የባከነ ሌሊት!!!! (በእውቀቱ ስዩም) ወይ ሮንድ አላደርኩ ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ ወይ ሰአታት ቁሜ ቤተክስያን ስሜ ሰይጣን አላሳፈርሁ:: ሌቦች ደብድበውት አንዱን ምስኪን ላሥር ባምቢስ ድልድዩ ሥር ቆስሎ የወደቀ ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ ፊቱ ተሸፍኖ : በደምና አቧራ "በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ ምስኪን አባወራ ብብት ሥር ገብቼ አፋፍሼ አንስቼ ተሸክሜ አድኜ ስፈልግ አምቡላንስ :ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ ወይ ምግባር አልሠራሁ ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ : ወይ ፅድቅ አላፈራሁ:: አንድ በትረ-ሙሴ ሁለት ስስ አሎሎ ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ ሲባክን ዝምብሎ " እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ" የምትል መለሎ ልቤን ሳትሰውረው አልጋየን ሳትሰብረው:: ወግ ቢጤ ሞንጭሬ: ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ " እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ:: አንዲት ሴት- አዳሪ :ቺቺንያ ምንገድ ላይ እድሉዋ ሰባራ :ሰውነቱዋ አማላይ ካፍያውና እንባዋ : ተጋግዞ ሚያረጥባት ደምበኛ ስትጠበቅ :ደመኛ ጥሎባት አምስት ደፋሪዎች : ከበው ሲያዋክቧት ሲገፉ ሲስቧት " እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን ልመናዋ ስቦኝ እንዳበጀ በለው : በደሏ አንገብግቦኝ ከሁዋላ ደርሼ ነበልባል ለብሼ: ነበልባል ጎርሼ እንደብሩስሊ: እንዳየሩ ጋኔን እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን በማረግ ቃኝቼ ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ:: ድል ሳላስመዘግብ ውጥረት ሳለረግብ ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ ያለምንም ጣጣ : ያለምንም ፀጋ አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ:: 2.5K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 19:52