Get Mystery Box with random crypto!

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

የቴሌግራም ቻናል አርማ finotehiwott — Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ። F
የቴሌግራም ቻናል አርማ finotehiwott — Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።
የሰርጥ አድራሻ: @finotehiwott
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.92K
የሰርጥ መግለጫ

በፌስቡክ ያግኙን፤ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
በድኅረ ገጽ ያግኙን፤
http://www.finotehiwotsundayschool.com

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-02-18 14:59:18 ሰበር መረጃ
ዛሬ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም እነ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ ስምምነቱን ሳይሸራረፍ እንደሚቀበሉና ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በቅዱስ ሲኖዶስ በመገኘት ቃላቸውን ሰጥተው አረጋግጠዋል።
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
እነ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አሕመድ በተገኙበት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ/ም በተደረገው ውይይት የተስማማንባቸውን (10) ዐሥር ነጥቦች ያለመሸራረፍ ለመፈጸም እንዲሁም ቀጣዩን ተግባር በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት ለማከናወን ተስማምተናል ሲሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት በመገኘት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

EOTC TV
2.0K views11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 14:58:56
1.9K views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 11:38:43 የዐቢይ ፆም የመዠመሪያው ሳምንት

#ዘወረደ_ወይም_ሕርቃል_ወይም_ሙሴኒ

አንዲት ቤተክርስቲያን ፥ አንድ ሲኖዶስ ፥ አንድ መንበር ።

 ጾም ማለት ፤
፨ ከእህልና ከውኃ እንዲሁም ከሥጋ ፈቃድ ጾሙ እስኪፈጸም ድረስ መተው ማለት ነው።
፨ ጾም ማለት በጾም ወቅት ሥጋ ነክ ምግቦችንም ሆነ ወተትን፤ ቅቤን የመሳሰሉትን የምግብ እና የመጠጥ ዓይነቶችን ጥሉላትነት በሌላቸው ምግቦች መለወጥ ብቻ ሳይሆን የምንወደውን የሥጋ ፍላጎት ስለ እግዚአብሔር ብለን መተው ማለት ነው። ራስን መግዛት በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ሁሉ አንድ ሰው የሥጋ ፍላጎቱን ወይም የዓለም ምኞቱን ትቶ እግዚአብሔርን እያሰበ የሚጾም ከሆነ በፈጣሪው ዘንድ ጾሙ ተቀባይነት አለው።

፨ ጾም ለእግዚአብሔር ያለንን ታዛዥነት የምንገልጽበት የፍቅር መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ዐቢይ ጾም ስንጾምም፤
፠ ዐይናችን ትጹም (ክፉ ከማየት)፤
፠ ጆሮም ትጹም (ክፉ ከመስማት ወይም ሰውን ከማማት እንታቀብ)፤
፠ አፋችን ትጹም (ከመሳደብ ሆነ ክፉ ከማውራት)፤
፠ እጅም ትጹም (ከመስረቅም ሆነ ሰውን ከመደብደብ)፤
፠ አግርም ትጹም (ወደ ኀጢአት ቦታዎች ከመሄድ)

….. ሁላችንም በተሰበረ ልብ ሆነን እንጹም።

#ዐቢይ_ጾም ማለት ታላቅ ጾም ማለት ነው። ታላቅ ጾም የተሰኘበት ምክንያት ለ55 ቀናት መጾሙና ከሌሎች አጽዋማት ጋር ሲነጻጸር በቊጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ፍጥረታትን የፈጠረ አምላክ፤ ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ሲል ከዙፋኑ ወርዶ ከእመቤታችን ተወልዶ፤ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርአያ ለመሆን ሲል በገዳመ ቆሮንጦስ የጾመው ጾም ነው።

የዐቢይ ጾም  የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ወይም ጾመ ሕርቃል በተጨማሪም ሙሴኒ በመባል ይታወቃል፤ ለምን እንደተባለ በዝርዝር ስንመከለከታቸው፤

፩ኛ. ዘወረደ ይባላል፤

‹‹#ሃሌ_ሃሌ_ሉያ_ዘወረደ_እምላዕሉ_አይሁድ_ሰቀሉ፤
#ወሚመ_ኢያእመሩ፤
#እግዚአ_ኵሉ_ዘየሐዩ_በቃሉ፡፡››
‹‹ #ዘወረደ_እምላዕሉ_እመልዕልተ_ኵሉ››፡፡
«ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምሥጢሩ አምላክ፥ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም፥ እኛን  ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን፤ በፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና መውረዱን፥ ከድንግል ማርያም መወለዱን፥ የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ይህ እንዲታወስበት፣ እንዲወሳበት የዐቢይ ጾም የመጀመሪያውን ሳምንትን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ ‹‹ዘወረደ›› ብሎ ሰይሞታል፡፡ /ዮሐ.3፥13፣ ጾመ ድጓ፡፡/

   ፪ኛ. ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡

የዐቢይ ጾም የመዠመሪያ ሳምንት ሌላ መጠሪያ ስሙ ‹‹ጾመ ሕርቃል›› ነው፡፡ ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ? በ614 ዓ.ም. ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ንግሥቲቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ካህናትን አሸክሞ፥ ሌላውን ንዋያተ ቅድሳት ዘርፎ፥ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ፥ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ፥ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፤ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርግ? አላቸው፤ እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን ፩ ሱባኤ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉ ያለበትን አጥቶ ሲቸገር ኪርዮስ መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሰ፤ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ፤ ይህንን ለማሰብ፥ ለማስታወስ የምንጾመው ሲሆን፤ ዛሬም እኛ በመስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን እያልን፥ ለሕርቃል በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳትን፥ መንፈሳዊ ኃይልን እንዲበዛልን እንጾመዋለን፡፡ በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡

  ፫ኛ. ሙሴኒ
የመጀመሪያው ሳምንት ሙሴኒ የተባለበት ምክንያትም፤ በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት (ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ») ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ካለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው አምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን  የሚያስታውስ ነው፡፡  /ዘፀ.24፥18፤  1ኛ.ነገ.19፥8፤  ማቴ.4፥1-4/፡፡

ይህ ታላቅ ጾም ሌሎች ስያሜዎችም አሉት ፡፡

አንዲት ቤተክርስቲያን ፥ አንድ ሲኖዶስ ፥ አንድ መንበር ።

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ ::/
   #share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/finotehiwott
http://tiktok.com/@finotehiwot
     www.finotehiwotsundayschool.com 

ዓዲ ፣

የዘወረደ_ምስባክ

* መዝ. 2፡11

ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ።
አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐዕ እግዚአብሔር።


የዘወረደ ምንባብ 1 (ዕብ.13÷7-17)
የዘወረደ ምንባብ 2 (ያዕ.4÷6-ፍጻ.)
የዘወረደ ምንባብ 3 (ሐዋ.25÷13-ፍጻ.)

ቅዳሴ ፡ ዘእግዚእነ
2.2K viewsedited  08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 11:38:27
1.9K views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 08:19:06 ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ እሥረኞች መፈታታቸውን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ገለጹ!!!

የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በሸገር ሲቲ በ ፉሪ ክፍለ ከተማ 04 ፖሊስ ጣብያ ታስረው ከነበሩ እሥረኞች መካከል ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ እሥረኞች መፈታታቸውን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ(ዶ/ር) ገለጸዋል።

ብፁዕነታቸው በፓሊስ ጣቢያው የሚገኙ ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በእስር ቤቱ በመገኘት ከጠየቁና ከአጽናኑ በኋላ ከሚመለከታቸው የፖሊስ ጣቢያው ኋላፊዎችና ዐቃቤ ሕግ ጋር ውይይት አድርገዋል ።

ከውይይቱ በኋላም ከአንድ መቶ በላይ እሥረኞች ተፈተዋል ሲሉ ብፁዕነታቸው ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው በጉብኝታቸው ወቅት በዐቃቤ ሕጉና በፓሊስ ኃላፊዎች ለተደረገላቸው መስተንግዶና አቀባበል የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ምስጋናቸውን በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም አቅርበዋል።

የቀሩትና በፓሊስ ጣቢያው ውስጥ የሚገኙ እሥረኞችም በአጭር ቀናት ውስጥ እንደሚፈቱ ከዐቃቤ ሕጉና ከፓሊስ ኃላፊዎቹ ማረጋገጫ እንደተሰጣቸው ብፁዕነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ምንጭ:- የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት
1.9K views05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 08:18:57
1.6K views05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 08:18:14 [ብፁዕ አቡነ አብርሃም በዛሬው ዕለት ከተናገሩት የተወሰደ]

"ከሁለት ቀናት በፊት ሰላም መፈጠሩን ማወጃችን ይታወሳል። በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የምንሰማቸው ነገሮች ሁሉ እንደገና ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍል አባቶችን ከልጆች ልጆችን ከአባቶች የሚያሻክሩ ነገሮችን እየሰማን ነው

"ወደ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ አዲሱ ሲኖዶስ በሚል አዲስ ስም እስካሁን ከሚጠቀሙበትም ለየት ባለ ስም የተሰጠ መግለጫ በሚል በሰጡት ባስተላለፉት ሁሉም በአንድነት ጵጵስናው የሚመለከታቸውም የማይመለከታቸውም የኤጲስ ቆጶስነቱ ደረጃም በስምምነቱም በጋራ የጠፋ ወይም የተሻረ የተደመሰሰ መሆኑን እያወቁም የቅድስናውን ልብስ በመልበስና ሌሎችም የስምምነቱ አካል ሆነው ስምምነቱን ያነበቡት ሳይቀሩ በአንድ ላይ ስምምነቱን ጥሰውታል ቀኖናውን እንደገና ደግመው ጥሰውታል። ሀይማኖቱንም ሕጉንም መልሰው መላልሰው ጥሰውታል።ሹመታቸው ሕጋዊ እንደሆነና በምንም ይሁን በምን የማይሻር መሆኑንም መልእክት አስተላልፈዋል። ይህ ከዕለት ወደ ዕለት የሚታይ የሚሰማ ከንቱ ክስ ሆኗል። ከሃይማኖታዊ ይልቅ ፖለቲካዊ ይዘትን ተጎናጽፏል። በሃይማኖታዊ መንገድ በሰላምና በፍቅር በክርስቶስ ደም የተመሠረተችውን ቤተ ክርስቲያን ከመጠበቅ በክርስቶስ ደም የተዋጁትን ምእመናን ከማስተማር ይልቅ በኃይልና በጉልበት ሁሉንም በነገረ ሰሪነት ግጭት በመፍጠር ሁሉንም ለመቆጣጠር ከዕለት ወደ ዕለት ደፋ ቀና ሲሉ ይታያሉ"

"አስተሳሰባቸው አነጋገራቸው ሁሉ በእኩል ደረጃ እንደሆኑም ተናግረዋል። 25 የተባሉትም የትናንትና ካህናት አገልጋዮች አሁንም ኤጲስ ቆጶሳት እንደሆኑ ተደርጎ ተንጸባርቋል። ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይህንን አድርገው ቀኑን ሙሉ አንመጣም ሲሉ ዉለው 10 ሰዓት ላይ ግን ለማንም ለማን መጣን ሳይሉ ቤታቸው ውስጥ[ቤተ ክህነት] ገብተዋል። ... ቤተ ክርስቲያንም እስቲ ሁሉንም ነገር በትዕግሥት እንየው በማለት ዝም ብለን እየተመለከትን ነው። ስለዚህ ሕግን የጣሰ ሰው ስምምነትን ያፈረሰ ሰው ዛሬም ደግመው ደጋግመው እውነት ለማስመሰል ሐሰትን በሚለፍፉ ሰዎች እንዲህ ዓይነት ድፍረት የሚመለከተው አካል ሊመለከተውና አሁንም በቃ ሊለው ይገባል ብለን መልእክታችንን እናስተላልፋለን።"
1.8K views05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 08:18:10
1.7K views05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 15:51:43
2.2K views12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 15:50:56 የሊቀ ስዩማን ኃይለ ማርያም ሥርዓተ ቀብር የካቲት 4 ተፈጽሟል ፡፡

ሊቀ ስዩማን ኃይለ ማርያም

ሊቀ ስዩማን ኃይለ ማርያም ባሳዝነው ወንድማገኘው በ1957 ሚያዝያ 23 ቀን በሰሜን ሸዋ ጅሩ ከአባታቸው አቶ ባሳዘነው ወንድማገኘው እና ከእናታቸው ከ እማሆይ አስካለ ማርያም ተወለዱ ፡፡

እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስም በቤተሰቦቻቸው ወደ ዘመናዊ ትምህርት እንዲሄዱ ቢፈልጉም እርሳቸው ለመንፈሳዊው ትምህርት ካላቸው ጉጉት ወደ መንፈሳዊ ትምህርት ለመማር ወደ አቡነ ዜና ማርቆስ ገዳም በመግባት የንባብ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ወደ ታላቁ ገዳም ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመመሄድ ከየኔታ ወልደ ጊዮርጊስ የንባብ ትምህርታቸውን አጠናክረው ተምረዋል የንባብ ትምህርታቸውንም ካጠናቀቁ በኋላ በዜማ ጉባኤ ቤት ከየኔታ መኮንን (የኔታ መርዐዊ) ጸዋትዖ ዜማን በሚገባ ተምረው ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ቅዳሴ ቤት በመግባት ከታወቁት የቅዳሴ መምህር ከየኔታ ጥበብ የቅዳሴ ትምህርታቸውን በሚገባ ተምረዋል ፡፡

ሊቀ ስዩማን ኃይለ ማርያም ባሳዝነው በ1969 ዓም ግንቦት 14 ቀን ከብጹዕ አቡነ ዮሐንስ ዲቁና ጠቀብለዋል ፡፡

ሊቀ ስዩማን ኃይለ ማርያም በደብረ ሊባኖስ ገዳም የነበራቸውን የትምህርት ቆይታ በማጠናቀቅ በ1973 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ማረፊያቸውን በደብራችን ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤ/ክ በማረፍ በወቅቱ በነበሩት አስተዳደር እና የሰ/ጉባኤ በወጣው የዲቁና ቅጥር ከ 30 ተወዳዳሪዎች ጋር በመወዳደር በ ኹለተኛ በመውጣት በዲቁና ተቀጥረዋል ፡፡

ሊቀ ስዩማን ኃይለ ማርያም ባሳዝነው በዚሁ ደብር በአገልግሎት ላይ ሳሉ በ 1981 ዓ.ም በቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓት መሰረት ከ ጋብቻን በመመስረት ሦስት ልጆችን አፍርተዋል ፡፡

ሊቀ ስዩማን ኃይለ ማርያም ባሳዝነው በደብራችን ለ 23 ዓመታት በዲቁና እና በቅስና አገልግለዋል ከመንፈሰዊው አገልግሎት በኋላ ወደ ቢሮ ስራ በመሸጋገር እስከ አሁን ለ 18 አስራ ስምንት ዓመታት በደብሩ ዋና ቁጥጥርነት ቤተ ክርስቲያንን በታላቅ ትጋት እያገለገሉ ቆይተዋል ፡፡

የአባታችን ለሊቀ ስዩማን ኃይለማርያም ባሳዝነው ነፍስ ከደጋጎቹ አባቶች ከአብርሃም ከይሰሓቅ ጋር ይደምርልን ፡፡

በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ /
#share

.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
2.1K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ