Get Mystery Box with random crypto!

በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ በኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ማሸማቀቅ እና እንግልት እየደረሰ | 💯

በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ በኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ማሸማቀቅ እና እንግልት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ተገለፀ !!!

ሐምሌ 15

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በጉራጌ ዞን በጉንችሬ ከተማ በጉንችሬ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ብሎም በተፈጠረው ችግር ምክንያት ተማሪዎች የትምህርት ዘመኑን ማጠቃለያ ፈተና አለመውሰዳቸው ተገልጿል።

መረጃውን ያደረሱን ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች እንደገለፁት በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ኦርቶዶክሳውያን መምህራኖችን እና ተማሪዎችን ማዋከብና ማንገላታት ብሎም ማስፈራራት ፣ ከክርስቲያንኖች ጋር አትቀመጡ ብሎ ማሸማቀቅ ፣ የክርስትና አማኝ ተማሪዎችና መምህራን ላይ ዛቻና ዘለፋ ማካሄድ በተማሪዎች ላይ ያለአግባብ ውጤት መቀነስ ፣ የታሪክ ትምርህት ላይ ስለክርስትና የሚያወሳውን የታሪክ ክፍል እኛ መማር አንፈልግም ስለክርስትና ማወቅ አንፈልግም የሚሉ ተማሪዎች የመማር ማስተማር ሂደቱን ማወክ ፣ የተለያዩ የእምነት መፅሐፍትን በመያዝ ክፍል ውስጥ በመሰባሰብ ድምፅ አውጥቶ በመጮህ የትምህርት ሂደቱን መረበሽ እንደሚገኙበት ገልፀዋል።

በመምህራን በኩልም አንድ የታሪክ መምህር 11ኛ ክፍል የታሪክ ትምህርት ላይ ስለ ክርስትና አይገባኝም በማለት የክርስትናን ታሪክ እና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የሀገር ባለቤትነት ያላከበረ ከሥርዓተ ትምህርቱ ተጻራሪ የሆነ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ ማድረግ ፣

ይሄ ተግባር አግባብ እንዳልሆነ ለሚመለከተው አካል በናሳውቅም ምንም አይነት ምላሽ ባለመሰጠቱ አሁን ላይ ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ቁጥራቸው 700 የሚሆኑ ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዋል ብለዋል።

እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ በዚህ ወቅት የትምህርት ማጠናቀቂያ ጊዜ ቢሆንም ውጥረቱ እየተባባሰ በመምጣቱ የክልሉ ልዩ ኃይል በከተማዋ ገብቶ ተማሪዎች የዘመኑን ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ሳይወስዱ ት/ቤቱ ሙሉ ለሙሉ መዘጋቱንም ምዕመናኑ ገልፀዋል።

ለዘመናት ተከባብረውና ተፋቅረው የኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች መካከል ደም የማቃባት እና እጅግ አሳፋሪ ድርጊት በመፈፀም በኦርቶዶክሳውያን እና በሌሎች አካላት ዘንድ አለመግባባትን እየፈጠሩ የሚገኙ አካላት ድርጊታቸው ሕገወጥ መሆኑን በመግለፅ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ከጉንችሬ ከተማ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

#Ethiopia
ኦሮቶዶክስ ሀገር ናት
https://t.me/Goodnessprevails_ETH
https://www.facebook.com/Goodnessprevails.ETH
https://vm.tiktok.com/ZMLv338SY/
“በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።”
— መዝሙር 4፥7