Get Mystery Box with random crypto!

በፍላጎት መንገድ... በምኞት ጎዳና ፣ ስመጣ ተጉዤ ገንዘብ እየፈለግሁ... 'ፍቅር ይበልጣል' የሚ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

በፍላጎት መንገድ...
በምኞት ጎዳና ፣ ስመጣ ተጉዤ
ገንዘብ እየፈለግሁ...
"ፍቅር ይበልጣል" የሚል ፣ ከንቱ ሙግት ይዤ
እኔም ልክ እንዳንቺ...
ከገንዘብ ወዳጅ ጋር ፣ ተከራክሪያለሁ
ገንዘብ የማይገዛው...
ብዙ ደስታ አለ ፣ ስል አስረድቻለሁ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ግን ደሞ ግን ደሞ...
በማስረዳቴ ውስጥ ፣ አለ የሚያስረዳኝ
ከፍቅር ከገንዘብ...
ከምንም የሚበልጥ ፣ "እውነት " ይሉት አዳኝ፡፡
፡፡፡፡፡፡
እናም እውነት ማለት...
በጭራሽ አይደለም!
አንድድ እውነት ለማቆም ፣ አንዱን እውነት መጣል
አትጠራጠሪ!!!
አንዱ ገንዘብ ሲመርጥ ፣ አንዱ ፍቅር ይመርጣል
አልጠራጠርም!!!
ወይ ልብ ይወስናል ፣ ወይ አንጀት ይቆርጣል!
"ሒድ"ወዳልሽኝ ልሒድ!!!
በማይሆን ክርክር ፣ ማን እውነቱን ያጣል?!
ሒጅ ወደ ፈለግሽው!!!
ከፍቅር ከገንዘብ ፣ ፍላጎት ይበልጣል፡፡
።።።።
(በላይ በቀለ ወያ) https://t.me/poem_by_poem