Get Mystery Box with random crypto!

ጀግና አንጀቷን ቢወጋ በሆድ ኑሮ ባን'ዳ ፣ አብሮ ከጠላት የእናት ቤት ሲከዳ ፣ ተነሳ ተቆጣ!፦ ል | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ጀግና
አንጀቷን ቢወጋ በሆድ ኑሮ ባን'ዳ ፣
አብሮ ከጠላት የእናት ቤት ሲከዳ ፣
ተነሳ ተቆጣ!፦
ልክ ግብሩን ሊያሳይ ነቅቶ በማለዳ ፤

ነጆ ያበቀለው እትብተ ወለጋ ፣
ምሎ ለኪዳኗ ጎህ ሲገፍ ሲውጋጋ ፣
ተነሳ ማለዳ ጠላቷን ፍለጋ ፤

በማለዳው ነቅቶ ፣
የጠላቱን ዱካ ካለበት አሽትቶ ፣
ኦኔ እያ'ነሳሳ በአጀብ በቀረርቶ ፤

ድል እያደረገ ቢያ'ዝም በጠላት ፣
እኛን ምሰል ቢሉት ቢሰጡት ዜግነት ፣
መሞት የመረጠ ክዶ ለባርነት ፤

እሱ...
የማይደራደር ከቶ ባገር ጉዳይ ፣
እትዮጵያን ከፍ አርጎ በሮም አደባባይ ፣
ከፎቅ ያመለጠ በእራፊ ትልታይ ፤

ጀግናው
አብዲሳ አጋ !።

ከሻምበል ዋቅጋሪ
ከ ጅማ
20/08/201