Get Mystery Box with random crypto!

ይቅርታ - ለትውልድ ውለታ! እኛ ገንዘብ የካዱንን ይቅር ማለት ሲያቅተን አዳም ገነትንና እግዚአብ | ሰባ ጊዜ ሰባት 70*7

ይቅርታ - ለትውልድ ውለታ!

እኛ ገንዘብ የካዱንን ይቅር ማለት ሲያቅተን አዳም ገነትንና እግዚአብሔርን ያሳጣችውን ሔዋንን ይቅር አላት።

ዮሴፍ ልጅነቱን ለመከራ እቶን የዳረጉትን ወንድሞቹን በበቀል ሳይሆን በይቅርታ አሸነፋቸው።

የእስጢፋኖስ ቤተሰቦች ደም መላሽ ቢሆኑ ኖሮ ጳውሎስን በመልዕክቱ ዛሬ አናገኘውም ነበር።

ይቅርታ ለትውልድ የምናቆየው ውለታ ነው። በእርግጥም ይቅርታ የማይገባንን በሰጠን በእግዚአብሔር ፊት ሰውዬው የማይገባውን መስጠት ነው።

ዲ/ን አሸናፊ መኮንን

@forgiveeness @ahavaha