Get Mystery Box with random crypto!

ቤተክርስቲያኗ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ20 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገች አዲ | 💯

ቤተክርስቲያኗ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ20 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15 መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ወገኖች የ20 ሚሊየን 863 ሺህ ብር ግምት ያለው የምግብ ድጋፍ አደረገች፡፡

ቤተክርስቲያኗ ከኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ነው ድጋፉን ያደረገችው ።

የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እርዳታና ልማት ማህበር ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ ፥ የልማት ድርጅቶቹ ከአሁን ቀደምም በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ድጋፉም ጤፍ፣ ባቄላ እና አልሚ ምግቦችን ያካተተ ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

በድጋፉ 20 ሺህ 842 የተፈናቀሉ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውንና መሰል ድጋፎችን በቀጣይ እንደሚያደርጉም ከከተማው ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኦሮቶዶክስ ሀገር ናት
https://t.me/Goodnessprevails_ETH
https://www.facebook.com/Goodnessprevails.ETH
https://vm.tiktok.com/ZMLv338SY/
“በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።”
— መዝሙር 4፥7