Get Mystery Box with random crypto!

ሁለት የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች ለስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈታኞች ለመፈተን ሲሞክሩ በቁጥጥ | Freshman and Preparatory Students Channel

ሁለት የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች ለስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈታኞች ለመፈተን ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

በደቡብ ብሔር ብሔረሶባችና ህዝቦች ክልል ፈተና በተሰጠባቸዉ በሁሉም ማዕከላት ፈተናዉ ያለምንም የፀጥታ ችግር የተጠናቀቀ ሲሆን በደቡብ ኦሞ ዞን ሁለት የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች ለሌላ ሰዉ ለመፈተን በመሞከራቸዉ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው አስታውቋል ።

ተፈታኝ ሆነው ነገር ግን ሌላ ሰው እንዲፈተንላቸው አይዲ ቁጥራቸዉ ሰጥተዉ የላኩ ሁለት ተማሪዎችን ጨምሮ አራት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዉለዉ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።

ፖሊስ ኮሚሽኑ ተፈታኞችን የሚረብሽና ፈተናዉ እንዳይስተጓጎል በማድረግ የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለተባበሩ ሁሉ  ምስጋናውን አቅርቧል ። ክልል አቀፍ የስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ከሰኔ 26 እስከ ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ተሰጥቶ መጠናቀቁ ይታወሳል ።


#ዳጉ_ጆርናል

ለኢንትራንስ ተፈታኞች
https://t.me/ATC_UEE

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news