Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ ሼፍ ዘሩ ነኝ ዛሬ በብና ሰአት ላይ ልታቀርብት የትችሉት ነገር እናያለን | ሼፍ ዘሩ

ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ ሼፍ ዘሩ ነኝ ዛሬ በብና ሰአት ላይ ልታቀርብት የትችሉት ነገር እናያለን።
ከብና ጋር የሚቀርብ ኬክ
4 ½ ኩባያ ዱቄት
• 4 እንቁላል
• ሶስት ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
• 1 ኩባያ ኮኮናት ዱቄት
• ¾ ኩባያ ስኳር
• ½ የሻይ ማንኪያ ጨው
• 2/3 ኩባያ ውኋ
• ¼ ኩባያ የተሰባበር ለውዝ
• ¾ ኩባያ ቅቤ
• 1 ኩባያ የተሰባበረ ቸኮሌት
• 1 ኩባያ ወተት

አሰራር

1. በትልቅ የጎርጓዳ ሰሃን ውስጥ ስኳር፣ውኋ፣ቅቤ፣ወተት፣ቅንቁላልና ጨዉን አድርገው በደንብ ይምቱት

2. ዱቄት፣ኮኮናትና ቤኪንግ ፓውደሩን በሌላ ሰሃን ውስጥ ይደባልቁት

3. በሁለቱ ሰሃን ውስጥ ያሉትን ይቀላቅሉና በትልቅ ማንኪያ በደንብ ይምቱት ( ይቀላቅሉት)

4. መጋገሪያ ሰሃኑን ዘይት ይቀቡት ፣ሊጡን ሰሃኑ ላይ ይገልብጡት፣ ከላዩ ላይ የተሰባበረውን ሎውዝ እና ቸኮሌት ከላይ በስሱ ይነስንሱ

5. በቅድሚያ በሞቀ የዳቦ መጋገሪያ ውስጥ ለ 50 ደቂቃ (ወርቃማ ከለር እስኪኖረው ድረስ) ያብስሉት

6. ሲቀዘቅዝ ቆራርጠው ከሻሂና ቡና ጋር ያቅርቡት።