Get Mystery Box with random crypto!

       የህልም ሩጫ ልተኛ ስል አይኔን ጨፍኜ እንዲወስደኝ እሱን አምኜ ትንሽ ሳልቆይ ሌላ ቦታ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

       የህልም ሩጫ

ልተኛ ስል አይኔን ጨፍኜ
እንዲወስደኝ እሱን አምኜ
ትንሽ ሳልቆይ ሌላ ቦታ
ስሮጥ ስባክን በማታ
እዛ ቦታ ምን ሰደደኝ
እንቅልፍ አደል የወሰደኝ
ስጋየ ያለ ከአልጋየ ወድቆ
ነብሴ ሚዳ ሲዋቃ ታጥቆ
ድቅድቅ ጨለማ የለ ገላጋይ
እንዳላመልጥ ገደል ድንጋይ
ወይኔ ዛሬ ማን ባነቃኝ ......
........
ከሴጣን ጋር ፍጥጫ
እዛው ድክድክ የህልም ሩጫ
ወደኋላየ እየሮጥኩኝ
እንኳን ልነቃ ደከምሁኝ
እንደ ምንም አጓጉሬ
ብንን ስል ላብ ዳክሬ
በስመአብ ብየ አማትቤ
ብርድ አለ ሚዘለው ልቤ
ነብሴ ፈርታ ተጨንቃ
እያሰበች አርቃ
የህልሙን ፍች ገምታ
ስትንቀጠቀጥ ፈርታ
ጎኔ አልጋውን ወይ አለቀቀ
አፈር ስጋ ዙሮ ወደቀ።

mk