Get Mystery Box with random crypto!

ገዳይ ተሸላሚ ገዳዪም ሸላሚ የቸገረ ነገር ሟች ሁኖ ታዳሚ ከእጃቸው አምልጦ ማን ይሆን ከራሚ በመ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ገዳይ ተሸላሚ ገዳዪም ሸላሚ
የቸገረ ነገር ሟች ሁኖ ታዳሚ
ከእጃቸው አምልጦ ማን ይሆን ከራሚ

በመደመር ሒሳብ ሰው እየቀነሱ
መሸላለም ሆነ ውጤቱ ለነሱ

የዛቱበት ምላስ ሳይደርቅ ምራቁ
ኮሜዲ መሰለን ተቃቅፈው ሲስቁ

ይገረማችሁ ብለው
የጃቸው ደም ሳይደርቅ ለሽልማት በቁ

የገደለ ሁሉ ሚሸለም ከሆነ
ህዝብ ሙቶ አለቀ ሀገር አፈር ሆነ

ገላችሁ ገላችሁ መሸለም ስትመጡ
ሽልማቱን ሚያደምቅ ታዳሚ እንዳታጡ


ርዕስ አውጡለት

mk