Get Mystery Box with random crypto!

አስታወሰኝ አስታውሰኝ ስረሳ... ፍጡር ሰው አይደለሁ፣ ተዘንግቶህ እንጂ... ፊቱን እረሳለሁ፣ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

አስታወሰኝ

አስታውሰኝ ስረሳ...
ፍጡር ሰው አይደለሁ፣
ተዘንግቶህ እንጂ...
ፊቱን እረሳለሁ፣

አዎ እኔ ረሺ ነኝ
ባለፈብኝ ሀሉ፣
በተረማመደኝ
መሬት ብሆን ቅሉ፣

ክፉ በሆነብኝ
ክፋት ላላወሳ፣
ምህላ ና ፀሎቴ
ጥፋትን ልረሳ፣

በሱባዬው ምህፅን
ብዋዋል ከእግዜሩ፣
የመርሳት ግንብ አጥር
ተከፍቶልኝ በሩ ፣

በዚያ በኩል ሳልፍ
ክፉ አልተከተለኝ፣
መጥፎን አስረሳና
ደጉን አስታወሰኝ።
27/09/2014
@*** 18