Get Mystery Box with random crypto!

#ክርስቲያናዊ_ስነ_ምግባር ክፍል 3 #የእግዚአብሔር_የአምላክህን_ስም #በከንቱ_አትጥራ ስም ሲ | ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

#ክርስቲያናዊ_ስነ_ምግባር

ክፍል 3

#የእግዚአብሔር_የአምላክህን_ስም
#በከንቱ_አትጥራ

ስም ሲባል አንድ ነገር ከሌላው ተለይቶ የሚታወቅበት መጠሪያ ነው ። ስም ጠባይን ግብርንና ሁኔታን እንደሚገልጥ ሆኖ ሊሰየም ይችላል ። እግዚአብሔርም ባሕርዩን ሕልውናውን ግብሩን የገለፁ ብዙ ስም አለው ። በሐዲስ ኪዳንም እግዚአብሔር ወልድ በስጋ ሲገለጥ #አማኑኤል #ኢየሱስ #ክርስቶስ በሚባሉ ስሞች ተጠርቷል። የእግዚአብሔር ስም ባዶ ቃል አይደለም። ኃይሉን ግርማውን ይዞ ይገኛል ። የማይታየው እግዚአብሔር ራሱን የገለጠው በስሙ አማካኝነት ነው

በተለይም ክርስቶስ በስጋ በተገለጠ ጊዜ ስሙን ለዓለም አስታውቋል ።/ ዮሐ 17:26/ ስሙም ከሁሉ በላይ ነው ። /ፊል 2:9/ ስሙ #ቅዱስ ነውና አክብረን ልንይዘውና ልንቀድሰው ይገባል እንጂ በከንቱ ልንጠራው አይገባም ። መላዕክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሚያመሰግኑት አምላክ መሆኑን አውቀን ስሙን በከንቱ መጥራት ግብሩን ማርከስ ነው

በማህበር ስንኖር ከሳሽ ተከሳሽ ስለሚኖር የክርክሩ መፈፀሚያ የእውነት ማረጋገጫ መሐላ ስለሆነ ዳኛው እንዲምል ካስገደደው መማል ይፈቀዳል ። /ዘፀ22:11 ዕብ6:13/ ከዚህ ሌላ ቃል ለመግባት አንድ ነገርን ለመስራት መሐላ መማል ቃል መስጠት የእግዚአብሔር ስም መጥራት የሚያስፈልግባቸው ጊዜ አለ ። እንዲሁም እግዚአብሔርን ለማገልገል ሲሉ ብፅዓት የሚያደርግ አለ ይኸውም በቤተክርስቲያን ስርዓት የተፈቀደ ነው። ለምሳሌ በድንግልና ለመኖር

#በከንቱ_አትጥራ
ከንቱ ማለት በእግዚአብሔር የተናቀ የማይገባ ነገር ማለት ነው ። የእግዚአብሔርን ስም በእንዲህ አይነት ሁኔታ መጥራት እንደማይገባ ይህ ትዕዛዝ ያስተምረናል እነሱም ፦

1.ስጋዊ ፍቃድ 2.ጣኦትን ማምለክ 3.ሐሰተኛ ትንቢት 4.በእግዚአብሔር ስም መማል 5.በእግዚአብሔር ስም መራገም 6.በእግዚአብሔር ስም መጠንቆል ... በነዚህ ሁሉ ስሙን መጥራት በከንቱ መጥራት ነውና በማስተዋል ልንጠብቀው ይገባል

#የእግዚአብሔርን_ስም_የምንጠቀመው_ምን_ጊዜ_ነው ?
1.በፀሎት ጊዜ 2.በሰላምታ ጊዜ 3.በአምልኮ ጊዜ 4.በቡራኬ ጊዜ

...ይቀጥላል ...

Comment @finotebrhan

@finotebrhan
@finotebrhan
@finotebrhan