Get Mystery Box with random crypto!

ለበላይ ከህብረ-ቃል መዞ ወርቁን የሚለየዉ የለየዉን እዉነት በገሀድ ሚገልጠዉ አሻፈረኝ ማይል ወቅ | ግጥም እና ጥበብ

ለበላይ

ከህብረ-ቃል መዞ ወርቁን የሚለየዉ
የለየዉን እዉነት በገሀድ ሚገልጠዉ
አሻፈረኝ ማይል ወቅሶ ለመገሰፅ
ዉሸትን ተቃርኖ ለእዉነት የሚያምፅ
ሺ'ዉ ስለተንጫጫ የማይነቃነቅ
ላመነበት ጉዳይ ራሱን የሚያሳንቅ
ወገንተኛ ያልሆነ የሰዉ ሁሉ አንደበት
የ'በላይ ነዉ ስሙ ግብሩ ለነፃነት
በ'በላይ
ጭቆና ተወግዞ
ሀቃችን ተመዞ
ከፊደላት በላይ የነርሱን ቤት መቷል
ከማስጨብጨብ ዘሎ ከልባችን ገብቷል

የህዝብ ድምፅ ማጥፋት
የጥበብ ቤት መዝጋት
ይበልጥ ያነሳ እንጂ ብዙ የህዝን ድምፅ
ይበልጥ ይፈጥር እንጂ ጥበብን የሚቀርፅ
በነካኩን ቁጥር ሲጭሩን ምንበዛ
ባንዱ የበላይ ምክንያት እልፍ የበላይ ገዛ
ለራሱ አበዛ
አንተ ጀግናዉ በላይ ብትሞትም አይቆጭህ
ለሰዉ አምላኪ ሰዉ እዉነቱን መንገርህ
ልክ ነበር ብለን እንድንል አርጎናል
ቀረ ያለነዉ እፈና ዛሬ ይፋ ሆኗል
የበላይ ልጅ ነበርክ ያዉም የኢትዮጵያ
የፊደላቶች ሀቅ የእዉነት ማሳያ!

#በላይ በቀለ ወያ የት ነዉ?!
እኔም ለርሱ ድምፅ ነኝ!!

ተፃፈ በሰላም

share and join us

@learneachother
@selamnen