Get Mystery Box with random crypto!

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tezekern — ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ
የቴሌግራም ቻናል አርማ tezekern — ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ
የሰርጥ አድራሻ: @tezekern
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.71K
የሰርጥ መግለጫ

አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነት ነው እንጅ እንደ በደላችን አይሁን ።

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-25 12:11:44
✥✥✥መዝ ፳:፩-፭✥✥✥
✥✥✥✥✥✥✥

✟በመከራ ቀን እግዚአብሔር #ይስማህ፤ የያዕቆብ አምላክ ስም #ያቁምህ።

✟ከመቅደሱ ረድኤትን #ይላክልህ፥ ከጽዮንም #ያጥናህ።

✟ቍርባንህን ሁሉ #ያስብልህ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህን #ያለምልምልህ።

✟እንደ ልብህ #ይስጥህ፤ ፈቃድህንም ሁሉ #ይፈጽምልህ።

✟በማዳንህ ደስ ይለናል፤ በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንላለን፤ ልመናህን ሁሉ እግዚአብሔር #ይፈጽምልህ።
ዲ/ን ምንቴ
703 views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 17:19:31
#መንፈሳዊ #ምክር

1 እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ሀውልት ሆነህ እንዳትቀር የተውከውን ሀጢአት ዞረህ አትመልከት ዘፍ19:26

2 ለደሀ ከመመፅወት አትቦዝን እንደ ነዌ ትፀፀታለህና ሉቃ13:4

3 በአባትህ ላይ በንቀት አትሳቅ እንደ ካም ትረገማለህና 1ኛ ነገ13:22

4 የሀሰት ቃል ከአንደበትህ አይውጣ እንደ ሃናንያና ሰጲራ ትሞታለህና ሀዋ 5:3

5 የቤተክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳት ለራስህ አትጠቀም እንደ ብልጣሶር ትመዘናለህና 2ኛ ሳሙ 6:6

#ምክሩንፈፃሚ ያድርገን #አሜን
ዲ/ን ምንቴ
811 views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 10:06:17
922 views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 20:22:44 ​​እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ፍቺ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ! በየትም ዓለም የምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሰላምታችን ይድረሳችሁ፡፡

#የእመቤታችን_ትንሣኤና_ዕርገት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሳ አራት ዓመት ነው፡፡ እነዚህ ዓመታት ሲተነተኑ ሦስት ዓመት በወላጆቿ ሐናና ኢያቄም ቤት፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፣ ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አሥራ አምስት ዓመት ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነው፡፡

ያረፈችውም ጥር 21 ቀን በ50 ዓ.ም ነው፡፡ ባረፈችበት ወቅት ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ሥጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሔዱ አይሁድ "ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፤ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ተመልሶም ይህን ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ በማስተማር ሕዝባችንን ወስደውብናል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች እያሉ በማስተማር ሊያውኩን አይደለምን? ኑ! ተሰብስበን በእሳት እናቃጥላት" ብለው ክፉ ምክር ተማከሩ፡፡

ከመካከላቸውም ብርቱ ሰው የሆነው #ታውፋንያ የተባለ ቅድስት ሥጋዋን ከሐዋርያት ነጥቆ ለማስቀረት ክቡር ሥጋዋ ያለበትን የአልጋ ሸንኮር ሲይዝ በመልአከ እግዚአብሔር እጁ ተቆርጣ ከአልጋው ላይ ተንጠልጥላ ቀረች፤ ከዚህ የጥፋቱ ሥራው ተምሮ እመቤታችንን በመለመኑ እመቤታችን የተቆረጠች እጁን መልሳለታለች፡፡

ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የተቀደሰ ሥጋዋን ጌታችን ይወደው የነበረ ተብሎ የተነገረለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሆነውን ሁሉ ለወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፡፡ እነሱም የእመቤታችን ሥጋ በክብር ለማሳረፍ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ፡፡

ከሁለተኛ ሱባኤ ቆይታቸው በኋላ በአሥራ አራተኛ ቀናቸው ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ ሰጣቸው፡፡ ሐዋርያትም በዝማሬና በታላቅ ምስጋና በጌቴ ሴማኔ ቀበሯት፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› › ተብሎ ትንቢት የተናገረውን ሲተረጉሙት ‹‹ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታሳርፈው የመቅደስህ ታቦት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ›› ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ /መዝ. 131፥8/፡፡

የእመቤታችንን ቅድስት ሥጋዋን ሐዋርያት ሲቀብሯት በሀገረ ስብከቱ ሕንድ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ሲመለስ እመቤታችን ስታርግ ያገኛታል ለምልክት እንዲሆነው ሰበኗን (የመግነዟን ጨርቅ) ተቀብሏት ይለያያሉ፡፡ ለወንድሞቹ ሐዋርያት ያየውን ይነግራቸዋል፡፡

ለበረከት የሰጠችውንም ሰበን ያካፍላቸዋል፤ ሐዋርያት ‹ ‹ዕርገቷን እንዴት እሱ ብቻ ተመልክቶ ለምን እኛ ይቀርብናል› › ብለው በዓመቱ ነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ ነሐሴ 16 ቀን የልባቸው መሻት ተፈጸመላቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቀ (ረዳት) ቄስ፣ ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ (ዋና ዲያቆን) አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡

በትኅትና የያዙት ሱባኤም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገቷን ለማየት አበቃቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን መሠረት አድርጋ ከነሐሴ 1-16 ጾመ ፍልሰታ በማለት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ አድርገን እንድንጠቀምበት ሥርዐት ሠራችልን፡፡

በነቢያና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጽን ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በየዓመቱ ይህን ጾም በሱባኤ በማሳለፍ ከእመቤታችን ጸጋና በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፤ ሆነናልም፡፡ የዓመት ሰዎች ይበለን፡፡

ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ተቋዳሾች ያድርገን፡፡
አሜን!

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
1.5K views17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 20:22:31
1.1K views17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 16:13:36
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ!
1.5K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 18:48:39 ✞✞ ፆመ ፍልሰታ✞✞☞
☞ሼር አድርጉት

(ጾመ ፍልሰታ) ፍልሰታ ፆም(ጾመ ማርያም) ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር የፍልሰታ ፆም ከነሀሴ 1እስከ15 ነው ቤተ ክርስትያናችን እደሚገለፀው

"እመቤታችን ያረፈችው ጥር 21ቀን ነው ሐዋርያት በድኗን ሊቀብሯት ወደ ጌተሰማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ አይተዋቸው በተኗቸው በዚህ ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን አስክሬን ወስደው በገነት አኑረውታል በ8ወር በነሀሴ ሐዋርያት አስክሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎትና በምህላ ቀብረዋታል በዚህ የቀብር ስነስርዓት ላይ ከ12 ሐዋርያት አንዱ ቶማስ አልነበረም።

ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ እየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል በዚህ ጊዜ ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያቶች አይተው ለእሱ የቀረበት መስሎት ተናዶ በፊት የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረው አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነበር ብሎ ከደመና ሊወረወር ቃጣው በዚህ ጊዜ
እመቤታችን ቶማስን አፅናንታ ከእሱ በቀር ሌላ ትንሰኤዋን እንዳላየ ነገረችው።

ቶማስም ሐዋርያት ወዳሉበት እየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን ቀበርናት ብለው ነገሩት እሱም አውቆ ምስጥሩን ደብቆ አይደረግም ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር አላቸው ለማሳየትም መቃብር ሲከፍቱ አጧት በዚህ ጊዜ"እመቤታችን ተነስታ አርጋለች ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው ለምስክርም ይሆናል ብሎ የሰጠችውን (ሰበኗን) አሳያቸው ሰበኗንም ለበረከት ቆራርጠው ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከት ተበታትነዋል በዓመቱ ትንሳዬሽን ቶማስ አይቶ እንዴት እኛ ይቅርብን ብለው ከነሀሴ 1 ጀምሮ ሱባዬ ገቡ በነሀሴ14ቀንም ትኩስ በድን አድርጕ አምጥቶ ሰጣቸው ከቀበሯትም በጟላ በነሀሴ16 ተነስታለች በዚህ ቀን ጌታ ቀድሶ እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተክርስትያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህች ጊዜ ትፆማለች።
የእመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛብን አሜን አሜን አሜን መልከም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን ።

<<< ወስብሀት ለ እግዚአብሔር >>>
<< ወለ ወላዲተ ድንግል >>
<< ወለ መስቀሉ ክቡር >>
4.2K views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 18:48:31
2.2K views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 21:05:24 የሰላም አባት ሰላምን ላክልን
2.2K viewsedited  18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 21:04:18
2.2K views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ