Get Mystery Box with random crypto!

​​ የፍቅር ንቅሣት ፀሀፊ፡ኮዜት ዳንኤል | 💫Getish💫

​​ የፍቅር ንቅሣት

ፀሀፊ፡ኮዜት ዳንኤል

ክፍል


በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ


ሁሉንም ፎቶዎች በቅርፅ ከቆራረጥኳቸው በኀላ ያዘጋጀሁት ማስታወሻ ደብተር ላይ ለጠፍኳቸው።የቀረው ቦታ ላይ የፍቅር ጥቅሶች በመፃፍ፣የተለያዩ ስዕሎችን በመሣል እና ለየት ያሉ ፅሁፎችን በመፃፍ ደብተሩን በደምብ ካስዋብኩት በኀላ ከጀርባው የቀረው ቦታ ላይ ከተዋወቅን ጀምሮ ያሣለፍነውን የማይረሣ ጊዜ ፅፌ ካሠብኩት ቀን ቀድሜ ጨረስኩ።ምንም እንኳን ከነ ሮቢ ቤት ብንወጣም አንድ ቀን እንኳን ርቀታችን እንዲሠማኝ አያረግም ነበር፤በቻለው ሁሉ ባገኘው አጋጣሚ ያገኘኛል።በስልክ ምናወራበት ሠአትም በጣም ብዙ ስለሆነ ሁለታችንም አብረነሸ ያለን ያህል ነበር ሚሠማን ግን ከኔና ከሡ ችግር ፍቅር የያዘው ይመስል ሁሌ አብሮን ነው።ጥቅምት ወር መጨረሻ አከባቢ እኔ ስልኬን ት/ቤት ተሠረኩኝ፤ያው ስልኬ ለኔ ስልክ ብቻ አልነበረችም ሮቢ አጠገቤ እንዳለ እንዳስብ ምታረግ ትልቅ ሀይልም ነበራት።ነገር ግን እናቴ ሁሉንም ነገር ስለምታውቅ በሷ ስልክ መደዋወል ጀመርን፤መቼም ከምንም ይሻላል።ህዳር 4 የሮቢ ልደት ነበር፤ምንም እንኳን ስልክ ባይኖረኝም ከሁሉም ሠው ቀድሜ ሮቢዬን መልካም ልደት የምልበት እድል አላጣሁም ነበር።የልደቱ ቀን እኔ ከቤት መውጣት ስላልቻልኩ እሡ እቤት መጥቶ ተገናኝተን በዛውም ያዘጋጀሁለትን ስጦታ ሠጥቼው ብቻውን እንዲያየው ነገርኩት።ሮቢ ስጦታውን እንዳየው ደውሎልኝ ብዙ አወራን፤በጣም ደስ ብሎት ነበር እኔም የሡ ደስታ ተጋብቶብኝ ደስተኞች ሆንን።ሰከንድ ሰከንድን፤ደቂቃ ደቂቃን፤ሠአት ሠአትን፤ቀናት ቀናትን እየተኩ ህዳር 15 ቀን ፍቅር ከጀመርን 9ወር ከ10 ቀን በኀላ ቀለበት አደረገልኝ።በጣም የተለየ ስሜት ነበር የተሠማኝ እንዴት ብዬ ላስረዳቹ በቃ ያላያችሁ ስታዩት ያያችሁ ደሞ የተሠማችሁን አስታውሣቹ ትንሽ ከገባቹም ተረዱኝ።ቀኑን ሙሉ ማታም ቁጭ ብዬ ቀለበቴን ሣየው አደርኩኝ።ሮቢ promise ካረገልኝ በኀላ ፀባዩ ቀስ በቀስ መለወጥ ጀመረ።



....ይ
......
.........ጥ
............ላ
...............ል



•.¸♡ ይ ጥላል ♡¸.•