ጀግና አንጀቷን ቢወጋ በሆድ ኑሮ ባንዳ ፣ አብሮ ከጠላት የእናት ቤት ሲከዳ ፣ ተነሳ ተቆጣ!፦ ልክ ግብሩን ሊያሳይ ነቅቶ በማለዳ ፤ ነጆ ያበቀለው እትብተ ወለጋ ፣ ምሎ ለኪዳኗ ጎህ ሲገፍ ሲውጋጋ ፣ ተነሳ ማለዳ ጠላቷን ፍለጋ ፤ በማለዳው ነቅቶ ፣ የጠላቱን ዱካ ካለበት አሽትቶ ፣ ኦኔ እያነሳሳ በአጀብ በቀረርቶ ፤ ድል እያደረገ ቢያዝም በጠላት ፣ እኛን ምሰል ቢሉት ቢሰጡት ዜግነት ፣ መሞት የመረጠ ክዶ ለባርነት ፤ እሱ... የማይደራደር ከቶ ባገር ጉዳይ ፣ እትዮጵያን ከፍ አርጎ በሮም አደባባይ ፣ ከፎቅ ያመለጠ በእራፊ ትልታይ ፤ ጀግናው አብዲሳ አጋ !። ከሻምበል ዋቅጋሪ ከ ጅማ 20/08/201 1.9K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 21:38