው በ1894 ዓ.ም ከሐረር ወደ አዲስ አበባ መጥተው ለመጀመሪያ ጊዜ ከአፄ ምኒልክ ጋር ተገናኝተው ተዋውቀው/ ተመልሰው ወደ ሐረር ሄዱ፡፡

አባታቸው ራስ መኮንን በ1898 ዓ.ም ህዳር 10 ቀን የደጃዝማችነት ማዕረግ ሰጥተው “ጋራ ሙለታ” የተባለውን አውራጃ ሾሟቸው::

“ተከታይ ልጀ ደጃዝማች ተፈሪ ነው” ብለውም ለመኳንንቶቻቸው ይፋ አደረጉ፡፡

ልጅ ተፈሪ በ14 ዓመታቸው የደጃዝማችነት ማዕረግ እንዳገኙ ወዲያው በ1898 ዓ.ም መጋቢት 13 ቀን አባታቸው ራስ መኮንን ሞቱ፡፡

በዚህ ጊዜ አፄ ምኒልክ ተፈሪን ከሓረር ወደ አዲስ አበባ ኣስመጥተው ደጃዝማችነታቸው እንዴፀና ቀረብ የሚለውን የሰላሌን ግዛት ሾሟቸው፡፡

ተፈሪ ግን ለተሰጣቸው ግዛት ሌላ እንዴራሴ ወክለው በኢትዮጵያ ብቸኛ ትምህርት ቤት በነበረው በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት ገብተው ሐረር እያሉ የጀመሩትን ትምህርታቸውን ቀጠሉበት፡፡

ከዚያም በ1899 ዓ.ም የባሶ በጌምድር/ ግዛትን፡ ቀጥሎ በ1900 ዓ.ም ሲዳሞን ተሾሙ፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላም ሲዳሞን ትተው የኣባታቸውን ግዛት ሰፊውን ሐረርጌንና አውራጃዋን እንዲያስተዳድሩ ተደረገ፡፡

የሐረርጌ ህዝብም በደስታ ተቀበላቸው:: በ1903 ዓ.ም በሐምሌ ወር የንጉስ ሚካኤልን የልጅ ልጅ ወ/ሮ መነንን አግብተው መኖር ጀመሩ፡፡

ደጃዝማች ተፈሪ በ19 ዓመታቸው ወ/ሮ መነንን ኣግብተው በ1905
ዓ.ም የመጀመሪያ ልጃቸውን ልዕልት ተናኘወርቅን ወለዱ፡፡

ከምኒልክ ሞት በኋላ ስልጣን የያዘው እያሡ በ1907 ዓ.ም ደጃዝማች ተፈሪን ከሐረርጌ ግዛት ሽሯቸው ወደአዲስ አበባ መጥተው እንዲቀመጡ ተደረገና ወዲያው የከፋን ግዛት ሾማቸው፡፡ ሆኖም ደጃዝማች ተፈሪ አልሄዱበትም፡፡

ተፈሪ የአውሮፓ ቋንቋ የሚያውቁ፣ ከአውሮፓውያኑ ጋር ያለአስተርጓሚ በቀጥታ የሚነጋገሩ ጨዋ፣ ዝምተኛ ... እየተባሉ ቆዩ፡፡

በ1909 እያሱ ከስልጣን ተወግዶ ዘውዲቱ ሲነግሱም በወቅቱ አዲስ አበባ የነበሩት ደጃዝማች ተፈሪ ራስ በሚል ማዕረግ ኣልጋወራሽ ሆነው የራስ ወርቅ አሰሩ፡፡

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ንጉሠ ነገስት እስከሆኑበት እስከ 1923 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ ልዑል አስፋወሰንን፣ ልዕልት ዘነብወርቅን፣ ልዕልት ፀሐይን፣ ልዑል መኮንንን እና አቤቶ ሳህለስላሴን ወልደዋል፡፡

***
(ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ እንኳን ለ130ኛ የልደት በዓልዎ አደረሰን! እርስዎና ቀደምት አባቶቻችን ዓለምን ያስደነቀ ሥልጣኔና ስርዓት ገንብታችሁ የኢትዮጵያን ስም ከፍ አድርጋችሁ በዓለም አቀፍ መድረክ አስጠርታችኋል::

ካለ እርስዎና ንጉሠና ንግሥተ ነገሥታት እናትና እባቶቻችን ታሪክ ሀገራዊ ክብር የለንም!

https://t.me/Goodnessprevails_ETH
https://www.facebook.com/Goodnessprevails.ETH
https://vm.tiktok.com/ZMLv338SY/
“በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።”
— መዝሙር 4፥7
21 viewsaⷶsᷤhͪuͧ yꙷeͤ kᷜuͧlᷝnᷡiͥ, edited  04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 07:46:48
20 viewsaⷶsᷤhͪuͧ yꙷeͤ kᷜuͧlᷝnᷡiͥ, 04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 07:24:24
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 19)
----------
23፤ ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ። እውነት እላችኋለሁ፥ ለባለጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ጭንቅ ነው።

24፤ ዳግመኛም እላችኋለሁ፥ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል አለ።

https://t.me/Goodnessprevails_ETH
https://www.facebook.com/Goodnessprevails.ETH
https://vm.tiktok.com/ZMLv338SY/
“በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።”
— መዝሙር 4፥7
21 viewsaⷶsᷤhͪuͧ yꙷeͤ kᷜuͧlᷝnᷡiͥ, edited  04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 07:09:27
በአሁኑ ጊዜ በመንፈሳዊ አገልግሎት ስም ብዙ የማይገቡ ነገሮቾ እየተሰሩ ነው ይህ ደሞ በሁሉም ሐይማኖት እየታዬ ያለ ነገር ነው። እኔ ለመውቀስ አቅም የለኝም ግን መንፈሳዊ ማለት ምን ማለት ነው? እንደ እኔ መንፈሳዊ ማለት በማንኛውም ቦታ መልካም ነገርን መስራት ነው። አጠገባችን ያለውን መልካም ስራ ትተን እየሔድን መንፈሳዊነትን መመኜት ከንቱ ነው።

https://t.me/Goodnessprevails_ETH
https://www.facebook.com/Goodnessprevails.ETH
https://vm.tiktok.com/ZMLv338SY/
“በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።”
— መዝሙር 4፥7
23 viewsaⷶsᷤhͪuͧ yꙷeͤ kᷜuͧlᷝnᷡiͥ, edited  04:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 22:18:08
31 viewsaⷶsᷤhͪuͧ yꙷeͤ kᷜuͧlᷝnᷡiͥ, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 20:52:28 በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ በኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ማሸማቀቅ እና እንግልት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ተገለፀ !!!

ሐምሌ 15

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በጉራጌ ዞን በጉንችሬ ከተማ በጉንችሬ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ብሎም በተፈጠረው ችግር ምክንያት ተማሪዎች የትምህርት ዘመኑን ማጠቃለያ ፈተና አለመውሰዳቸው ተገልጿል።

መረጃውን ያደረሱን ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች እንደገለፁት በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ኦርቶዶክሳውያን መምህራኖችን እና ተማሪዎችን ማዋከብና ማንገላታት ብሎም ማስፈራራት ፣ ከክርስቲያንኖች ጋር አትቀመጡ ብሎ ማሸማቀቅ ፣ የክርስትና አማኝ ተማሪዎችና መምህራን ላይ ዛቻና ዘለፋ ማካሄድ በተማሪዎች ላይ ያለአግባብ ውጤት መቀነስ ፣ የታሪክ ትምርህት ላይ ስለክርስትና የሚያወሳውን የታሪክ ክፍል እኛ መማር አንፈልግም ስለክርስትና ማወቅ አንፈልግም የሚሉ ተማሪዎች የመማር ማስተማር ሂደቱን ማወክ ፣ የተለያዩ የእምነት መፅሐፍትን በመያዝ ክፍል ውስጥ በመሰባሰብ ድምፅ አውጥቶ በመጮህ የትምህርት ሂደቱን መረበሽ እንደሚገኙበት ገልፀዋል።

በመምህራን በኩልም አንድ የታሪክ መምህር 11ኛ ክፍል የታሪክ ትምህርት ላይ ስለ ክርስትና አይገባኝም በማለት የክርስትናን ታሪክ እና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የሀገር ባለቤትነት ያላከበረ ከሥርዓተ ትምህርቱ ተጻራሪ የሆነ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ ማድረግ ፣

ይሄ ተግባር አግባብ እንዳልሆነ ለሚመለከተው አካል በናሳውቅም ምንም አይነት ምላሽ ባለመሰጠቱ አሁን ላይ ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ቁጥራቸው 700 የሚሆኑ ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዋል ብለዋል።

እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ በዚህ ወቅት የትምህርት ማጠናቀቂያ ጊዜ ቢሆንም ውጥረቱ እየተባባሰ በመምጣቱ የክልሉ ልዩ ኃይል በከተማዋ ገብቶ ተማሪዎች የዘመኑን ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ሳይወስዱ ት/ቤቱ ሙሉ ለሙሉ መዘጋቱንም ምዕመናኑ ገልፀዋል።

ለዘመናት ተከባብረውና ተፋቅረው የኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች መካከል ደም የማቃባት እና እጅግ አሳፋሪ ድርጊት በመፈፀም በኦርቶዶክሳውያን እና በሌሎች አካላት ዘንድ አለመግባባትን እየፈጠሩ የሚገኙ አካላት ድርጊታቸው ሕገወጥ መሆኑን በመግለፅ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ከጉንችሬ ከተማ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

#Ethiopia
ኦሮቶዶክስ ሀገር ናት
https://t.me/Goodnessprevails_ETH
https://www.facebook.com/Goodnessprevails.ETH
https://vm.tiktok.com/ZMLv338SY/
“በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።”
— መዝሙር 4፥7
32 viewsaⷶsᷤhͪuͧ yꙷeͤ kᷜuͧlᷝnᷡiͥ tђє ร๏ภ ๏Ŧ tђє ๓คкєг, edited  17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 20:47:57 ጎዳና ተዳዳሪዎችን ለጉባኤ ማሟያነት ያስገባው ፓርቲ

ለኢትዮጵያ ነፃነት ፓርቲ የጉባኤ ተሳታፊዎች ቁጥር አልሞላለት ሲል የጎዳና ተዳዳሪዎችን ጉባኤው ውስጥ እንዳስገባ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እጅ ከፈንጅ ተይዟል
በዚሁ ምክኒያት ፓርቲው መታገዱን ምርጫ ቦርድ ገልፆል
ኦሮቶዶክስ ሀገር ናት
https://t.me/Goodnessprevails_ETH
https://www.facebook.com/Goodnessprevails.ETH
https://vm.tiktok.com/ZMLv338SY/
“በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።”
— መዝሙር 4፥7
28 viewsaⷶsᷤhͪuͧ yꙷeͤ kᷜuͧlᷝnᷡiͥ tђє ร๏ภ ๏Ŧ tђє ๓คкєг, 17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 20:45:21
ቤተክርስቲያኗ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ20 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15 መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ወገኖች የ20 ሚሊየን 863 ሺህ ብር ግምት ያለው የምግብ ድጋፍ አደረገች፡፡

ቤተክርስቲያኗ ከኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ነው ድጋፉን ያደረገችው ።

የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እርዳታና ልማት ማህበር ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ ፥ የልማት ድርጅቶቹ ከአሁን ቀደምም በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ድጋፉም ጤፍ፣ ባቄላ እና አልሚ ምግቦችን ያካተተ ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

በድጋፉ 20 ሺህ 842 የተፈናቀሉ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውንና መሰል ድጋፎችን በቀጣይ እንደሚያደርጉም ከከተማው ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኦሮቶዶክስ ሀገር ናት
https://t.me/Goodnessprevails_ETH
https://www.facebook.com/Goodnessprevails.ETH
https://vm.tiktok.com/ZMLv338SY/
“በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።”
— መዝሙር 4፥7
28 viewsaⷶsᷤhͪuͧ yꙷeͤ kᷜuͧlᷝnᷡiͥ tђє ร๏ภ ๏Ŧ tђє ๓คкєг, edited  17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 20:36:54
https://www.facebook.com/Goodnessprevails.ETH
25 viewsaⷶsᷤhͪuͧ yꙷeͤ kᷜuͧlᷝnᷡiͥ tђє ร๏ภ ๏Ŧ tђє ๓คкєг, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ