Get Mystery Box with random crypto!

#ይፋዊ የትላንት የሬሜዲያ ፈተናዎች ተሰርዘዋል። በሬሜዲያ ፈተና ሂደት ወቅት በተፈጠሩ ችግሮች | Freshman and Preparatory Students Channel

#ይፋዊ

የትላንት የሬሜዲያ ፈተናዎች ተሰርዘዋል።

በሬሜዲያ ፈተና ሂደት ወቅት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔዎች አሳልፏል።

የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ረሜዲያል ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ትናንት ሰኔ 26/2015 ዓ.ም በዩኒቨርስቲዎች መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በፈተና ሂደት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።

1) ሰኔ 26/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ።

2) ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊት በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም እንዲሰጥ።

3) በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች በተያዘው ፕሮግራም መሰረት ይሰጣል።

(ትምህርት ሚኒስቴር)

NB. ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ ትላንት ፈተናው መሰጠት ከተጀመረ በኃላ ተፈጥረዋል ያላቸውን ችግሮችን በዝርዝር አላሳወቀም።

ለኢንትራንስ ተፈታኞች
https://t.me/ATC_UEE

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news