Get Mystery Box with random crypto!

አለማወቅህን አትወቅ! የሃመር ብሄረሰብ አባቶች ሲረግሙ “አለማወቅህን አትወቅ” ይላሉ። ለገባው ከ | ሰባ ጊዜ ሰባት 70*7

አለማወቅህን አትወቅ!

የሃመር ብሄረሰብ አባቶች ሲረግሙ “አለማወቅህን አትወቅ” ይላሉ። ለገባው ከባድ እርግማን ነው።

መቼም አለማወቅን ማወቅ ትልቅ ጸጋ ነው። ያላወቀ ሰው ይሰማል። ያላወቀ ሰው ይማራል።

ነገር የሚበላሸው አውቃለሁ ብለን የተቀመጥን ቀን ነው። አገር የሚጠፋው ‘አውቅልችዋለው’ ብለን ማሰብ ስንጀምር ነው።

ኢትዮጵያን ለመታደግ ስለራሳችን ምን መለወጥ አለብን ብለን ለጠየቅነው ጥያቄ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሀሳቦችን ተቀብለናል። ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

ብዙ ሰዎች የሚስማሙበት ዋንኛ ነጥብ “በጥሞና የመደማመጥ ባህል” ማነስ ነው። በጥሞና የመደማመጥ ባህል ለማዳበር እንዴት እንጀምር?

አለማወቃችንን ሳናውቅ አይምሽብን።

@forgiveeness @ahavaha