የኖረ ያልኖረ ዓለት እየታዬ ፥ድንጋይ የበዛበት ፤ ተራራ እየታዬ ፥ዠንጀሮ ያለበት ፤ ማን እንቅልፍ ይተኛል፥ቆርበት ቢያነጥፉለት፣ ዝናብ ያረጠበው ፥ ያልደረቀ ኩታ ፣ ማን ለብሶትስ ያድራል ፥ ቢገኝስ በማታ ፣ ሜዳ ሙሉ ሳር ፥ የገመተው መናኝ ማን በሌት ይጓዛል ፥ገደሉን ሰው ቢቃኝ ማን አምኖ ይሄዳል፥ በመኖር ለሚቃኝ ለማን ነግሮ ሄደስ ፥ እግዜር ላለ በቃኝ ገድሉን ማን ይፃፍ? ሸፍቶስ ለሞተው ፣ እውነትስ እንዳለው ፥እውነት እንደሌለው ፣ ማነውስ የሚያውቀው ፥ማነውስ ሚፈርደው ? ለዛ ነው እኮ..? መኖርን ምፈራው...? በእነዛ ቀለማት፥ የእኔ ነፍስ ታጅሎ ያወራውን ፊደል ባለማድረግ ውሎ ብደክም አይገርመኝ ስወጣ ከክፍሉ ፣ አይደለም እኔው ፥የሚማር በዕድሉ ፣ አስተማሪው ሁሉ፥ ረቡኒው ሁሉ፣ ኑሮ አላሳዬኝም ፥ ተገኝቶ ከቃሉ ፣ ለዛ ነው ምፈራው ፥የሰውን ልጅ ቃሉ፣ ____ ግዕዝ ሙላት ( @geez_mulat ) 532 viewsጥ ቁር ዝምታ, 08:09