Get Mystery Box with random crypto!

​​ የፍቅር ንቅሣት ፀሀፊ፡ኮዜት ዳንኤል | 💫Getish💫

​​ የፍቅር ንቅሣት

ፀሀፊ፡ኮዜት ዳንኤል

ክፍል


በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ


የኔና የሮቢ ፍቅር በድጋሚ ሊፈተን ነው፤የኔና የሮቢ እናት ተጣሉ።ሮቢ ነገሩ ስላስጨነቀው ሁሉቱን ለማስታረቅ የአስትን እናት ሊያመጣት ወደ አሠላ ሄደ።ሮቢ ስልኩ ተበላሽቶበት ስለነበር እሡ በሌላ ሠዉ ስልክ ሲደዉልልኝ ብቻ ነበር ማገኘው፤እናቴም ቤቱን ለመልቀቅ አስባ ለጊዜው እዛው ሠፈር አገኘች።ለሮቢ እንኳን ነግሬው እንዲያስቆማት ማድረግ አልቻልኩም ነበር ምክንያቱም ሮቢ አልደወለልኝም፤ሮቢ አርፍዶ ነበር ቤቱን ለቀን አዲሡ ቤት እቃውን አስገብተን ስንጨርስ ደወለልኝ።ሮቢ በጣም ባይናፍቀኝ ኖሮ ቀዛ ሠአት ባላወራው ደስ ይለኝ ነበር፤አነሳሁና አዋራሁት በጣም ቅዝቅዝ ብዬበት ስለነበር ምን እንደሆንኩ ሲጠይቀኝ ሁሉንም ነገር ነገርኩት ሮቢ ምንም አላለኝም ሣወራም አይመልስልኝም በጣም ጨነቀኝ ስሙን ደጋግሜ ብጠራውም መልስ የለም ከብዙ ዝምታዎች በኀላ ያለ ምንም መልስ ስልኩ ተዘጋ።ሮቢ በጣም ሲከፋው ምንም አይናገርም ዝምታን ነው ሚመርጠው፤ምንም አያጠያይቅም አሁን ሮቢ በጣም ከፍቶታል።እኔም ሀዘኔን ዋጥ አድርጌ እሡን እንዳላፅናናው እንኳን እንደ ሌላው ጊዜ አብረን አይደለንም ሌላው ቢቀር እንኳን ስልኩ አይሠራም።ሮቢ በነጋታው ከተረጋጋ በኀላ ደወለልኝ እዛ ምንም እንደማይሠራ እና ቶሎ እንደሚመጣ እቤትም መጥቶ እንደምንገናኝ ነገረኝ።ሮቢ በነገረኝ ቀን እቤት መጣ።ሮቢዬን ከ3 ቀን ናፍቆት በኀላ አገኘሁት፤ሁሉንም ሠላም ብሏቸው እኔ ጋ ሲደርስ ተያየን እና ተቃቀፍን።እስኪሄድ ድረስ አቅፎኝ ቁጭ አልን፤ማም እያየችን ትገረማለች ምንም ብንፈተን ፍቅራችን ይበረታል እንጂ ቀዝቅዞ አያውቅም ነበር።ከሮቢ ጋ በዚህ መንገድ እሡ እቤት እየመጣ መገናኘት ጀመርን።ከነ ሮቢ ቤት ነሀሴ 21/2010አ.ም ነበር የወጣነው፤ማም የተሻለ ቤት ስታገኝ ነሀሴ 28/2010አ.ም ጭራሽ ሠፈሩን ለቀን ወደ ሌላ ሠፈር ገባን።የገባን ቀን ለሮቢ በምልክት እየነገርኩት መጣ።ሮቢ አዲስ የተከራየንበት ቤት ሁሌ ይመጣል፤ቢያንስ አሁንም ሮቢዬን አገኘዋለው ለኔ ይሄ በቂ ነበር።እንግዲህ በዚህ ሁኔታ 2011 መጣው መጣው ተቀበሉኝ ማለት ጀመረ።መስከረም 1/2011አ.ም ሮቢዬ ወደ ከሠአት እቤት መጥቶ አብረን በአሉን ደስ ብሎን አሣለፍን።ለ10ኛ ክፍል ሁለታችንም መዘጋጀት ጀመርን፤ት/ትም ተጀምሮ እንደ በፊታችን ት/ቤት መገናኘት ጀመርን ቅዳሜ ቅዳሜ ደግሞ ሮቢ እቤት እየመጣ አብረን እንውል ነበር።የሮቢ ልደት ህዳር ወር ላይ ስለነበር እኔ ልሠጠው ያሠብኩት ስጦታ ደሞ ጊዜ ስለሚፈልግ ስልኬ ያሉትን ፎቶዋችንን ቶሎ በማሳጠብ ጀመርኩኝ።ሁሉንም ፎቶዎች በቅርፅ ከቆራረጥኳቸው በኀላ ያዘጋጀሁት ማስታወሻ ደብተር ላይ ለጠፍኳቸው።


....ይ
......
.........ጥ
............ላ
...............ል



•.¸♡ ይ ጥላል ♡¸.•