Get Mystery Box with random crypto!

#ትምህርተ_ሃይማኖት_ርትዕት ክፍል 2 #ሥነ_ፍጥረት #ሥነ ፍጥረት ማለት ያማረ የተዋበ ፍጥረት | ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

#ትምህርተ_ሃይማኖት_ርትዕት

ክፍል 2

#ሥነ_ፍጥረት

#ሥነ ፍጥረት ማለት ያማረ የተዋበ ፍጥረት ማለት ነው ። "እግዚአብሔርም የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደሆነ አየ " እንዲል ዘፍ 1:31#አንድም ሥነፍጥረት ማለት የተስማማ ስምሙ ፍጥረት ማለት ነው ። የማይስማሙ ውሃን ከእሳት ፣ ነፋስን ከአፈር አስማምቶ ፈጥሮዋል #ስምሙ_ፍጥረት ይባላል።እግዚአብሔር ፍጥረት የፈጠረበትን ሥርዓት የምንማርበት ትምህርት ሥነ ፍጥረት ይባላል ። እግዚአብሔር በ6 ቀን 22 ፍጥረታትን ፈጠረ ። ዘፀ 20:8 ሃያ ሁለት የተባሉትም በዓይነታቸው ተመድበው ነው ። አፈጣጠራቸው #በ3 ወገን ነው ። #1ኛ. በሃልዮ / በማሰብ / -7ፍጥረታት #2ኛ.በመናገር /በነቢብ/ -14ፍጥረታት #3ኛ.በመስራት /በገቢር/ -1 ፍጥረት ሰውን ፈጠረ

#የእለተ_እሑድ_ፍጥረታት

እሑድ ማለት አሐደ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መጀመሪያ አንደኛ ማለት ነው ። እግዚአብሔር በመጀመሪያ የፍጥረት ቀን እሑድ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ 7 አንድም 8 ፍጥረታትን ፈጠረ ። እነሱም #ነፋስ_እሳት_መሬት_ውሃ_ጨለማ_ብርሃን_ሰማያትና_መላዕክት ናቸው ። 8ፍጥረት መባሉ ስለምንድነው ቢሉ 7 የሚሉ ሊቃውንት ጨለማና ብርሃንን አንድ አርገው ቆጥረው ሲሆን 8 የሚሉት ደግሞ ለየብቻ ቆጥረው ነው

#የሰኞ_ፍጥረት

በውሆች መካከል ጠፈር ይሁን ብሎ ተናግሮ ከበላያችን የምናየውን ሰማይ ፈጠረና ውሆችን ወደ ላይና ወደታች ከፈለ ፡ ጠፈርንም ሰማይ ብሎ ሰየመው ። ሰማዩም ሙሉ ነጭ አይደለም በውሀና በመሬት ከነበረው ጨለማ ቀባ አድርጎ ፈጥሮታልና ። ሙሉ ነጭ ቢሆን እንደ ፀሐይ ዓይናችንን እየወጋ ለማየት እንዳይከለክለን ነው ። ዝርግነቱም እንደ ወለል ቀጥ ያለ ሳይሆን እንደ ጋሻ ጎበብ ያለ ነው ። ስለምን እንዲህ አደረገው ቢሉ ከጠፈር(ከሰማይ) በታች ያሉ ብርሃናት ብርሃናቸውን የሚነዙ ወደ ላይ ነውና ወደታች ወደምድር እንዲመልሰው ብሎ ነው

#የእለተ_ማግሰኞ_ፍጥረታት

በቃሉ በማዘዝ 3 ፍጥረታትን ፈጠረ ። እግዚአብሔር ቡቃዮችን ፍጥረታትን ሲፈጥር በአበባ በፍሬ ማለትም አበባ ፍሬ እንደያዙ ነው የፈጠራቸው እንጂ በቡቃያነት አይደለም ። ተፈጥሯቸው ከ4ቱ ባህርያተ ስጋ ከመሬት ፣ ከነፋስ ፣ ከእሳት እና ከውሃ ነው ። በባህርያቸው 3 ተግባር አላቸው

#1.ምግብ መውሰድ #2.መርዘም #3.መስፋትና መወፈር እነዚህን መምህራን በ3 መደብ ይመደቡአቸዋል

#1.የሣርና የእህል ዘር አይነት #2.የአትክልት አይነት #3.ሌሎች ዛፍና እንጨት አይነት። በፍሬ አሰጣጣቸው #1.በስራቸው የሚያፈሩ #2.በጎናቸው የሚያፈሩ #3.በአጽቃቸው የሚያፈሩ ተብለው ይመደባሉ ። በፍሬ አሰባሰባቸው ደሞ #1.በጣት የሚለቀሙ #2.በማጭድ የሚታጨዱ #3.በምሳር ሚቆረጡ /በቁፋሮ የሚወጡ/ ተብለው ይመደባሉ ። የማክሰኞ ስነፍጥረት የድንግል ማርያም ምሳሌ ናቸው ይኸውም የመጀመሪያዋ ምድር ያለዘር እፅዋትን እንዳስገኘች ድንግልም ያለ ወንድ ዘር ክርስቶስን አስገኝታለች

Comment @finotebrhan

@finotebrhan
@finotebrhan
@finotebrhan