Get Mystery Box with random crypto!

ከግጥሞቼ ======= ከግራህ ++++ እኔ መሆንን እንድሆን | ግጥም እና ጥበብ

ከግጥሞቼ
=======
ከግራህ
++++

እኔ
መሆንን እንድሆን
አንተን እያየዉኝ
ባይንህ ስርጉዶች ዉስጥ
እራሴን ፈለኩኝ
ፈለኳት
ምትሻትን እንስት
እሷኑ መስዬ
አንተን እንዳስደስት
አብሬ እየተጓዝኩ
ምትርህን ቃኛለዉ
የቷ ትስብ ብዬ ከብሌንህ እረፍት
አብሬ አርፋለዉ
ድንገት እኔነቴ
አንሶብህ እንዳልገኝ
ፍርሀት ቢዉጠኝ
ያቺኛዋን ወጣት
ምናብህ የሳላትን
ለመሆን ስጣጣር
ብሆን ማስመሰልን
ደሞ ተቀይረ
ሌላኛዋን ብትሻስ?
እሷን መሆን
ቢያቅትስ?
እላለዉ
እብሰለሰላለዉ
ከጎንህ መሆኔ
ከአይንህ ቢሰወርም
የሆንኩትን ስሆን
ከፊትህ አልመጣዉም
አይን ክፉ
መመኘት ነዉ ላየዉ ሁሉ
ስንቷን እንስት
በምኞት ቤት አዋልክ አሉ
እኔም ትቼ መሆንን
ሆኜ ባለሁበት ቆየዉ
ሴትነቴን ከአይንህ ሳይሆን
ከጎንህ ላገኘዉ
በግራህ ጎን ተወሽቄ
ስሪቴን ልመልከት
ያርግልኝ ግጣሜን
በዛዉ እንድከተት
ምትሻትን ሳይሆን
ምታሻህን እንስት
ሄዋንህ ነኝና
ባንተ ምትደሰት
ልዋል ልደር
ልቆይ በዚያ
ስትነቃ እንድታየኝ
አዳም'ኤ በጉያ።

ተፃፈ በሰላም
share and join us

@learneachother
For any comment

@selamnen