Get Mystery Box with random crypto!

ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር-ቤት የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት! የደብረ ብርሃን | Amhara today

ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር-ቤት የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት!

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ የፀጥታ ስጋትን አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል።

1ኛ. በከተማ አስተዳደሩ በተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚኖር ተፈናቃይ ከምሽቱ 12:00 በኋላ ወደ መጠለያ ጣቢያውም ሆነ ወደ ከተማው መግባት ክልክል ነው።

2ኛ. በከተማው የሚገኙ የባጃጅ ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2፡00 በኋላ መንቀሳቀስ አይችልም ክልክል ነው ይህን ሲያደርግ የተገኘ ባለባጃጅ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል።

3ኛ. በከተማው የሚገኙ መጠጥ ቤቶች ምግብ ቤቶች ምሽት ጭፈራ ቤት እስከ ምሸት 2:00 ሰአት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ወስኗል።

4ኛ. በከተማው በሚገኙ የንግድ ቤቶች የምርት የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

5ኛ. ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ሀይሎች ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው

6ኛ. ከመንግስት ዕውቅና ውጭ የሚደረጉ ማናቸውም አይነት ውይይቶችና ስብሰባ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

7ኛ. የጠላትን ሀሳብና እንቅስቃሴ በመደገፍ አሉባልታና ወሬን ማሰራጨት በህብረተሰቡ ላይ ሽብር መንዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው።

8ኛ. አዳር የሚሰሩ በከተማችን ያሉ ፍብሪካዎችና ድርጂቶች ድርጁቱ በሚሰጣቸው ህጋዊ መረጃ ና በፀጥታ መዋቅሩ የተረጋገጠ የይለፍ ከያዘ ብቻ መንቀሳቀስ ይችላል፡፡

9ኛ. መላው የከተማው ማህበረሰብ በአደረጃጀት አካባቢውን ቀንና ሌሊት ከሰርጎ ገቦች በንቃት መጠበቅ አለበት።

10ኛ. በከተማ አስተዳደሩ ፀጉረ ልውጥ ሲያጋጥም በፍጥንት ለህግ አካል ጥቆማ በመስጠት በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረግ ከማህበረሰቡ ይጠበቃል።

11ኛ. የከተማው ባለሆቴሎች እና አልጋ አከራዮች ማንነቱ ያልታወቀ የታጠቀ ግለሰብ በድርጅታችሁ ሲያጋጥማችሁ ለህግ አካላት ጥቆማ እንድትሰጡ።

12ኛ. በከተማ አስተዳደሩ ያላችሁ የቤት አከራይዎች የምታከራዩትን ግለሰብ ማንነትት መታወቂያ በመጠየቅ ለይታችሁ እንድታከራዩ የተከራዩንም መረጃ በፎርም በመሙላት ለከተማው ሰላምና ፀጥታ መምሪያ እንድታሳውቁ መልዕክት አስተላልፏል።

ይህ የውሳኔ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ከላይ በዝርዝር የተቀመጡትን የውሳኔ ሀሳቦች የሚጥስ ማንኛውም አካል ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድበትም የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር

የቪዲዮ መረጃ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe ያድርጉ!