Get Mystery Box with random crypto!

/////ማስታወስን መርሳት///// ከሁሉም ከሁሉም እሱን በማምለኬ እኔን የሚቆጨኝ የሰናፍጭ ቅንጣት | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

/////ማስታወስን መርሳት/////
ከሁሉም ከሁሉም
እሱን በማምለኬ እኔን የሚቆጨኝ
የሰናፍጭ ቅንጣት
ታህል እምነት ሰጥቶኝ ተራራ እሚያጋጨኝ
ቃሌን ሳለሰልስ የሚያነጫንጨኝ
አለ የሆነ አምላክ!
በሴቶች ልብ ላይ ጀምሮ እማይቋጨኝ።
.......
ጀመረ ልማዱን!
ካቻምና ካንዷ ጋር በፍቅር ዘረረኝ
እሷን እሷን እያልኩ
እሱን ስለረሳሁ አጣልቶ መከረኝ
ስጣላት ደጁ ሄድኩ
አልቅሼ ልማፀን ''አታሳጣኝ'' ብዬ
ባይሰማኝም ሰማኝ ደረሰው እንባዬ
''አንድ አለችኝ''ምላት
ልቤ ላይ ከሰመ አስረሳኝ አንድዬ።
.......
ጀመረ ላይቋጨኝ!
አምናም ከአንዷ ጋር በፍቅር ተሰዋሁ
''እሷን እሷን''እያልኩ የሱን መኖር ረሳሁ
ስረሳው ትዝ አልኩት እንባዬ ናፈቀው
ልቤን ከልቧ ላይ በደማቁ ፋቀው
ስፋቅ ደጁ ሔድኩኝ
እንደለመደብኝ እሱን አስታውሼ
እሷን ረሳኋት
ወጣች ከልቤ ላይ ሸኘኋት አልቅሼ።
.......
ጀመረኝ ላይቆጨኝ!
ዘንድሮም አፈቀርኩ ላንዷ ሰጠሁ ነፍሴን
እሷን እሷን እያልኩ..
አምላኬን ረሳሁት ዘነጋሁ ራሴን።
ስረሳው ትዝ አልኩት ለእንባ ደጁ ጠራኝ
መቼም የማይረሱት...
አንድ ነገር አለ ሲል አንድዬ መራኝ።
እላለሁ እሷ ናት መቼም የማልረሳት
እኩል እረስቻት እኩል ማስታውሳት።
......
እላለሁ እሷ ናት!
በሰፈሯ እንዳላልፍ
የመረጥኩት መንገድ ደጇ የሚወስደኝ
እረስቻት ስኖር...
ረስቻት የማላውቅ ልቤ እያስገደደኝ።
እሷን ለመርሳት ስል
ከብዙ ከሴቶች ጋር ልላመድ ብለፋም
እላለሁ ለራሴ...
ነፍስ ላይ ያተሙት ልብ ላይ አይጠፋም።
አዎ ነፍሴ ላይ ነች!
ስትሔድ ነው የሞትኩት ስጋዬ በስብሷል
ህያውነቴ ላይ ትዝታዋ ነግሷል።
እላለሁ ለራሴ....
ሰው ገነትን ቢወርስ ፃድቅ ቢሆን ነፍሱ
ካምላኩ ጋር ቆሞ...
ብቻውን ከሆነ ሲኦል ነው ለራሱ።
አዎ ሲኦል ላይ ነኝ ገነትን ወርሼ
ራሴን በራሴ ...
ሳቃጥል የምኖር እሷን አስታውሼ።
እላለሁ ለራሴ....
እሷ ራሷ ማናት...
ሁሉን ምታስረሳኝ ነፍሴ ላይ ታትማ?
ከረሳሁት ጋራ...
ረስቻታለሁ ትዝ አትለኝማ!
የለም
የለም
የለም
ረስቻት እንኳን አልችልም ልረሳት
አለ አይደል አንዳንዴ...
ገነትን ሲወርሱ ሚናፍቁት እሳት
እሷ ማለት ያ ናት!
እሱ ግን ማን ነበር....
በሴት ልጅ ልብ ላይ ጀምሮ ማይቋጨው
እረስቸዋሁ መርሳቴ እስኪቆጨው።

በላይ በቀለ ወያ
https://t.me/poem_by_poem