Get Mystery Box with random crypto!

ገጸ ሰብእ

የቴሌግራም ቻናል አርማ getseseb — ገጸ ሰብእ
የቴሌግራም ቻናል አርማ getseseb — ገጸ ሰብእ
የሰርጥ አድራሻ: @getseseb
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 718
የሰርጥ መግለጫ

አንድ ሰው
https://t.me/getseseb

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 21:09:11
"ዕርቅን የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤ እነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።
ማቴ ፭፥፲
https://t.me/getseseb
68 views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 18:19:12
"እኔ ግን እላችኋለሁጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁን መርቁ፤ ለሚጠሏችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚበድሉአችሁና ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ። በሰማያት ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ፤ እርሱ ለክፉዎችና ለደጎች ፀሐይን ያወጣልና፤ ለጻድቃንና ለኃጥአንም ዝናምን ያዘንማልና።"
ማቴ ፭፥፵፬-፵፭
https://t.me/getseseb
169 views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 07:04:40 "ኅጠተ ሥርናይ ለእመ ኢተዘርዓት ኢትመወት ወእመሂ ኢሞተት ኢትፈሪ ወከማሁ ቂም ለእመ ኢሞተት እምህሊናሁ ለመስተበቅል ኢትመውት ኃጢአቱ እንተ ገብራ።

የስንዴ ቅንጣት ካልተዘራች አትሞትም ካልሞተችም አታፈራም እንዲሁ ቂም ከበቀለኛ ህሊና ካልሞተች የሠራት ኃጢአት አትሞትም።"

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
መጽሐፈ ምሥጢር


https://t.me/getseseb
1.9K views04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 11:41:30 "የእግዚአብሔር ቃላት የነፍስን ሙቀት ያድሳሉ። እንድታድግ ከፈለግህ የእግዚአብሔርን ቃላት እንደሕፃን ልጅ መጥባት አለብህ።"
ቅዱስ አትናቴዎስ

https://t.me/getseseb
1.7K views08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 10:33:04
"እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤"
ማቴ ፳፩፥፳፩
https://t.me/getseseb
2.0K views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 20:21:12 ቅዱሳን ኹሉ ከእግዚአብሔር የተሰጡን ልዩ ሎተሪዎቻችን ናቸው። በዓለም እንዳለው ያሉ ሎተሪዎች ግን አይደሉም። ኹሉም ዋጋ አላቸው፤ ኹሉም ደራሽ ናቸው። ዋጋቸውም መጠኑ መጠን የለውም። ቅዱሳን ሎተሪዎችን ለመግዛት ገንዘብ አይጠይቅም። ስማቸውን መጥራት በቂ ነው። ዘጸውዓ ስምክሙ ይላልና።
እንግዲህ ሀብታም መኾን ከፈለግን ያለወጪ ሀብታም የምንሆንበት ድንቅ ምሥጢር ይኽ ነው። የቅዱሳንን ስም ጠርተን ችግር የተባሉ ችግሮቻችንን ኹሉ እናስወግድ። ለዘላቂው ኑሮ ዘላቂ ሀብት ከትሩፋታቸው፣ ከረድኤታቸው እንሰበስባለንና።
ማንኛውም ችግር አለብኝ ካልክ ይኽን ሎተሪ በአንደበትህ ኹልጊዜ ቁረጥ፤ ኹልጊዜም ይደርስኻል።

ዲ/ን ሳሙኤል በላቸው
ሠኔ ፳፬ ፳፻፲፬ ዓም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
"ወአንቢበክሙ አንትሙ ለዘኢያንበበ አይድኡ እናንተ አንብባችሁ ላላነበበው ንገሩ"
https://t.me/getseseb
395 views17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 06:04:32 "መ" ሲሉት ይደርሳል የሚለውን ምስክርነት ከምወዳት እናቴ ስሰማው ልቤ ካልወደድኹት ብሎ ሞገተኝ። እውነትም የሚወደድ ድንቅ ሰማዕት ነው። አንዳንዴ እንኳን "መ" ሲሉት አይደለም "መ" ሊሉት ሲያስቡ ከተፍ እንደሚል አስባለሁ። የሰማዕታት ወጉ ነው ልበል? ለሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስም ከተሰጠው ቃል ኪዳን አንዱ ሦስት ጊዜ "አምላከ ጊዮርጊስ ርድአኒ" የሚል ሰው ወዲያው እንደሚደርስለት ነው። የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስም ዝኒ ከማሁ ነው። ሳይብስስ ይቀራል ብላችሁ ነው? የስሙን የመጀመሪያ ፊደል ገና ሲሉት "ወይ" የሚል ግሩም ሰማዕት።
የሰማዕታት እልቅና የተሰጠኽ ጽኑ ተጋዳይ ቅዱስ መርቆሬዎስ አባታችን ስምህ ከማር ከወተት ይልቅ ይጣፍጣልና "መ" ብቻ ብለን አናቆምም።
"መርቆሬዎስ መርቆሬዎስ መርቆሬዎስ" እንላለን እንጂ።

ተወዳጆች ብዙ ሊመለሱልን የሚያስፈልጉ ጥያቄዎች ቢኖሩንም ጥያቄዎቹን ግን አናውቃቸውም። እንፈልጋለን ግን ምን እንደኾነ አልገባንም። እንደክማለን ግን የድካማችን ምክንያትና ዋጋው ምንና ምን ያህል እንደኾነ አናስተውልም። ታዲያ ለዚህ ታላቅ መናወጥ ጸጥታውን የሚሰጥ አያስፈልገንም? ታዲያ ለምን የእግዚአብሔር ታማኝ፣ ፈጥኖ ደራሹ መርቆሬዎስን ጠርተን አናዋየውም?
"መ" ብለን እንጥራው፤ "መርቆሬዎስ" ብለንም ልባችንን በሐሴት እንሙላው። እንደነፋስ በፈረሱ ገሥግሦ ግሳንግሳችንን ያስወግድልናል። ከእኛ የሚጠበቀው ማመን፣ መጥራትና መንገር ነው። የምንነገረው ከጠፋን እንኳ የምንነግረው እንደጠፋን እንንገረው። ሰማዕቱ ዘዴኛ ነው፤ የተሰወረብንን ገልጦ፣ ከዓይናችን ላይ ይደረድረዋል። ያኔ አንደበታችን ሳይሆን ዓይናችን በእንባ መናገር ይጀምራል። ተወዳጁ መርቆሬዎስም ከእግዚአብሔር በተሰጠው ሥልጣን ጓዳ ጎድጓዳችንን ሞልቶ፣ እንባችንን አብሶ፣ ያጣነውን ክሶ ያሳርፈናል።
ታድያ ምን እንጠብቃለን? እንጥራዋ!! ልብ ያለው ልብ ያድርግ።

ዲ/ን ሳሙኤል በላቸው
ሠኔ ፳፭ ፳፻፲፬ ዓም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
"ወአንቢበክሙ አንትሙ ለዘኢያንበበ አይድኡ እናንተ አንብባችሁ ላላነበበው ንገሩ"
https://t.me/getseseb
593 views03:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 19:56:03 ማንነታችንን በኃጢአት ጎርፍ ለመስበርና ለማፈራረስ ደፋ ቀና የምትለዋን ዓለም የምናሸንፋት ቅዱሳን አባቶቻችንን እና ቅዱሳት እናቶቻችንን አውቀን፤ ከእነርሱ ሕይወት ተምረን፤ በተግባር ስንኖር ነው። ምክንያቱም የአባቶቻችን እና የእናቶቻችን ማንነት በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ የተገነባ የማይሰበር ዐለት ነውና።
ዲ/ን ሳሙኤል በላቸው
https://t.me/getseseb
2.3K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 10:03:43
"ዛሬ የሚያዝኑ ብፁዐን ናቸው፤ መጽናናትን ያገኛሉና።"
ማቴ ፭፥፬
https://t.me/getseseb
2.3K views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 08:41:35 "በውኑ ከናዝሬት ደግ ሰው ሊወጣ ይቻላልን?" ዮሐ ፩፥፵፯

ይኽንን ቃል የተናገረው እንደ ዮሐንስ ወንጌል አዘጋገብ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በመከተል አራተኛው ሰው የኾነው ናትናኤል ነው። ነገሩ እንዲኽ ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ ሲያልፍ መጥምቁ ዮሐንስ "እነሆ የዓለም ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ" ዮሐ፩፥፴፮ ብሎ ለደቀ መዛሙርቱ ለእንድርያስና ጴጥሮስ ለተባለው ስምዖን እርሱን እንዲከተሉ ይነግራቸዋል። አስቀድሞ "የእግሩን ጫማ ጠፍር መፍታት የማይቻለኝ"ዮሐ፩፥፳፯ ብሎ በተከበረበት ሀገር "ክርስቶስ ይበልጠኛል" ብሎ ተናገረ።ይኽንን ባለ በነጋታው ደግሞ ለዓመታት ሲያገለግሉት ለነበሩት ደቀ መዛሙርቱ "ሂዱ ከእኔ ይበልጣልና ተከተሉት" ብሎ በፍጹም ልቡ አምኖ አዘዛቸው።

ዮሐንስ ሆይ በዘመናችን ሥልጣን አለን የምንል ሰዎች አንተን ባየን፣ ቃልኽን በሰማን ጊዜ ኃፍረታችን ብዙ ነው። የበረሃው ኮከብ ሆይ በዘመናችን በታዋቂነታችን የምንመካ ሰዎችን ስራኽን በተመለከትን ጊዜ ወዮልን ወዮታ አለብን። ልክን ማወቅ በልክ መኖርን አልቻልንምና፤ የማይገባንን ስንሻ፣ ታላላቆቻችንን ስንንቅ እየኖርን ነውና።
ከእንድርያስና ከጴጥሮስ ቀጥሎ ጌታችን ፊልጶስን አግኝቶ "ተከተለኝ" አለው። በዚኽ ጊዜ ፊልጳስ "ባልንጀራኽን እንደራስኽ ውደድ"ማቴ፲፱፥፲፱ የሚለውን ቃል በተግባር ሲኖረው ተመለከትን። ፊልጶስ ጌታችንን ብቻውን ሊከተለው አልወደደም። የመሲሑን መምጣት ወዳጁ ናትናኤል እንዲጠብቅ ያውቃልና "ሙሴ በኦሪት ነቢያትም ስለእርሱ የጻፉለትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስ አገኘነው"ዮሐ፩፥፵፯ ብሎ ነገረው።
ይኽ መሲሕ እስራኤላውያን ካሉበት መካራ እንዲያወጣቸው እጅግ የሚጠብቁት ነው። አንዳንዶቹ የመሲሑ ንግሥና በዚኽ ዓለም እንደኾነ አስበው ቀኝ ጌታና ግራ ጌታ መኾንን ሲሹ አማላጅ ሲልኩም ተመልከተናል። ፊልጶስ መልካም ወዳጅ ባይኾን ወደዚኽ መሲሕ ናትናኤልን እንዲመጣ ባልጋበዘው ነበር። ዛሬ ብዙዎች ጥቂት ነገር ሲያገኙ አልያም ደግሞ ጓደኞቻቸው ጥሩ ነገር ሲገጥማቸው ከመደሰት ይልቅ የሰይጣን ባሪያ በመኾን በጓደኞቻቸው ላይ የክፋት ስራን ሲሰሩ ማየት የተለመደ ኾኖአል። ፊልጶስ ግን እኔ ያየኹትን መልካም ነገር ወዳጄም ይየው ብሎ ወደ ናትናኤል ሮጠ።
ፊልጶስ ሆይ መልካም ዜና ለመንገር ፍቅረ ቢጽን ለመተግበር የተፋጠነች እግርኽ የተባረከች ናት።

ነገር ግን ፊልጶስ እንደጠበቀው አላገኘም። ናትናኤል "እግዚአብሔር ይመስገን መሲሑ የት ነው? ውሰደኝ እባክኽ ጓደኛዬ "አይደለም ያለው። "በውኑ ከናዝሬት ደግ ሰው ሊወጣ ይቻላልን?" አለ እንጂ። ብዙዎቻችን በተለያየ መንገድ የምንጠይቃት ናትናኤላዊ ጥያቄ ናት። አንደ ሰው መልካም የሚባል ደረጃ እንደደረሰ በሰማን ጊዜ "የእንትን ሰፈር የነበረው አይደል እንዴ?" "እንትን ትሰራ የነበረችው አይደለች?" "እንዴት እንዴት እዚኽ ደረሰች" መሰል ጥያቄዎችን እናዘንበዋለን። ናዝሬት በወንበዴዎች የምትታወቅ ቦታ ነበረች በጊዜው። ስለዚኽ በአብዛኛው ሰው የናዝሬት ልጆች ወንበዴዎች ስለመኾናቸው ነው የሚገምቱት። ፊልጶስ ግን "መጥተኽ እይ" አለው። እንዴት የሚደንቅ ነገር ነው! ሰዎች ስራኽን ሰምተው ባይቀበሉኽ፣ መለወጥኽን ሰምተው ባያምኑ ጉዳዩ ያንተ አለመስራትና አለመለወጥ ሳይኾን የእነርሱ አለመቀበልና አለማመን ብቻ ነው። ስለዚኽ መጥተው ይዩኽ። አንድም ለሰዎች ስለእግዚአብሔር ፍቅር ስትነግራቸው፣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለተትረፈረፈው ሰላምና ጸጋ ስትመሰክር አንዳንዶች በማፌዝ አንዳንዶች በሚሰሙትና ያላግባብ ሲያገለግሉ ባዩአቸው አገልጋዮች ላያምኑኽና ላይቀበሉኽ ይችላሉ። ቁም ነገሩ መምጣታቸው እግዚአብሔርን እንዲያዩ እንጂ ሰዎችን እንዲያዩ አለመኾኑን ገና ስትጠራቸው ልትነግራቸው ይገባል። መጥታችኹ እግዚአብሔርን እዩ ልትላቸው ይገባል። ወዳጄ ናትናኤል ጌታችንን መጥቶ ሲያየው ምን ያለ ይመስልኻል? ወንበዴው? ደካማው? በፍጹም ይልቁንስ እንዲኽ አለው "መምህር ሆይ በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነኽ፤ የእስራኤልም ንጉሥ አንተ ነኽ"። ስለዚኽ በእውነት ከናዝሬት መልካም ነገር ይወጣልና ናዝሬት በተባለች ከኃጢአት መንደር ነጽተን እንውጣ። በእውነት ከናዝሬት መልካም ነገር ይወጣልና ከናዝሬት የወጡ ሰዎችን ከቦታቸው አንጻር ሳይኾን ከስራቸው አንጻር በማየት ልንቀበላቸው ይገባል።
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ዲ/ን ሳሙኤል በላቸው

"ወአንቢበክሙ አንትሙ ለዘኢያንበበ አይድኡ እናንተ አንብባችሁ ላላነበበው ንገሩ"
https://t.me/getseseb
3.6K views05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ