Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ ሼፍ ዘሩ ነኝ ቀለል ያለ ጁስ እናያለን። እርጎ እስትሮበ | ሼፍ ዘሩ

ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ ሼፍ ዘሩ ነኝ
ቀለል ያለ ጁስ እናያለን።
እርጎ እስትሮበሪ ጁስ
¾ ኩባያ ስኳር
• 6 ትልቅ እንቁላል ነጩ ክፍል
• 120 ግራም እርጎ
• 2 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ
• 1 ½ ኩባያ ክሬም
• 4 ኩባያ እስትሮበሪና እንጆሪ
• 8 ፍሬ ብስኩት

አሰራር

1. በሰፊ ድስት ውስጥ ውኋ ጨምሮ ማፍላት

2. ስኳሩንና እንቁላሉን ከሩብ ኩባያ ውኋ ጋር መካከላኛ ሰሃን ውስጥ ጨምሮ በሚንተከተከው ውኋ ላይ ሰሃኑን በመንከር ሳያቋርጡ ማማሰል

3. ለ8 ደቂቃ ያብስሉት (እያማሰሉ)

4. ከሞቀው ውሃ ላይ ያውርዱት ፣እርጎውና ቫኒላውን ይጭምሩና ለ 5 ደቂቃ ያማስሉት

5. ያዘጋጁት እርጎ ላይ 1 ½ ኩባያ ክሬሙን ያደባልቁት፣ ፍሪጅ ውስጥ ለ 3 ሰአት ያቀዝቅዙት

6. ከፍሪጅ ያውጡትና በብርጭቆዎች ላይ ይገልብጡት ፣እስትሮበሪና እንጆሪውን ከላይ ጨምረው ከማንኪያ ጋር ያቅርቡት።