Get Mystery Box with random crypto!

ከግጥሞቼ ማህደረ-ታሪክ ========= ይነበባል እንጂ፤ መች ተፅፎ ያልቃል? ይቀለማል እንጂ፤ መ | ግጥም እና ጥበብ

ከግጥሞቼ

ማህደረ-ታሪክ
=========
ይነበባል እንጂ፤ መች ተፅፎ ያልቃል?
ይቀለማል እንጂ፤ መች ብፅር ይበቃዋል?
የሰዉ ልጆች ፍዳ፤ ሰቆቃችን በዝቶ
የዘራነዉ ሁሉ፤ አሜኬላ አፍርቶ
የእግራችን ሰንሰለት፤ ይዞን እንዳንሄድ
እዛዉ እየሮጥን፤ ጊዜዉ ሲገባደድ
የዘመናት ታሪክ እያሸጋገረ፤ ዉጊያና ጦርነት
የተፃፈን ልንደግም፤ ከቀን ስንሟገት
ብዕር ተለየ እንጂ፤ ወረቀትን ወልዶ
እራሱን ሲሸልም፤ በዘመን ተገዶ
የያዘዉን ሲጥል፤ በቆጥ ባለዉ ሽሚያ
ባጣ ቆዩ ሲሆን፤ የአንድኛዉ ጉያ
በሽግግር ሂደት፤ በደረስንበት ልክ
ለማጥፋት ብንጥር፤ ስንደልዝ ታሪክ
ገሸሽ ላይል ከመስመሩ፤ ከተፃፈበት
ማይነበብ ሚነበብም፤ ድንግዝግዝ ያለ እዉነት
እያጋባ ከግራዉ ጎን፤ ምናለበት ቢያጣምረዉ
ለኛስ እድሜ የከበደን፤ግራዉ ሳይሆን የቀኙ ነዉ
ምኑስ ቢሆን ማጥፊያ ያለዉ፤ ከስራስ ጫፍ ላይ
ቢገለበጥ ባዶ እንዲሆን፤ ወረቀት ሳይ
የማንን ታሪክ፤ ላበላሸዉ ልሰርዘዉ
ለካስ ላጲስ፤ ባሁን ስአት ነዉ ሚያስፈልገዉ
ተዉ ባይ ላጣ፤ ታሪክ አጠልሺ
እምቢን እንጂ፤ የምን እሺ
ስር ስር ሄዶ፤ እያጠፉ
ለሚመጣዉ አዲስ ትዉልድ፤ ምቹ ህይወትን ይፃፉ
አዎ ሀገር ወዳድ፤ አቅላሚ ነኝ
ስሳሳት ግን፤ ቶሎ አርሙኝ
በእርማት ማይሽር ካለ፤ የፅሁፍ ጠባሳ
እንዳይሳሱ ሊያስወግዱ፤ት በክፉ እንዳንወሳ።

ታሪክ የሰዉ ልጆች ማህደር ነዉ በርግጥም መልካምም መጥፎም ይገጥመናል ሆኖም ነገ ለሌሎች ማህደር አርገን ለምናስቀምጠዉ ነገር እንጠንቀ።

ተፃፈ በሰላም ቢሻዉ

share and join us

@learneachother
For any comment

@selamnen