Get Mystery Box with random crypto!

​​ የፍቅር ንቅሣት ፀሀፊ፡ኮዜት ዳንኤል | 💫Getish💫

​​ የፍቅር ንቅሣት

ፀሀፊ፡ኮዜት ዳንኤል

ክፍል


በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ


ሁለታችንም ዝም ዝም ብቻ እንደምንም አፌን አላቅቄ ሮቢ አልኩት፤ መጥቶ አቀፈኝ።ይኸዉልሽ ርብቂ ሚም ፈቅዳለች አለኝ እየሣቀ እስካሁን እንዳዘነ ያስመሠለው surprise ሊያረገኝ ፈልጎ እንደሆነ ነገረኝ።ደስታዬ አሳብዶኝ ዘልዬ ተጠመጠምኩበት።ሁሉንም ነገር ያወሩትን አንድ በአንድ ነገረኝ፤ማምን ጠርቷት ውጪ እንደወጡ እሡ ምንም ሣያወራ<ሮቢ ይኸውልህ ለምን እንደፈለከኝ አውቃለው ያንተና የርብቃ ፍቅር ብዙ ተፈትኗል ግን የእናንተ ፍቅር እንኳን ሊቀንስ ይበልጥ ጨመረ፤የሁለታችሁንም ፀባይ እያስተዋልኩ ነበር እናንተን መለየት ፈፅሞ ማይታሠብ ነው እግዚአብሔር ያጣመረውን ማንም መለየት አይችልም>ብላው ፍቅራችንን እነሸደመረቀችልን እና እሡንም ብዙ እንደመከረችው ነገረኝ።
የዛሬው ደስታዬ ልክ አጣ፤ወደ ማታ አከባቢ የተጠራው ሠው ሁሉ ተሸኝቶ እኛ ተሠብስበን መጨዋወት ጀመርን።ሌሎቹ ምርቃቱን ሲያከብሩ እኔና ሮቢ ደግሞ የፍቅራችንን የነፃነት ቀን እያከበርን በጣም ተደስተን አሣለፍን።ከዛ በኀላ ያሉት ቀናቶች ሁሉ በጣም ደስተኛ እየሆንን የፍልሠታ ፆም ደረሠ።ፍልሠታን አብረን ማስቀደስ ጀመርን፤የ6 ወራችን ማግስት ጊዜ አልሄድንም ነበር ሳናስበው በጣም ለየት ባለ መንገድ አከበርነው፤ቤቱን ቀለም እየቀባን ደስ የሚል ቀን ነበር አንዴ ፊታችንን አንዴ ፀጉራችንን እየተቀባን ቤቱን ቀብተን ጨረስን።ነሀሴ 14/2010አ.ም እኔና ሮቢ መንገድ ላይ ቆመን እያወራን ሶስት ወንዶች ከፊታችን መጡ፤ልክ አጠገባችን ሲደርሱ ቆሙና አንዱ ልጅ እኔን ጎተተኝ ሮቢ እኔን ሊያስለቅቀኝ ሲሌ የቀሩት ሁለት ልጆች ከሗላ ይዘውት ቸመዞሪያ እንኳን ጊዜ ሣይሠጡት በጩቤ ወጉት፤ሮቢ አይኔ እያየ ከፊቴ ሲወድቅ ነበር ከዚ እውነት ከሚመስል አስፈሪና አስቀያሚ ቅዠት የነቃሁት፤ልክ እንደተነሳው የእውነት የሆነ ይመስል የሆነውን እያስታወስኩ አለቀስኩ።ከእናቴ ጋ ስለነበር የተኛሁት ሳለቅስ ተነስታ ምን እንደሆንኩ ስትጠይቀኝ ነገርኳት፤እሧም ሁኔታዬ አስገርሟት እየሣቀች ጠግቦ በልቶ ስለተኛ ነው አለችኝ፤እኔም የሠጠችኝ ምክንያት ፈገግ ቢያስብለኝም ሮቢን እስካገኘው እና ምንም እንዳልሆነ እስካረጋግጥ አላመንኩም።አይነጋ የለ ያ የጭንቅ ለሊት ነግቶ ሮቢን አገኘሁት፤ያየሁትን ህልም ስነግረው ሆዱን እስኪያመው በኔ እንደዛ መሆን እየሣቀ እሡም እናተሰ እንዳለችኝ ጠግቦ በልቶ ስለተኛ እንደሆነ ነገረኝ።እኔም እያሾፍኩ ሁለተኛ ጠግበህ እንዳትበላ አልኩት፤ሁለታችንም ተሣሣቅን።
ቀናቶችም እየበረሩ መቼም ህይወት ብዙ ስሜቶች ሚፈራረቁባት ናት፤ደስታ ሲኖር ሀዘን ይኖራል።የኔና የሮቢ ፍቅር በድጋሚ ሊፈተን ነው።


....ይ
......
.........ጥ
............ላ
...............ል



:..。o○ ይ ጥላል .... .... ○o。..: