Get Mystery Box with random crypto!

የ #Remedial ተማሪዎች የትምህርት ሚኒስቴርን ድንገተኛ ውሳኔ በፅኑ ተቃወሙ የግል የከፍተኛ | Freshman and Preparatory Students Channel

የ #Remedial ተማሪዎች የትምህርት ሚኒስቴርን ድንገተኛ ውሳኔ በፅኑ ተቃወሙ

የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የአቅም ማሻሻያ ትምህርታቸውን ተከታትለው በትላንትናው ዕለት የማጠቃለያ ፈተና የጀመሩ ተማሪዎች ቀሪዎቹን ፈተናዎች በቀጣይ ዓመት ይፈተናሉ የሚለውን የትምህርት ሚኒስቴር ድንገተኛ ውሳኔ በተለያዩ ቦታዎች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ውሳኔውን ተቃውመዋል።

ተማሪዎቹ በዚህ ኑሮ ውድነት ገንዘባችንን ለወራት ከፍለን በተጨማሪም የተለያዩ ጥቃቅን የማይባሉ ወጪዎችን አውጥተን፣ ብዙ ደክመን፣ ጥረን ፍፃሜው ላይ ስንደርስ በትምህርት ሚኒስቴር የፈተና አሰጣጥ ድክመት ልፋታችን መና መቅረት የለበትም ያሉ ሲሆን በዛሬው ድንገተኛ ውሳኔ ምክንያት በሚቀጥለው ዓመት ማለትም ከወራት በኋላ መፈተናቸው በፈተናው ውጤት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድርባቸው በመግለፅ ውሳኔውን እንደማይቀበሉት ገልፀዋል።

ፈተናውን አሁን ካልተቻለም ደግሞ የተማሪዎች ለፈተናው ያደረጉት ዝግጅት ብዙ ሳይጠፋባቸው በአጭር ቀናት ውስጥ ይሰጥ ዘንድ ተማሪዎች እና የተማሪዎቹ ወላጆች ጠይቀዋል።

ይህንን ድንገተኛ ውሳኔ ተማሪዎች፣የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት እንዲሁም የማሪዎቹ ወላጆች በፅኑ ተቃውመውታል።

ለኢንትራንስ ተፈታኞች
https://t.me/ATC_UEE

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news