Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም እና ጥበብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ getami_mintesnot — ግጥም እና ጥበብ
የቴሌግራም ቻናል አርማ getami_mintesnot — ግጥም እና ጥበብ
የሰርጥ አድራሻ: @getami_mintesnot
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.60K
የሰርጥ መግለጫ

የግጥም መፀሐፎች
የግጥም ድምፆች
አንዲሁም የተለያዩ የጥበብ ወጥቶች ምቀርብበት
ኑ ይቀላቀሉን☺☺☺
እባካቹን ተቀላቀሉን

✋አንዴ🤚
አስተያየት ካላቹ
👇👇👇👇👇👇👇👇
Contact me @Mintesnot_suleyman

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-28 22:19:54 ከግጥሞቼ

ያለ እሮሮ
======
ቁና ቁና አለኝ ሰዉ፤ አለኝ ሀገር
ቀብርም እድል ሲሆን በምድር
ከብረዉ አብረዉ በኖሩበት
አንሺ ማጣት
የለቅሶን ወግ ማን አየበት
ይባል ኖሯል በዚ ህይወት
ቁና ቁና አለኝ ፍቅር ፤ አለኝ መንደሩ
የወዳጅ ቢላ ሲሳል በግብሩ
ቁና ቁና ነዉ አሁንስ ኑሮ
አንዴት ይቅለለን ያለ እንጉርጉሮ
ያለ እሮሮ
እየደለቁን እንደ ከበሮ

ተፃፈ በሰላም
share and join us

@learneachother
@selamnen
329 viewsSelam Bishaw, 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 20:13:29 ከግጥሞቼ
ኖርማል
=====
ሲፋጭልኝ አልስቅም!
ሲፋጭብኝ አላፍርም!

ተፃፈ በሰላም
መልካም ምሽት::
share and join us

@learneachother
@selamnen
463 viewsSelam Bishaw, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 23:27:22 .........#ትዝ_አለኝ...........

በሀይለኛው ዝናብ በዛ በክረምት
በጎርፍ በጭቃ በመብረቁ ምት
ምንም ሳይገድበን እንኳን ንፋስ ብርድ
ማንንም ሳንሰማ በፍቅር ስንነድ
ከሩቅ ለሚያየን እንመስላለን እብድ
ክፍሌ ቁጭ ብዬ ትውስ ስትይኝ
ልገልፅሽ እልና በአጫጭር ስንኝ
ምሆነውን ያሳጣኛል ናፍቆትሽ ብሶብኝ
ናፍቆቴን ለመወጣት እንዳላገኝሽ
ደውዬ ላግኝሽ ናፍቆቴ ነይሊኝ ልልሽ
ፈራውኝ ክረምቱን ብርድ እንዳይመታሽ
ግን አያስችለኝም ብዙም ሳልቆይ
እደውላለሁኝ ውጪውን ሳላይ
ሄለው ስትይኝ ድምፅሽን ስሰማው
በትንሹ ይሻለኛል ኡፈይም እላለው
ፍቅሬ ማሬ ነፍሴ አለሺሊኝ ወይ
እንገናኝ እላታለሁ ውጪውን ሳላይ
ዝናብም በረዶ ቢዘምብም ምንም
ዴንታም አይሰጠኝም ከልካይ የለኝም
ኑዛዜዬን ሰምተሽ ስጨርስ አውርቼ
መልስሽን ሳልሰማ እሩጬ ወጥቼ
ቀጠሮው ቦታ ደረስኩኝ እሮጬ
መች ልብ አልኩና ክረምት መሆኑን
ልብም አላልኩ ዝናቡ መኖሩን
ሰው ዣንጥላ ይዞ ሲያልፍ ከፊቴ
ሰላም ብላኝ ስቴድ አንዱዋ ጎሮቤቴ
የዛኔ ነው ያወኩት ለካ ዝናብ ነው
መምጣቴ ትዝ ሲለኝ መልሱዋን ሳልሰማው
ተስፋ ቆረጥኩ ትቀራለች ብዬ ዝናቡን ፈርታው
ተስፋ ቆርጬ በዝናብ ቆሜ ተገትሬ
እንዳልዝናና እንደሌላ ግዜ በወፎች ዝማሬ
ለካ እነሱም ሸሽተው
ዝናቡን ኖሩዋል ፈርተው
ከቤታቸው ሳይወጡ ተሸሽገው
ይመለከቱኛ በኔ ሁኔታ አዝነው
ተስፋ ቆርጬ ልሄድ ስል ወደ ቤት
የሆነ ሰው ታየኝ በጣሙን አምሮበት
ሂወቴን ሳያት ለማመን አቃተኝ
እየቀረበች ስትመጣ ምሆነውን አሳጣኝ
ዘልዬ አቀፍኩዋት ጥምጥም አልኩባት
ቀና ብዬ ከንፈሩዋን አጥብቄም ሳምኩዋት
ሂወቴ እስትንፋሴ አለኝታዬ እያልኩዋት
ድጋሚ አጥብቄ በደምቡን አቀፍኩዋት
አፀፋውን እሱዋም በደንቡን ስትመልስ
ለካ ፈልጋ ኖሩዋል ናፍቆቷን መተንፈስ
ይሄ ሁላ ሲሆን ዝናቡ መዝነቡን እንደዛው ቀጥሏል
ልብሳችን ሰውነታችን እንዳልሆነ ሆኑዋል
አይገርምም እኛ ግን ረስተነው ኖሩዋል
እንግዲ ፍቅር ነው ምንስ ይደረጋል
ከቅፌ አውጥቼ ልናገር ስል ፍቅሬን
አጥብቃ ሳመቺች አማላይ ከንፈሬን
ለካ ከኔ በላይ አብዳ ምቶነው አታለች
ዝናቡ ሳይበግራት እኔን እኔን እያለች
በኔ ፍቅር ለካ እጅጉን አብዳለች
ከዛማ ጨለልን ሁለታችን ብቻ በፍቅር አበድን
በዛ በክረምት በፍቅር አንድ ላይ እንደህፃን ቦረቅን
አይ የኔ ፍቅር ትዝ ይለኛ ያኔ እንደዛ ስንሆን
የማይረሳ ፍቅር ነው እኮ ያለን

#በሰፊ_አብዴ
479 viewsፍቅርን በፍቅር ፈልገው, 20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 22:06:06 ከግጥሞቼ
እንስከን
=====

በሰከነ መንፈስ መነጋገር ሲቻል
ሁልጊዜ፤
እየገነፈሉ ማቃጠልስ ይሰለቻል።

ተፃፈ በሰላም
share and join us

@learneachother
@selamnen
402 viewsSelam Bishaw, 19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 19:57:27 ከግጥሞቼ

እንዴት ሆነዉ ይሆን?
============
እንዴት ያማል! አሉ በጣም ያመማቸዉ
ፍርሀትን ሰጉ ፍርሀት የያዛቸዉ
የነርሱ ገብቷኛል አልገባ ያለኝ ግን
ህመም ከፍርሀት ጋር ሞትን አስከትሎ በግፍ የተሰዉ እንዴት ሆነዉ ይሆን ?
ይከብዳል! ያስፈራል!


ተፃፈ በሰላም
share and join us

@learneachother
@selamnen
396 viewsSelam Bishaw, 16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 14:52:54
584 viewsፍቅርን በፍቅር ፈልገው, 11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 14:52:45 #ወይ_አለማወቅ

#ይህንን_ድንቅ_መፅሀፍ_ተጋበዙልኝ!

በህይወት ሊደርሰብን የሚችለው የመጨረሻው ክፉ ነገር ቀድሞ ደርሶብናል!"
.
የመኖር ትልቁ ጥቅም አጋጣሚ መሆኑ ነው። መኖር አጋጣሚ ነው ብዬ ነው ዘባረቅሁ? ትልቅ አጋጣሚ። እንደሁሉም አጋጣሚዎች መኖር ሁሉት ዕድል ይሰጠናል። በአንድ ወገን የመለምለም፣ የማወቅ፣ የመርካት፣ የመሰፋት..አልያም ደግሞ የመደኽየት ፣ የመሰነፍ፣ የመሳሳት፣ የመጥበብ...ከተወለድንባት ሰከንድ ጀምሮ ህይወት በአጋጣሚዎች የተሞላች ነች።የምናገኛቸው አጋጣሚዎች በጠቅላላ ማለትም ወላጆች፣ ጎረቤት፣ ትምህርት፣ የሰፈር ልጅ...ሁሉም የማናውቀው ሁኖ ለህይወታችን የብርሀን ምንጭ ይሆናል ወይም የድቅድቅ ጨለማ መነሻ ይሆናል።
.
ሰው መሆን ይቻላል፣ የሚቻል ነገር ነው። ዋናው ጉዳይ ሰው እንድንሆን ወይም እንዳንሆን በሌላ ወገን ደግሞ ሙሉ ሰው ' ወይም ጎዶሎ ሰው 'እንድንሆን የሚያደርገን ምንድን ነው? አጋጣሚ ? መልካም ምክር ? መልካም ሀሳብ በፍፁም! መልካም ሀሳብ ክፉ ሀሳብ፤ መልካም ምክር የሚባል የለም! ቢያንስ እኔ ያለ አይመስለኝም። ሙሉ ሰው የምትሆነው በአንድ ምክንያት ብቻ ነው። ማሰብ በመቻል!
.
አንድን ሀሳብ መልካምም ሆነ ክፉ የሚያደርገው የሀሳቡ ምንነት ሳይሆን የአሳቢው ማንነት ነው። የትኛውም መልካም' የሚባል ሃሳብ ድንጋይ ላይ እንደፈሰሰ ውሃና 'ጥሩ መጥበሻ ላይ እንዳረፈ ዘይት ኮለል ብሎ ሊወርድ ይችላል፤ መጥበሻውም አይዝ ድንጋዬም አይበሰብሰ። በአንፃሩ ደግሞ የሃሳብ ጠብታ እየቆየ እየቆየ ድንጋይን የሚቦረቡርበት አጋጣሚም አለ ልክ እንደ ውሃ።
.
የሀሳብ አሳቢ የማይቦረቦር ድንጋይ ከሆነ ሀሳብ ይመክናል። ማሰብ ግዴታ ነው። ይህ የሆነው ደግሞ የሌለንን እና ያለንን የምናውቅ ማሰብ ስንጀምር ብቻ ሰለሆነ ነው። እያንዳንዱ አጋጣሚ የማሰብ አጋጣሚ ነው። በእያንዳንዱ አጋጣሚ ማሰብ የቻለ #ሙሉ_ሰው_የመሆን ዕድል ይኖረዋል። በእያንዳንዱ አጋጣሚ ማሰብ ያቃተው ደግሞ አንደ በጋ ምንጭ እያደር ይደርቃል፤ አንደ በጋ ቅጠል አድሮ ይጠወልጋል። #ማሰብ_ብቻ_ሙሉ_ሰው_ያደርጋል።
.
ለዚህ ነው ሊደርሰብን የሚችለው ክፉ ነገር ሁሉ ቀድሞ ደርስብናል ያልኩት። በህይወታችን ሊደርሰብን የሚችለው ብቸኛው አሰቸጋሪ ነገር አልፏል። ይህ አጋጣሚ ምንድን ነው? መወለድ! መወለድ ነው!

.
መወለድ #የመጀመሪያውም_የመጨረሻውም አሰቸጋሪ የህይወት ገጠመኝ ነው። ከዚህ በኋላ ያለው ሁሉ የመወለድ ምንዛሪ ነው። ባንወለድ ኖሮ ምንም አይገጥመንም። አያሳዝንም? አያስጨንቅም? አይገርምም ?
.
እኔ እንግዲህ እንዲህ አስባለሁ እንኳንም ተወለድኩ እላለሁ። ባለወልድ ኑሮ ይህ ሁሉ ጭንቀት፣ ሁሉ ግራ መጋባት፣ ይህን ሁሉ ሀዘን፣ ይሁን ሁሉ መከራ ... ከወዴት አገኘው ነበር ? በህይወት ውሰጥ መከራ፣ ሃሳብ፣ ትካዜ፣ እና ጭንቅላት የመኖሩን ያሀል ስኬት፣ ደስታ፣ ፍሰሃና፣ ተድላ እንዳሉም ይነግረኛል። የእኔ ሀላፊነት እንዴት እንደማገኛቸው ማሰብ ነው!
.
አንዴ እንደሆን ተወልደናል፥ መኖር ነው። ሌላ ምን አማራጭ አለ? ሰዎች አማራጭ ያለን ሲመስለን ይገርመኛል። ራስን ለማጥፋት እንኳን መጀመሪያ መኖር ግዴታ ነው።
.
#ምንጭ_አለማወቅ_መፅሐፍ

በዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ
.
አለማወቅ ድንቅ መፅሐፍ ስለሆነች ለአቅመ ንባብ የደረሰ ሁሉ ቢያነባት ያተርፋል ብዬ አምናለሁ።
528 viewsፍቅርን በፍቅር ፈልገው, 11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 07:00:12 የኔ አለም
==+===

ሀሳብ በመብዛቱ፥
ቃላትን ልሰድር፤
የኔ አለም ነው ብዬ፥
አለምን ሳሰፍር፤
ባይኖርልኝ ኖሮ፥
ደብተር ና ብዕር፤
ይሄኔ ይሄኔ፥
እንዴት እሆን ነበር።
ምንተስኖት ሱሌይማን መሀመድ
ቀን፦23/07/2014
423 viewsራስ ምንቴ, 04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 15:28:08 ፍቺ ያጣ ቅኔ
==+==+==

ሀኪሙ ማከሙን ትቶት፤
ገባ ፖለቲካ በሽተኛ መስሎት።
ለምን ፖለቲካ?..
ሕዝብ ለመርዳት፤
በጉራ ደረቶን ገልብጦ ሲል ሰማውት።
ሄድኩኝ ከመምሕር ዘንድ ነገሩ ከብዶኝ፤
ልጠይቅ ልረዳ ፖለቲካን ስለፈለኩኝ።
መምሕሩ ጀመረ....
ማፍረስ ቀላል ነው መገንባቱ ግን ከባድ፤
ለሀገር ጠቃሚ አዋቂ ሰው ሲብድ።
ይሕ ያንተ የኔውም ጥያቄ፤
ፖለቲካን ስተነትን ከስራው እርቄ፤
መልሱን ብመልስም፤
ጣዕሙን ከአፌ ፈፅሞ አታይም።
ብለው ዘበቱብኝ ቃላት አወሳስበው፤
ይባስ ግራ ገባኝ እንዴትስ ልረዳው።

ፖለቲከኛው ሀኪም
ሀኪሙ ፖለቲከኛ፤
በማን እየታከምኩ እንዴትስ ልተኛ።
መክሊታችን ሌላ፤
ስራችንም ሌላ፤
ማሕንዲስ ተብሎ ሲሸጥ ካቲ ካላ።
ሕዝቡ እራሱ ለራሱ ሳይገባው፤
ጥበብ ጠፍቶ ሲንገላታ ሳየው።
ስልጣኔ ቢባል ፈፅሞ በጭፍን፤
ጤነኛው ታመመ በሽተኛው ሲድን።
ገንዘብ፣ነዋይ፣ፍራንካ ሁሉም አንድ ናቸው፤
ቋንቋ አጠቃቀም ፈፅሞ ማይለያቸው።
እንደዚሕ ነው ብሎ ዶክተሩም ተታሎ፤
ሙሉኝ እያለ ቢታይ እኳ ጎሎ።
ለስልጣኑ ጥም ሞያው ጥሎት፤
ፖለቲካን መረጠ ማከሙ ሰልችቶት።
አይገርምም ባይገርምም ያናዳል፤
ይሄኔ አክማለው ለስንቱ ቃል ገብቷል።
አጋጣሚ አይደል ከስልጣን መቀመጥ፤
ጨው ሆኖ ለኑ ከቶ እንኳ ማይጣፍጥ።

እስኪ ልጠይቅኽ አንተ ባለ ስልጣን፤
እረስተኽ ከሆነ ከቶ የሸመኽን።
ምን መደረግ አለብኽ፤
ማከም ትተኽ ብትይዝ ስልጣንን።
ስልጣኑስ ይሞቃል?
ለኑሮስ ይመቻል?
መንገድ ተበላሽቶ መንገዱ ሲስቸግር፤
መኪና ከመኪና ለባለስልጣኑ መቀየር።
መብራት እየጠፋ ሕዙብን ያማራል፤
ከባለስልጣኑ ቤት በጄኔኔተር በርቷል።
ታድያ በኔ ሀገር ስልጣን እንዲ ሆኗል፤
ከፍሎ አስተምሮ ስራ ያጣም በዝቷል፤
የተማረው አቤቱታ ላያቀርብ መጥቶ፤
በባለ ስልጣኑ ሲሄድ ተሰድቦ ተመቶ።
ታድያ ሕዝብ ነው የሾመው ፈፅሞ ካላቹ፤
መልሱልኝ ለኔ ወደታች ወርዳቹ።


ይድረስ በስልጣን ጥም አፋቹ ተጣሞ፤
ሀደራን ተይዞ ስልጣን ተሸክሞ።
መቀመጫ ሞቆክ ስራኽን ለረሳክ፤
ጆሮሕን ስጠኝ አንተ አሽከሬ ነክ።
አሽከር ማለት ገረድ፤
ለመኖር ብላ ወደታች ምቶርድ።
ሰርታ ሰርታ ሰርታ፤
የምትኖር ለፍታ።
በልፋቷ የተሰጣት ማረግ፤
አሽከር ናት ፈፅሞ ማትባልግ።

ሰማኽኝ ማነኽ ባለ ስልጣን፤
ዋ ብያለው ከተመካክ ወንበሩን፤
ትላንት ተመክተው የኖሩትን ካየሕ፤
እጣክ እንደነሱ መልካሙን ካልሰራሕ።
መፍታቱ ካቃተክ ስልጣን ተሸክመክ፤
መርምረው ወደታች ማን ነበርኩ ብለክ።


ያልተፈታው ቅኔ ሕብረቃሉን ይዞ፤
አንተ ሾምከኝ ይላል ተንኮልን አርግዞ።

ምንተስኖት ሱሌይማን
ቀን፦03/02/2014
@Getami_mintesnot
479 viewsራስ ምንቴ, 12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 19:49:20 ፍቅር ና ስለት

ፍቅርና ስለት በአንድ ቀን አይደርስም
መጠበቅ አለበት ብዙ የምያደክም
የተሰላቹ እንደሆን ትቶት እሚበንን
ቁሞ ለሚያየዉ ያሰኛልም ምስኪን

አቤት የኔ ነገር

በዬትኛዉ አቅጣጫ እግርሽ አቅንቷል
ዱካሽን ልከተል ዉስጤ ጉልበት አጥቶል
በፍቅር ዓለም ዉስጥ ጥርጣሬ ዬታል
እምነትን አንግቦ አንችን ብቻ ይላል

እንደዚ እንደዛ ብዬ ምተርከዉ ነገር ባይኖረንም
አዉቃለዉኝ ዉዴ ብህር ምያስጨርስ ታሪክ አያጣንም
ከጣፋጩ በፊት መራራዉን መቅመስ
መዘነጡ ሳይደርስ በእዳፊ መላወስ
የምድር እግጋት ያስቀመጡት ጠባይ
መሆኑን ታዉቂያለሽ ፡ ከልካዮቹን አልፈን ለምን አንተያይ ?

ብትሰሚም ባትሰሚም ፡ ብትወጂኝ ባትወጂኝ
ብዬማ አልገጥምም ፡ ይቀራታል እንጂ አልቋጥርም ስንኝ
አንችን ለማግኘት የሄድኩትን ጉዞ ጋራና ሸንተረር
አዉን ላይ ሳስበዉ ከሀገሬ አደለም ያሶጣኛል ከአህጉር

ብቻ ምን አለፋሽ

በዝችኛዉ ፁፌ ፡ ልገልፀዉ የሞከርኩት
ልፋቴን አደለም ላንች ከዚ በላይ ይገባሻል በእዉነት
ግና ምናገረዉ አንድ ቃል አለችኝ
በዉስጤ ሰርፃ እረፍት የነሳችኝ

"ፍቅርና ስለት በአንድ ቀን አይደርስም
መጠበቅ አለበት ብዙ የምያደክም "

#መልካም_ምሽት


በ #Safi_Abde
510 viewsፍቅርን በፍቅር ፈልገው, 16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ