Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም እና ጥበብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ getami_mintesnot — ግጥም እና ጥበብ
የቴሌግራም ቻናል አርማ getami_mintesnot — ግጥም እና ጥበብ
የሰርጥ አድራሻ: @getami_mintesnot
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.60K
የሰርጥ መግለጫ

የግጥም መፀሐፎች
የግጥም ድምፆች
አንዲሁም የተለያዩ የጥበብ ወጥቶች ምቀርብበት
ኑ ይቀላቀሉን☺☺☺
እባካቹን ተቀላቀሉን

✋አንዴ🤚
አስተያየት ካላቹ
👇👇👇👇👇👇👇👇
Contact me @Mintesnot_suleyman

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-06-09 19:01:19 // አዳም ምን ይል ይሆን \\
የመጀመሪያው ሰው
ዝንጀሮ ነበረ
ከእለታት በኋላ
እየተቀየረ እየተቀየረ
የፍጥረታት አባት
አዳምን መሰለ
ይህን አውቆ ቢሆን
አዳም ምን ይል ይሆን

ነጭነት ንጉስ ነው
ጥቁር ደግሞ ባርያ
ታላቅ ቋንቋ እንትን ነው
ታናሽ የነእንትና
በብሔር በጎሳ
በአገር ተከፋፍለን
ይህን አውቆ ቢሆን
አዳም ምን ይል ይሆን

ሰውና እንስሳ
አንድ ላይ ሲ፡ዳሩ
ወንድ ከወንድ ጋር
ሴት ከሴት እያሉ
ተፈጥሮን ታሪክን
እረስተው ሲኖሩ
እንትና ይገደል
ሺ አመት ይንገስ እሱ
የኔ አምነት ትክክል
ህግን እየጣሱ
ባልኖሩበት ሰአት
በታሪክ አሻራ ውለታ እየረሱ
በዛኛው ጊዜ ቂም
ዛሬን ሲያቆሽሹ
ይህን አውቆ ቢሆን
አዳም ምን ይል ይሆን

ልገምት

አዳም: ምን አቅም አለኝ እኔ
እንዴትስ ያምኑኛል
ፈጣሪ እንኳን መጥቶ
ሰቅለው ገለውታል


በሰፊ አብዴ
752 viewsፍቅርን በፍቅር ፈልገው, 16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 18:06:45 ሰለ ጠፋውባችሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ
509 viewsፍቅርን በፍቅር ፈልገው, 15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 18:04:33 ​​​

በሰሞነ ሁዳዴ ህዝበ አዳም ፈሰከ፣
ለአምላኩ ታምኖ ለሴት ተማረከ።
እድሜ ላማረ ጥርስ ለገዳይ ፈገግታሽ፣
ስትስቂ ነው አሉ ስንቱን ፆም ያስፈታሽ።
.
.
"እድሜ ለፈገግታሽ"
.
.
የሚበር አሞራን 'ባንድ ተኩስ የምጥል፣
ከመንጋ ንብ መሃል ንግስት የምነጥል፣
ስሜ እንኳን ሲጠራ ልብ የማንጠለጥል፣
ኩሩ ጀግና ነበርኩ ሺ ገዳይ ባገሩ፣
ጠልፎ ጣለኝ እንጂ የሳቅሽ ገቢሩ።
.
.
በጥርስሽ ውብ ስንኝ በተደረደረው፣
አምላክ በጥበቡ ለጉድ በሰደረው።
ምን ተጋብቶት ይሆን የሚያደናቅፈኝ፣
በምንስ ስሌት ነው ሳቅሽ የጠለፈኝ።?
ብዬ አልጠይቅሽ ሸንጎ አልሰይም ነገር፣
ሀጃ አታውቅም ነፍስሽ ከመፈገግ በቀር።
.
.
እድሜ ለፈገግታሽ፤
እድም ላማረ ጥርስ፤
ልክ እንዳ'ባቶቼ ልክ እንደ ትላንቱ፣
ታንክ በከዘራ እንደማረኩቱ።
"ዘራፍ ወንዱ!
ቅጥሬን እንዳታልፉ አትንኩኝ" አልልም፣
በሳቅ ትጥቅ የፈታ ምርኮ አይሸልልም።
እድሜ ለፈገግታሽ፤
እድሜ ለጥርሶችሽ፤
እጅ የሰጠ ልቤ ከ'ግርሽ ስር የዋለ፣
ጀግና መች ይሆናል "ጀግና ነኝ" ስላለ።
.
.
ቢሆንም ቢሆንም፤
ብርቱ ነው የኔ ልብ ለሳቅ አይረታም፣
ላንዲት ቆንጆ ብዬ፤
እንኳን ቀበቶዬን ጫማዬን አልፈታም።
ያ ደማቅ ፈገግታሽ፤
የሳቅ ስርቅርቅታሽ፤
እያወናበደ ሩህ ቢወሰውስም፣
እኔ ያባቴ ልጅ!፤
ለምትስቅ ኮረዳ ልቤን አላውስም።
ማርኮ እንደረታ፤
ምሮ እንደፈታ፤
ከዘመን ቀድሜ፤
እንዲህ ስል የሸለልሁ በቀዬው ያናፋሁ፣
እንኳንስ ፈግገሽ፤
አይንሽን ሳይ ገና 'ባፍጢሜ ተደፋሁ።
( ድንቄም ያባቱ ልጅ¡¡ )

ተመልከች እንግዲህ፤
በየጥጋጥጉ በየሰርጣሰርጡ፣
ሀዘን የደረቡ ሳቃቸውን ያጡ።
እልፍ ያገሩን ሌጣ ስቀሽ ስታክሚ፣
የታረዘች ነፍሱን ሀሴት ስተሸልሚ።
እኔ ያንቺ ምርኮ በግዞትሽ ያለሁ፣
በሳቅሽ ታምሜ አልጋ ላይ ውያለሁ።

እናም የኔ አበባ፤
እንደ መ'ዳኒቴ ልክ እንደ እናቴ እቅፍ፣
ስንኩል ቀን ሸሽጎ ክፉ እንደሚያሳልፍ።
ሰርክ እየታወስሺኝ ስለምትናፍቂኝ፣
ፈገግታሽን ይዘሽ ነይና ጠይቂኝ።


ተጽፎ በሰፊ አብዴ
562 viewsፍቅርን በፍቅር ፈልገው, 15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 13:30:20 ከግጥሞቼ

አሁን ምን ይሉታል?
===========
የተጎዳዉ እኔ የተጎሳቆልኩኝ
ከትቢያ ወድቄ አፈር የመሰልኩኝ
ሰዉነቴ ኮስምኖ የተንከራተትኩኝ
እያለዉ
ያንተን ማለቃቀስ ምን ሚሉት ሸፍጥ ነዉ?
የጎዳኸኝ አንተ በነፍሴ የተጫወትክ
እንዳሻህ የሆንክብኝ ሒወቴ እስኪታወክ
በጥብጠ የለቀከዉ ሰላሜን እየናጥክ
ያንተን እሪ ማለት አሁን ምን ይሉታል
ብታታልል ሰዉን እንጅ አምላክ እንዴት ይታለላል?
ተቀጣዉ ተመታዉ አንተ ባጠፋኸዉ
ዝምታ መረጥኩኝ አንት ሰላመጣኸዉ
በይሁን እሺታ እራሴን በሰጠዉ
ምን ይሉታል ደርሶ ተጎዳዉኝ ማለት
እንዴት ብትንቀኝ ነዉ የሄን ያህል ድፍረት??

ተፃፈ በሰላም ቢሻዉ
share and join us

@learneachother
For any comment

@selamnene
552 viewsSelam Bishaw, 10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 21:45:01 ከግጥሞቼ

ማህደረ-ታሪክ
=========
ይነበባል እንጂ፤ መች ተፅፎ ያልቃል?
ይቀለማል እንጂ፤ መች ብፅር ይበቃዋል?
የሰዉ ልጆች ፍዳ፤ ሰቆቃችን በዝቶ
የዘራነዉ ሁሉ፤ አሜኬላ አፍርቶ
የእግራችን ሰንሰለት፤ ይዞን እንዳንሄድ
እዛዉ እየሮጥን፤ ጊዜዉ ሲገባደድ
የዘመናት ታሪክ እያሸጋገረ፤ ዉጊያና ጦርነት
የተፃፈን ልንደግም፤ ከቀን ስንሟገት
ብዕር ተለየ እንጂ፤ ወረቀትን ወልዶ
እራሱን ሲሸልም፤ በዘመን ተገዶ
የያዘዉን ሲጥል፤ በቆጥ ባለዉ ሽሚያ
ባጣ ቆዩ ሲሆን፤ የአንድኛዉ ጉያ
በሽግግር ሂደት፤ በደረስንበት ልክ
ለማጥፋት ብንጥር፤ ስንደልዝ ታሪክ
ገሸሽ ላይል ከመስመሩ፤ ከተፃፈበት
ማይነበብ ሚነበብም፤ ድንግዝግዝ ያለ እዉነት
እያጋባ ከግራዉ ጎን፤ ምናለበት ቢያጣምረዉ
ለኛስ እድሜ የከበደን፤ግራዉ ሳይሆን የቀኙ ነዉ
ምኑስ ቢሆን ማጥፊያ ያለዉ፤ ከስራስ ጫፍ ላይ
ቢገለበጥ ባዶ እንዲሆን፤ ወረቀት ሳይ
የማንን ታሪክ፤ ላበላሸዉ ልሰርዘዉ
ለካስ ላጲስ፤ ባሁን ስአት ነዉ ሚያስፈልገዉ
ተዉ ባይ ላጣ፤ ታሪክ አጠልሺ
እምቢን እንጂ፤ የምን እሺ
ስር ስር ሄዶ፤ እያጠፉ
ለሚመጣዉ አዲስ ትዉልድ፤ ምቹ ህይወትን ይፃፉ
አዎ ሀገር ወዳድ፤ አቅላሚ ነኝ
ስሳሳት ግን፤ ቶሎ አርሙኝ
በእርማት ማይሽር ካለ፤ የፅሁፍ ጠባሳ
እንዳይሳሱ ሊያስወግዱ፤ት በክፉ እንዳንወሳ።

ታሪክ የሰዉ ልጆች ማህደር ነዉ በርግጥም መልካምም መጥፎም ይገጥመናል ሆኖም ነገ ለሌሎች ማህደር አርገን ለምናስቀምጠዉ ነገር እንጠንቀ።

ተፃፈ በሰላም ቢሻዉ

share and join us

@learneachother
For any comment

@selamnen
683 viewsSelam Bishaw, 18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ