Get Mystery Box with random crypto!

ቃል… (ሰለሞን ሳህለ) -------------- ከጎጆው አጠገብ በረንዳው ላይ ቆሞ ስለሷ እያሰበ ደ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ቃል…
(ሰለሞን ሳህለ)
--------------
ከጎጆው አጠገብ በረንዳው ላይ ቆሞ
ስለሷ እያሰበ ደጋግሞ ደጋግሞ
የጻፈውን ግጥም እያነበበችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው
‘’ቃልሽ ቀን ነበረው…
ቃልሽ ቅን ነበረው…
ቃልሽ ቀን ገደለው…’’
የሚለውን መግብያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ
ቃሏንና ቀኗን አንድ ላይ አስባ
መአልትና ሌቱን አንድ ላይ ሰብስባ
የገደለችውን ቀን ልክ እንዳወቀችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው
‘’ህይወት ውጣ ውረድ የትሙ ብዙ ነው
ቀን የገደልሽውም አውቀሽ ሳታውቂ ነው
በፀሀይቱና በጨረቃ መሀል
በሰዓታት እጣ በቀን ማታ ክፍል
ከአንደኛው ትንፋሼ ቀጣዩ ሲቀጥል
ስጠብቅሽ ነበር ከእስትንፋሴ እኩል
እዛው ነሽ አውቃለሁ እዚህ ነሽ መጥተሻል
ልቤ ገራገር ነው እስከዚህ ያምንሻል!’’
የሚለውን መዝጊያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ
ፎቶ ደብዳቤውን አንድላይ ሰብስባ
ፍቅር የሰጣትን በፍቅር አስባ
ልበ ገራገሩን…
ልቡን እንዳደማች ልክ እንዳወቀችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው !!

Solomon Sahele