Get Mystery Box with random crypto!

ልረሳሽ እየጣርሁ ነው (በእውቀቱ ስዩም) በጣራው ላይ ሲረማመድ፥ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ መጋረጃው ሲውለ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ልረሳሽ እየጣርሁ ነው
(በእውቀቱ ስዩም)
በጣራው ላይ ሲረማመድ፥ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ
መጋረጃው ሲውለበለብ፥ ሰንደቅ ሆኖ ለመስኮቴ
ዋርካው በቅጠል ጽዋ
ውሀ ሲያቁር ከሕዋ
የምድርን ጉሮሮ ሊያርስ
መሬት ፍጥረትን ስትፀንስ
በዚህ ሁሉ ጸጋ መሀል፥ ያንቺን መሄድ ስተምነው
ኢምንት ነው፥ ምንም ነው
ልረሳሽ እየጣርሁ ነው::
መጣ፥ መጣ ፥ መጣ ፥ የዝናቡ ኮቴ አየለ
ክረምት የፍጥረት መሲሕ፥ በቀጠሮው ከተፍ አለ
ስሱ የጉም አይነርግብ፥ ውብ ገጽሽን ሸፋፈነው
የርጥብ አፈር ፥ ርጥብ ሽታ፥ ውብ ሽቶሽን አዳፈነው
ልረሳሽ እጣርሁ ነው ::
የዝናቡ ኮቴ ይደምቃል
እንደ ብስል ሾላ ፍሬ ፥ አሮጌው ሰማይ ይወድቃል
አዲስ ሰማይ ይነቃል፥
እንኳንስ የግርሽ ኮቴ ፥ ጎዳናሽም ታጥቦ ያልቃል
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው ።
(የማለዳ ድባብ)