Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ሰላም ሼፍ ዘሩ ነኝ ጠዋት ተነስቼ ምን ቁርስ ልስራ ብለዉ አያስቡ ቀለል ያለ ቁርስ እናያለን | ሼፍ ዘሩ

ሰላም ሰላም ሼፍ ዘሩ ነኝ ጠዋት ተነስቼ ምን ቁርስ ልስራ ብለዉ አያስቡ ቀለል ያለ ቁርስ እናያለን።
የእንቁላል አነባበሮ
'3 ዕንቁላል
• 1 ቀይ ሽንኩርት በደቃቁ የተከተፈ
• 1 ተለቅ ያለ ቲማቲም በደቃቁ የተከተፈ
• 2 ቃሪያ ሽንኩርት በደቃቁ የተከተፈ
• ዘይት ለመጥበሻ ያህል ጨው እንደ አስፈላጊነቱ

አሰራር

1. ዕንቁላሉን መተን መጥበሻ ላይ በትናንሹ እንደ እንጎቻ መጋገር

2. የተከተፈውን ሽንኩርት ቃሪያ እና ቲማቲም በአንደኛው እንጎቻ ላይ እንነሰንሳለን

3. በሌላው የዕንቁላል እንጎቻ ሸፍነን ካበሠልነው በሇላ በትኩሡ ማቅረብ።