Get Mystery Box with random crypto!

-ማር____ትሬዛ እና እኔ --- _---------_ አድሮ ለማያስብ ገዝፎ ላስጠላሺኚ፣ ለአምሳሉ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

-ማር____ትሬዛ እና እኔ ---
_---------_

አድሮ ለማያስብ ገዝፎ ላስጠላሺኚ፣
ለአምሳሉ ሲባል በአባትሽ ፊት ነበር
በማር  የገዛሺኚ...፣
ትሬዛሺን ትተሺ  ለአንገትሽ አሰርሺኚ፣
(ይሁን አልኩ ...አመንሺኚ)

በእኔ ብቻ  ስምሽ!
በበአል ሲስሙሽ፣
ላታወሪ ነገር ቡና ጠጥተው አሙሽ፣

ባሪያ ለሚንቀው
የክረምት ወር መቃ ሙቶ ለሚሳሳሽ፣
ይሄ ዓለም እኮ
በሸለምሺው ፈረስ
አንቺኑን ነበር ለመጫን የረሳሽ፣

ሳስብ መርሳትሽን፣
ሳለቅሰው ለቅሶሽን
ስሆነው ትክሽን፣
ስንቴ ተገተርኩ
አማጥኩ መምጣትሺን፣
ለበደልሽው ልቤ ጠብቄ ይቅርታሽን፣

እንጃ ግን...ምህረትሽን...

____

# ግዕዝ ሙላት


@geez_mulat