Get Mystery Box with random crypto!

ሰባ ጊዜ ሰባት 70*7

የቴሌግራም ቻናል አርማ forgiveeness — ሰባ ጊዜ ሰባት 70*7
የቴሌግራም ቻናል አርማ forgiveeness — ሰባ ጊዜ ሰባት 70*7
የሰርጥ አድራሻ: @forgiveeness
ምድቦች: መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 205
የሰርጥ መግለጫ

ጤና ይስጥልኝ!
ለእኛም ሆነ ለሀገራችን ፈውስ ይቅርታ ነው!
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ይህ የሁሉም ነገር መቋጫ እና መደምደሚያ ስለሆነው ይቆርታ የምንነጋገርበት፣ የምንወያይበት እና ይቅርታን ምርጫችን የምናደርግበት የእኛው ቻናል ነው!
ስለመጣችሁልን እናመሰግናለን!
ይህንን መልዕክት ለአንድ ወዳጅዎ ያጋሩ!
@forgiveeness @ahavaha

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-02-08 08:05:51 The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 8 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-29 08:22:55 The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 18 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-12-19 08:11:17 ይቅርታ!

ይቅርታ ማለት አንድ ፍሬ ያፈራ ዛፍን በድንጋይ በመታኸው ሰዓት በአፀፋው የሚጥልልህ ጣፋጭ ፍሬ ማለት ነው!

@forgiveeness @ahavaha
7.7K views05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-11-14 09:17:14 “ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ”

ታሪኩ ከተከሰተ ትንሽ ሰንበት ብሏል፡፡ ይህ ታሪክ የሆነው በስፔን ሃገር ነው፡፡ አባትና ልጅ ችላ ቢሉት ቀለል ሊል የሚችልን አንድን የግጭት ሁኔታ በማካበዳቸው ምክንያት ተጣልተዋል፡፡ በጉዳዩ ተጎድቻለሁ ባይ አባት በልጁ ላይ ስለጨከነበትና ይቅር አልለው በማለቱ ምክንያት ልጅ ቤቱን ጥሎ በመሄድ ይጠፋል፡፡ በጊዜው ከነበረበት ንዴት የተነሳ አባት ምንም አልመሰለውም፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ግን ጉዳዩ እያሳሰበው ስለመጣ የልጁን ደህንነት ለማወቅ መፈለግ ጀመረ፡፡ በተለያዩ መንገዶች ሲያጣራ ከቆየ በኋላ ከብዙ ወራት ሙከራ በኋላ በዚያው ከተማ ውስጥ እንደሚኖር አወቀ፤ በትክክል የት እንዳለ ግን ማወቅ አልቻለም፡፡ ልጁ በሕይወት መኖሩንና እጅግም ያልራቀ መሆኑን ሲያውቅ የተከሰተውን ችግር ሁሉ በመርሳት ይቅርታን ሊሰጠው ፈለገ፡፡ ይህንንም ለማድረግ ልጁን ማግኘት ስላልቻለ አንድን የመጨረሻ ሙከራ ለማድረግ ቆረጠ፡፡

በማድሪድ (ስፔን) ከተማ በሚታተመው ብዙ በመነበብ የታወቀ ጋዜጣ ላይ እንዲህ የሚልን መልእክት አወጣ፣ “ልጄ ፓኮ፣ ያለፈውን ስህተተህን ሁሉ ይቅር ስላልኩህ እባክህን ቅዳሜ ከቀኑ በስድስት ሰዓት በዚህ ጋዜጣ ማተሚያ ዋና ቢሮ በር ላይ ላግኝህ፡፡ የሚወድህ አባትህ፡፡” በተባለው ቀን ይህ አባት ልጁን ለማግኘት በተቀጣጠሩበት ቦታ ሲሄድ አንድን አስገራሚ ነገር ተመለከተ፡፡ ስማቸው ፓኮ የሆነና ከአባታቸው ይቅርታን የሚፈልጉ 800 ወጣቶች መልእክቱ የተላከው ከእነሱ አባት ስለመሰላቸው በዚያ ቢሮ በር ላይ ተሰብስበዋል፡፡ በተከሰተው ነገር እጅግ የተገረመው አባት ከዚያ ሁሉ ወጣት መካከል ልጁን ፈልጎ አግኘቶ ከሳመው በኋላ፣ “ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” አለውና ይዞት ወደቤቱ ወሰደው፡፡

ማሕበራዊ ኑሮ እስካለ ድረስ አለመግባባት የተሰኘው የሕይወት ሂደት የማይቀር ነው፡፡ ይህንን ምስጢር የዘነጉ ሰዎች ትኩረታቸውን ሁሉ በዚያ አለመግባባት ላይ ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ ትኩታቸውን የሚጥሉበት ነገር የወደፊታቸው ላይ ታላቅ ተጽእኖ እንዳለው የገባቸው ሰዎች ያለፈውን በመተው ወደፊት በመዝለቃቸው ላይ ሲያተኩሩ፣ ሌሎች ግን በአለመግባባትና በጸብ “መንፈስ” ውስጥ የመቆየት ዝንባሌ አላቸው፡፡ ትኩረታቸውን በይቅርታና ከተከሰተው ችግር ባሻገር በመሄድ ላይ ማድረግን ትተው ነገርን በመጎተትና በማካበድ ላይ የሚያደርጉ ሰዎች ወደ ተሻለ ሕይወት ለመዝለቅ የሚያበቃ አመለካከት እንደጎደላቸው አመልካች ነው፡፡

ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ዝንብንና ንብን፡፡ ዝንብ ቆሻሻው፣ መጥፎ ሽታ ያለውና የሞተው ነገር ሲስባት፣ ንብ ደግሞ ንጹህ፣ መልካም ጠረን ያለውና ሕይወት ያለው ነገር ይስባታል፡፡ ዝንብ ቆሻሻን፣ በሽታንና ሞትን ስታዛምት፣ ንብ ስትሰራ ውላ ጣፋጭ ነገርን በማምረት የብዙዎችን ሕይወት ታጣፍጣለች፡፡

አሁንም ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ንስርንና ጥንብ አንሳን፡፡ ንስር ሕይወት ያለውን ነገር ተናጥቆ ሲመገብ፣ ጥንብ አንሳ የከረመን፣ የሞተንና የበሰበሰን ነገር ሲያነሳ ይኖራል፡፡ ምርጫው የእኔ ነው፡፡ ያለፈውንና የሞተውን ነገር መከታተልና ያንን “እየተመገቡ” መኖር፣ ወይስ ያንን ትቶ የወደፊቱን፣ ትኩሱንና በይቅርታ የታደሰውን?

መዘንጋት የሌለብህ እውነታዎች …

• ተበደልኩ በማለት ወደኋላ በመመለስ ወደምታስታውሰው የጊዜ ርቀት የመመለስና ኋላ ቀር የመሆን እድልህ የሰፋ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የዛሬ 10 ዓመት የሆነብህን አሁንም የምትቆጥር ከሆነ በአመለካከትህም ሆነ በኑሮ እድገትህ 10 ዓመታት ወደኋላ ተጎትተህ በመመለስ እንዳዘገምክ አትዘንጋ፡፡

• ይቅር ያላልከው ሰው በአንተ ላይ የበላይነት አለው፡፡ አንተ የሆነብህን ስታብሰለስል ምናልባት እርሱ የግሉን፣ የቤተሰቡንና የሕብረተሰቡን ሕይወት እንዴት እንደሚሳድግ እቅድ እያወጣ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡

• አንተ ይቅር ያላልከው ሰው ምን እንዳደረገብህ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ ስታስተላልፍ፣ ምናልባት እርሱ አዳዲስ እውቀቶችንና ስልጣኔዎችን በማስተላለፍ አልፎህ ሄዶ ይሆናል፡፡

እኔ ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ፣ አንተስ? አንቺስ?

ዶ/ር ኢዮብ ማሞ

@forgiveneess @ahavaha
2.0K views06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-11-12 17:42:46
አለማወቅህን አትወቅ!

የሃመር ብሄረሰብ አባቶች ሲረግሙ “አለማወቅህን አትወቅ” ይላሉ። ለገባው ከባድ እርግማን ነው።

መቼም አለማወቅን ማወቅ ትልቅ ጸጋ ነው። ያላወቀ ሰው ይሰማል። ያላወቀ ሰው ይማራል።

ነገር የሚበላሸው አውቃለሁ ብለን የተቀመጥን ቀን ነው። አገር የሚጠፋው ‘አውቅልችዋለው’ ብለን ማሰብ ስንጀምር ነው።

ኢትዮጵያን ለመታደግ ስለራሳችን ምን መለወጥ አለብን ብለን ለጠየቅነው ጥያቄ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሀሳቦችን ተቀብለናል። ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

ብዙ ሰዎች የሚስማሙበት ዋንኛ ነጥብ “በጥሞና የመደማመጥ ባህል” ማነስ ነው። በጥሞና የመደማመጥ ባህል ለማዳበር እንዴት እንጀምር?

አለማወቃችንን ሳናውቅ አይምሽብን።

@forgiveeness @ahavaha
1.6K views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-11-11 17:30:16 ይቅርታ - ለትውልድ ውለታ!

እኛ ገንዘብ የካዱንን ይቅር ማለት ሲያቅተን አዳም ገነትንና እግዚአብሔርን ያሳጣችውን ሔዋንን ይቅር አላት።

ዮሴፍ ልጅነቱን ለመከራ እቶን የዳረጉትን ወንድሞቹን በበቀል ሳይሆን በይቅርታ አሸነፋቸው።

የእስጢፋኖስ ቤተሰቦች ደም መላሽ ቢሆኑ ኖሮ ጳውሎስን በመልዕክቱ ዛሬ አናገኘውም ነበር።

ይቅርታ ለትውልድ የምናቆየው ውለታ ነው። በእርግጥም ይቅርታ የማይገባንን በሰጠን በእግዚአብሔር ፊት ሰውዬው የማይገባውን መስጠት ነው።

ዲ/ን አሸናፊ መኮንን

@forgiveeness @ahavaha
4.2K views14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-11-11 16:46:12
ትገርማለህ

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንደሚታይ ትንታግ አድርጎሃል። እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን ነውም።

ግማሽ ልጩ ግማሽ ጎፈሬ በሆነች ሀገር ላይ መላጣው ጥለውህ (ቆመህ) ጎፈሬውን ጨብጠህ የቆምክ ይመስለኛል። ጥሬ በሞላበት በስለህ የተገኘህ፣ ያም ጥሬ ይህም ጥሬ፤ አለ እያቃጠለህ።

አብዩ መሪዬ መጥኔውን ይስጥህ፣
እግዚአብሔር በቅኝህ ሆኖ ይጠብቅህ!

@forgiveeness @ahavaha
5.3K viewsedited  13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-11-06 14:51:43 እስቲ እንወያይ!

የይቅርታ ልብ ምንድነው?

(ብዙዎች የይቅርታ ልብ አለህ/ሽ ይላሉ! የይቅርታ ልብ ምንድነው?)

(ይቅርታ ለመጠየቅ ሆነ ይቅርታ ለማድረግ የይቅርታ ልብ ያስፈልገን ይሆን?)

( የይቅርታ ልብ የት ነው የሚሰጠው? )


ሀሳባችሁን በዚህ ቻናል ሰብሰብ አድርጌ መልሼ አቀርበዋለው!
(ስማችሁን ከአስተያየት ጋር በዚህ @ahavaha ሊንክ ላኩልን!)
እስቲ እንወያይ!

@forgiveeness @ahavaha
1.3K viewsedited  11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-11-06 14:24:00 ሀገራችንን ለማሻገር!

የሀገራችንን ታላቅነት ለማየት የእኛንም ታላቅነት ለመጨበጥ ተሻግረን እንድናሻግራት የመሻገሪያ ድልድዩ ይቅርታ ይባላል!

ይቅርታ ለሁሉም ነገር የመሻገሪያ ድልድይ ነው!

@forgiveeness @ahavaha
12.3K views11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-11-05 09:21:44 ሲበድሉ ማሩኝታ!

በአንድ ወቅት በዚህ በከተማችን አዲስ አበባ በአንድ ደብር ሁለት ባላጋራ ቀሳውስት ወደ ቅዳሴ ይገባሉ፡፡

በመሰረቱ ባላጋራ ሆኖ መቀደስ ክልክል ነው፡፡ ገባሬ ሰናዩ ቄስ አሀዱ ሲል ለካ ጽዋውን አልገለጠውም ነበር፡፡ አሀዱ ወልድ ጋር ሲደርስ ባለጋራው ንፉቅ ቄስ ያየውና ‹‹ አንተ እንከፍ ጽዋውን ከድነህ ነው አሀዱ የምትለው›› ይለዋል፡፡ ቄሱም ጸሎቱን አቋርጦ ‹‹ ምቀኛ ምን አገባህ›› ብሎ ‹‹አሀዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› በማለት ጨረሰው፡፡

መቼም ድምጽ ማውጊያው ሲገዛ አሜን አሜን የሚያሰኝ ነገር ተገጥሞበታል መሰል ቢሳደቡም ህዝቡ አሜን ብሎ ይሄዳል፡፡ የተማረው ግን ‹‹ሞኝ ባያፍር ዘመዱ ያፍራል›› ሆኖበት ያዝናል፡፡ ለዚህ ቄስ ባላጋራ ሆነው መቀደሳቸው አልተስማማውም፡፡ የጽዋው መከደን ግን ተሰማው፡፡

ጠላት ትልቁን እያስጣለ በትንሹ ጠንቃቃ ያደርገናል፡፡ በፍቅር ብንቆም የተከደነውን ጽዋ እግዚአብሔር መባረክ ያቅተዋል?

ጌታችን ‹‹የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፣ ይህንንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ… ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እጅግ ንቃችኋል›› (ማር. 7፣8-9) ያለው ተፈጽሞብናል፡፡

ዲ/ን አሸናፊ መኮንን

@forgiveeness @ahavaha
4.9K viewsedited  06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ