Get Mystery Box with random crypto!

ሐምዱ<=>ቋንጤ

የቴሌግራም ቻናል አርማ hamdquante — ሐምዱ<=>ቋንጤ
የቴሌግራም ቻናል አርማ hamdquante — ሐምዱ<=>ቋንጤ
የሰርጥ አድራሻ: @hamdquante
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.39K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው።
✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼
👇🏾👇🏾👇🏾
@hamdquante
አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል
👉🏿 @hamdquante_bot👈🏿

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 12:30:29
አላህ ለባሪያ መልካም ሲሻለት
የሰራውን መልካም ስራ
በልቡ እንዳያስበውና
በምላሱ እንዳይናገረው በማድረግ

የሰራውን ወንጀል በማሰብ ላይ እንዲጠመድ ያደርገዋል።


የሰራውን ወንጀል እያሰበ ከመፀፀት አይወገድም ጀነት እስከ ሚያስገባው ድረስ

አንድ መልካም ስራ አላህ የተቀበለው እንደ ሆነ ባሪያው ያንን ስራ "ሰርቻለሁ" እያለ በልቡ እንዳያስበውና በምላሱ እንዳይናገረው ይደረጋል


https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB
1.1K views09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:59:49
ያዝልኝማ..!

የመሆን እንጂ የመባል ገመድ ላይ አትንጠልጠል። የመባሉ ያንተ እውነተኛ ገመድ ስላልሆነ መበጠሱ አይቀርም። የመሆኑ ገመድ ግን የግልህ ስለሆነ  ከቆሸሸ ማጠብ፣ ካለቀ መቀየር፣ ያንተ ድርሻ ነው¡¡¡


https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB
1.6K viewsedited  18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:43:19
የተሰቀለ አያድንም፤
የሚያድን አይሰቀልም



የተሰቀለ አያድንም
ምክንያቱም፦
ራሱን ሊያጠቃ የመጣ ጠላት መክቶ ማሸነፍ ያቃተውና በጠላት ተሸንፎ የተሰቀለ፣ የተገረፈ፣ የተሰቃየና የተገደለ በፍፁም ዓለምን ሊያድን አይችልም።
በጠላቶቹ ሲሰቀል ራሱን ማዳን ያልቻለ እንዴት ሆኖ ዓለምን ሊያድን ይችላል



የሚያድን አይሰቀለም
ምክንያቱም፦
አዳኝ ሆኖ ዓለምን በአጠቃላይ የሚጠብቅ ጠላቶቹ አይደለም ሊሰቅሉትና ሊጎዱት ሊቀርቡትም አይችሉም። ዓለምን የሚያድነው እሱ ከሆነ በግልባጩ ዓለምን ማጥፋትም ይችላል ማለት ነው። ጠላቶቹም ቢሆኑ በዓለም ውስጥ ያሉ ናቸውና ከፈለገ እሱ ሊጎዳቸው እንጂ እነሱ እሱን ሊጎዱት አይችሉም። ስለ ሆነም የሚያድን አ ይ ሰ ቀ ል ም

https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB
1.9K views11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 22:14:13
ሰላም ለሀገራችን

https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB
438 viewsedited  19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:00:11
ቋሚ ተሰላፊው ጅህልና


ሁሌም ወንጀልና ሙሲባ (በላ) ባለበት ቦታ ቋሚ ተሰላፊ በመሆን የሚያገለግል መሳሪያ ቢኖር ጅህልና ነው።

የትኛውም ዓይነት ወንጀል ሲሰራ ለዝያ ወንጀል መገኘት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ጅህልና አይቀሬ ምክንያት ነው።

የትኛውም ዓይነት ሙሲባ ሲከሰት ለዝያ ሙሲባ መከሰት ምክንያት ተደርገው ከሚጠቀሱ ነገሮች ጅህልና አይቀሬ የሆነ ምክንያት ነው።

ለምሳሌ……
ከወንጀሎች ብናይ፦
ስለ ክህደት ከተወራ…
ጅህልና አንዱ ምክንያት ነው።
ስለ ቢድዓ ከተወራ…
ጅህልና አንዱ ምክንያት ነው።
ስለ ዝሙት ከተወራ…
ጅህልና አንዱ ምክንያት ነው።
ስለ ምቀኝነት ከተወራ…
ጅህልና አንዱ ምክንያት ነው።


ከሙሲባ ብናይ፦
ስለ ፊርቃ ከተወራ…
ጅህልና አንዱ ምክንያት ነው።
ስለ ጠላት መሰለጥ ከተወራ…
ጅህልና አንዱ ምክንያት ነው።
ስለ ጀሀነም መግባት ከተወራ…
ጅህልና አንዱ ምክንያት ነው።

ለእነዚህ ሁሉ ችግሮች በዋነኝነት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች አንዱ ይህ ጅህልና (አለማወቅ) ከሆነ ይህንን በሽታ ከራስ ለማስወገድ መጣር (መማር) የእያንዳንዱ ሙስሊም ግዴታ ይሆናል።

ጅህልና የሚባለው ነገር በ2 መልኩ ልናየው እንችላለን።
1ኛው, አለ ማወቅ ወይም አለ መማር ሲሆን፤
2ኛው, ባወቁት አለ መስራት ይሆናል። ምክንያቱም "ዕውወት" ማለት የተሸመደደው ሳይሆን የጠቀመው ነው።

https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB
1.0K views15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:22:26 ከፊሎች…
መልካምነትህ አይተው ይወዱሃል።

ከፊሎቹ ደግሞ…
መልካምነትህ አይተው ይበሉሃል።


https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB
1.6K views14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:58:00
"አንድ ሰው ኢማኑ ከፍ ባለ ልክ
ወደ የፈተና አዳራሽ እየገባ ነው።"
[አቡ ዐብዱል መናን ኻሊድ]


አላህ ከሁሉም ፊትና እንዲጠብቀን እንለምነዋለን። ከመሆኑም ጋ ወደ አላህ በተቃረብክ ልክ ፊትናዎች ተጠናክረውና ተበራክተው እንደ ሚጠብቁህ እወቅ።

ኢማንህ ከጠነከረ ፈተናዎች ቢጠነክሩም ታልፋቸዋለህ።
ምክንያቱም
አላህ ከአንተ ጋ ነው

ስለ ሚወድህ ይፈትንሃል፤
ፈተናውን ስታልፍ…
የበለጠ ከፍ ያደርግሃል

https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB
2.1K views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 15:19:35 ለእኛ ብሎ ቢሰቀል ራሱ
ሊመለክ አይገባውም



የዒሳ (የእየሱስ) አምላኪ ነን ብለው
“እየሱስ ያድናል፣ እየሱስ ጌታ ነው” እያሉ የሚሰብኩ ፔንጤዎችና ይህንኑ አመለካከት የሚያምኑ ኦርቶዶክሶች ለዚህ ባጢል ለሆነው እምነታቸው መረጃ አድርገው ከሚያቀርቧቸው ነጥቦች አንዱ…
“እየሱስ እኛን ለማዳን ሲል ተሰቅሏል” የሚል ነው።

ይህ አባባል በሎጂካልም ይሁን በእምነታዊ መነፅር ቢታይ በብዙ ዓይነት መልኮች ሙሉ ለሙሉ ውድቅ የሚሆን ሲሆን እኔም በዚህ ዳሰሳዬ ውድቅ ከሚሆንባቸው መንገዶች አንዱን ለማየት ወደድኩኝ።


«ለእኛ ብሎ ቢሰቀል ራሱ ሊመለክ አይገባውም።»
እንዴት

“ለእኛ ሲል ተሰቀለ” የሚለው ዓረፍተ ነገር ሲተረጎም፦
እኛ (የሰው ልጆች) አመፃችን በዝቶ የሆነ አካል (አምላካችን) አስቆጣነው። አምላካችንም እኛን በወንጀላችን ብዛት ሊያጠፋን ተቃረበ። በዚህ ጊዜ የሆነ አካል (ዒሳ (እየሱስ)) መጣና እኛ እንማር ዘንዳ እሱ ተሰቀለና በእሱ መሰቀል (መቁሰል) እኛ ተፈወስን (ተማርን)። ስለዚህ “እኛን ያዳነን እየሱስ ነውና እናመልከዋለን”
ማለት ነው።
ይህ ነው እምነታቸው።


አሁን ተከታተሉኝ…
1ኛ,በወንጀላችን ምክንያት የተቆጣ አካል (አምላክ) አለ ማለት ያንን አምላክ ዋነኛው (የሐቅ) አምላካችን እሱ ነው።

2ኛ,አምላካችን በወንጀላችን ብዛት ተቆጥቶ እኛን ከጥፋት ለመታደግ ራሱን ሰውቶ የተሰቀለ አካል ቢኖር ራሱ ያ አካል እኛን ከአምላካችን ቁጣ ሊታደገን አማላጅ የሆነ አካል እንጂ እሱ ራሱ አምላካችን ሊሆን አይችልም።

3ኛ,እኛን ለማዳን አማላጅ ሆኖ የተሰቀለ አካል አለ ማለት፦
3.1, እሱ አምላካችን እንዲምረን አማላጅ የሆነ አካል እንጂ እሱ ራሱ የሚምር (የሚያድን) አካል አይደለም።
3.2, ይህ ተሰቀለ የተባለው አካል እውነተኛው (ሐቁ) አምላካችን እንዲምረን የሚለምንና የሚማፀን እንጂ እሱ ራሱ መማርም ይሁን ማዳን የማይችል አካል እንደ ሆነ ያሳየናል።

በራሳቸው አንደበት……
“አምላካችን እንዳይቀጣን እየሱስ ለእኛ ሲል ተሰቀለ” እያሉ
በሌላኛው ምላሳቸው
“እየሱስ ጌታ ነው፣ እየሱስ ያድናል” እያሉ ይሰብካሉ።

ወገን!
አንድ ሽንቱን የመቆጣጠር ያህል እንኳ አእምሮው ጤነኛ የሆነ ሰው……
እየሱስ ጌታ ከሆነ፣ እየሱስ የሚያድን ከሆነ
ለምን ተሰቀለ ሳይሰቀል ለምን አላዳነንም ብሎ አይጠይቅም

እውነታው ግን……
ዒሳ (እየሱስ)
አልተሰቀለም አልተገደለም።
ማዳንም መማርም አይችልም።


የአላህ ትእዛዝና ክልከላ ወደ ባሮች እንዲያስተላልፍ አላህ በትልቅ ተኣምር ላይ አድርጎ የላከው ባሪያውና መልእክተኛው ነው። ጠላቶቹ ጥቃት ሊፈፅሙበት ባሴሩ ጊዜ አላህ ወደ ሰማይ ከፍ አደረገው
ይህንን እውነታ የተቃረነ የትኛውም እምነት ውድቅ (ባጢል) ነው።


ሐምዱ ቋንጤ
ከፉርቃን ሰማይ ስር
https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB
2.3K views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 15:15:37
1.9K views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 06:18:20 አንድ አላህ የወሰነው ነገር “ባይሆን ኖሮ” ከምል…
ፍም የሆነ እሳት እስኪበርድ ድረስ ነክሼ መቆየቱ የበለጠ እወዳለሁ።
[ኢብኑ መስዑድ]


https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB
2.2K views03:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ