Get Mystery Box with random crypto!

1 ነን ==== ዘመናት ያበጀን ቀናት ያደራጀን በልዮነት አድማስ ፍቅር ያጣመረን እንደ ችቦ መብራ | ግጥም እና ጥበብ

1 ነን
====

ዘመናት ያበጀን ቀናት ያደራጀን
በልዮነት አድማስ ፍቅር ያጣመረን
እንደ ችቦ መብራት ብርሀን የፈጠርን
ህብረ ብሔርነት ቀለሙን ያተምን
እኛ አንድ ነን።
ድንጋይን ፈልፍለን ህንፃ የገነባን
በራሳችን ዘይቤ ፊደላት የሰራን
የዜማን መዋቅር ቀድመን የዘመርን
የሰዉ ልጅ መገኛ ድንቅ ተፈጥሮ ያለን
እኛ አንድ ነን።
የጊዜዉ ሁካታ ከቶ የማይረታን
የነካኩን ጊዜ ማንም የማይገታን
አሻፈረን ላልን ወኔያችን ማይላላ
በወንጨፎ ጠጠር አንገት የምንቀላ
የተባበርን ለ'ት አለም የሚፈራን
መጀገን የቻልን ከጀግኖች የተማርን
አባይን ገድበን ገድልን የገደልን
እምቢ ለጠላቴ ብለን የሸለልን
እኛ አንድ ነን።
እናም ዛሬ
የጓዳችን ኩርፊያ ጠበኛ አያድርገን
ከወንድም ቤተሰብ አያቀያይመን
መነቋቆር ትተን
ልዩነትን ጥለን
እንደጥንቱ እንስራ
ለሀገር እናብራ
የበደለን ምረን
ነገን ተስፋ አድርገን
ሀሰትን ተቃዉመን
ለእዉነት ደግፈን
ኢትዮጵያዊነትን በጉልህ እንፃፈዉ
ከቶ እንዳይደበዝዝ የኛን እንጣለዉ
እጆች ተዘርግተዉ ወደፈጣሪያችን
ድምፃችን ተሰምቶ የፀሎቶቻችን
ማረሻ አድርጎልን ሰይፍና ቢላን
ድንቁርናዉ ጠፍቶ እንሁን ሰላምን
እኛ
በነጠላ አንደበት ለስም የማንበቃ
ለየለብቻችን ጤፍ እንኳ ማንወቃ
አብሮነት ያሰረን
አምላክ የፈተለን
ከጊዮን ጠጥተን ከምድሯ የጠገብን
እንኳንስ ለዘመድ ለባዳ የተረፍን
አንጀት የሚበላዉ አነጋገራችን
የትም ማይገኘዉ ወጉ ባህላችን
አንድነትን አልፈን አንዱን ራሱን የሆን
ኢትዮጲያዊ ብቻ ሳንሆን ኢትዮጵያ ነን።
1 ነን!!!

Share and join us

@learneachother
@selamnen