Get Mystery Box with random crypto!

{ብሒለ አበው ወ ሕይወት መንፈሳዊ}

የቴሌግራም ቻናል አርማ finoteabew — {ብሒለ አበው ወ ሕይወት መንፈሳዊ}
የቴሌግራም ቻናል አርማ finoteabew — {ብሒለ አበው ወ ሕይወት መንፈሳዊ}
የሰርጥ አድራሻ: @finoteabew
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.16K
የሰርጥ መግለጫ

ይዘቱ
፩ ➛ብሒለ አበው(የአባቶችን ለሕይወትታችን መርህ የሚሆኑ ብሒሎች)፣
፪ ➛የቅዱሳን ምክር ተግሳጽ
፫ ➛ለመንፈሳዊ ሕይወት የሚጠቅሙ ትምህርቶች
፬ ➛ ወቅቱን የጠበቁ ትምህርቶች
አላማው
የአባቶቻችንን ፍኖት (መንገድ) ማወቅና መከተል
መንፈሳዊ ህይወት መኖር
ከቅዱሳን ታሪክ ተሞክሮ መውሰድ
።።።።።።።
ሀሳብ አስተያየት ካሎት ➙ 0994794784

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-19 21:25:23 ✞እንደ ፀሐይ✞

እንደ ፀሐይ ፊቱ ሲያበራ
ዓይናችን ካየ ታቦር ተራራ
በታቦር መሆን ለእኛ መልካም ነው
ስለጠገብን ክብሩን አይተነው

የአምላክ ልጅ አምላክ ንጉሥ ነው እርሱ
ሌላ አያስመኝም ፍቅሩን ሲቀምሱ
/ሁሌ ከእርሱ ጋር መሆን ደስ ይላል
እንዳለፈ ወንዝ ችግር ያስረሳል/(፪)
አዝ= = = = =
ገናናነቱ ክብሩ ተገልጦ
የግርማው ሙቀት ሰንሰለት ቆርጦ
/ከዓለም መንጋጋ እኛን ተናጥቋል
ሞትን ዘልፎልን ህያው አርጎናል/(፪)
አዝ= = = = =
ከቶ አይደለንም እኛማ የእኛ
በዋጋ ገዝቶን መልካሙ እረኛ
/ተከፍቶልናል የምህረት በሩ
ፍቅር የሳበው ስቦን በፍቅሩ/(፪)
አዝ= = = = =
የተሰሎንቄ አሸንክታቧ
እንዳይማርከን ያ ወጥመድ ልቧ
/ክብሩ ይውረሰን ሌላ አይግዛን
ልባችን ታቦር ይሁነው ዙፋን/(፪)

መዝሙር
አዜብ ከበደ

"...ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤..."

ማቴ ፲፯፥፩-፱
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮   
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
204 views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 21:19:00
https://t.me/Amde_Tewahedo_SS
163 views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 12:37:51 ደብረ ታቦር (ቡኄ)
ደብርየሚለው ቃል የግእዝ ቃል ሲሆን ተራራ ማለት ነው ፤ ታቦር ደግሞ የተራራው ስም ነው።የታቦር ተራራ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው።ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊሊጶስ ቄሳርያ ለደቀመዛሙርቱ "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" ብሎ ጠይቋቸው ነበር።እነርሱም "አንዳንዶች ከእናቱ ማህፀን ጀምሮ ቅዱስ ነውና ኤርሚያስ ነው ይሉሀል፤ አንዳንዶቹ ድንቅ የሆነ ልደትህንና የምታጠምቀውን አዲስ ጥምቀት አይተው መጥምቀ ዮሐንስ ነው ይሉሀል፤ ሌሎች ደግሞ ለአባቶችህ ቤት ያለህን ቅናት አይተው ኤልያስ ነው ይሉሀል" እያሉ መልሰውለት ነበር። ጌታችንም መልሶ፦ "እናንተስ ማን ትሉኛላችው?" ብሎ ጠየቃቸው። ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስም "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ነህ" ብሎ መልሷል። ጌታም "የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማይ ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይሄንን አልገለጠልህምና ብፁህ ነህ" ብሎታል።(ማቴ16)
ከዚህም በኃላ የሚደርስበትን መከራ ሁሉ ይነግራቸው ጀመር በዕለተ አርብ መገረፉን መሰቀሉን መሞቱን እንዲሁም ደግሞ በሶስተኛ ቀን ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሳ ሲነግራቸው ሰይጣን በቅዱስ ጴጥሮስ አንደበት አድሮ እንዳያደርገው እንዳይሆን ይከራከረው ነበር ። ጌታችንም ይገስጸዋል ወደ ምድር የመጣው የገባውን ቃል ሊፈጽም ነውና።(ማቴ 16)
ይህ በሆነ በሰባተኛው ቀን ዘጠኙን በእግረ ደብር ትቶ ሦስቱን ደቀመዛሙርቱን ማለትም ጴጥሮስ ፣ዮሐንስ እና ያዕቆብን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ወጣ።እንዲሁም ሙሴ ና ኤልያስንም አመጣቸው ። በዚያም ክብረ መንግስቱ፤ ብርሃነ መለኮቱን ገለጠላቸው።ጴጥሮስም ለጌታ አንተ ብትወድስ አንዱን ላንተ አንዱን ለሙሴ አንዱን ለኤልያስ ሶስት ጎጆ ሠርተን በዚሁ እንኑር አለው።ይህን ሲናገር ብሩህ ደመና መጥቶ ጋረዳቸው ። ወዲያውም "ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ወሎቱ ስምዕዎ'' በእሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እሱን ስሙት"የሚል ድምጽ ከሰማይ ተሰምቷል።እነ ጴጥሮስ ደንግጠው ወደቁ ''ተንሥኡ ወኢትፍርሁ'' ተነሱ አትፍሩ ብሎ አንስቷቸዋል።ከርእሰ ደብር ሲወርድ ያዩትን የሰሙትን እስከ ትንሣኤው ለማንም እንዳይናገሩ አዟቸዋል።(ማቴ17:3-9)

ምሥጢረ መንግስቱን ስለምን በታቦር ተራራ አደረገው?

ብዙ ተራሮች እያሉ ስለምን ታቦር ተራራን መረጠ ቢሉ ትንቢቱ እና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ ነው።
ትንቢቱ:- "ታቦርና አርሞንየም በስምህ አምነው በተደረገላቸው ነገር ደስተኛ ይላቸዋል፤ስምህን ያመሰግናሉ፤ለስምህም ምስጋና ያቀርባሉ።" መዝ 88:12
ምሳሌውም:-
ስለምን ሦስቱ ሐዋርያትን ብቻ ይዞ ወጣ?

ስለምን ዘጠኙን ሐዋርያት ከእግረ ደብር ትቶ ሦስቱን ብቻ ጴጥሮስ ፣ዮሐንስና ያዕቆብን ይዞዋቸው ወደ ተራራው ወጣ?

በይሁዳ ምክንያት ነው።ኀጥእ ሰው የእግዘብሔርን ክብር እንዳያይ ያርቁታል እንዲል(ኢሳ.26:13)በዚያን ጊዜ ይሁዳ ከሐዋርያት መካከል ነበርና ያንንም የብርሃነ መለኮት ምሥጢር ማየት አልተገባውም ነበርና እሱን ብቻውን ትቶት ቢሄድ "ከምሥጢሩ ቢለየኝ ሞትን አሰብኩበት" እንዳይል ከእሱ ጋ ዘጠኙን ከዛው ትቷቸው ሄዷል።
➮ ሦስቱ ሐዋርያት የምሥጢር ሐዋርያት ናቸውና።
➮ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችን እሞታለው እሰቀላለው ባለ ጊዜ አይሁንብህ ብሎት ነበርና አብ በሰማይ እርሱን ልጄን ስሙት ብሎ ሲመሰክርለት ይህ ላንተ አይገባም አትበሉት አትቃወሙትእርሱ የሚላችሁን ስሙ ሲላቸው ነው
➮ ቅዱስ ጴጥሮስ የእግዚአብሔር ወልድ የባሕርይ ልጅነቱን መስክሮ ነበርና እግዚአብሔር አብም ሲመሰክርለት እንዲሰማ ወደ ተራራው ወስዶታል።
➮ ሦስቱም ለፍቅሩ ይሳሱ ነበርና ቅዱስ ጴጥሮስ ለጌታ ካለው ፍቅር የተነሳ አትሙት አትሰቀል ብሎታልና፤ቅዱስ ዮሐንስም በወንጌል "የጌታ ወዳጅ" ተብሎ ተጽፏልና፤ ቅዱስ ያዕቆብ ይኸዎም "እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችው?"(ማቴ 20:20) አዎ በማለት በሄሮድስ አግሪጳ ሰማዕት ሆኖ መሞቱ ማረጋገጫ ነው።

ኤልያስና ሙሴን ለምን አመጣቸው?

ሙሴ እግዚአብሔር በሚያናግርበት ጊዜ እንዲህ ብሎት ነበር "በአንተ ዘንድ ባለሟልነት ማግኘቴ እውነት ከሆነስ ፊት ለፊት ተገልጸህልኝ ልይህና በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘቴን ልወቅ።" እግዚአብሔርም "ጀርባዬን ታያልህ ፊቴን ግን አታይም" ብሎት ነበርና ከብሔረ ሙታን አምጥቶ አሳይቶታል።
➣ ጌታች ነቢዩ ኤልያስን"በኃለኛው ዘመን ምስክር ትሆነኛለህ" ብሎት ነበርና ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶታል ታያለህ የተባለው ሙሴ አይቷል ትመሰክራለህ የተባለው ኤልያስም ጌታችን አምላከ ኤልያስ እንደሆነ መስክሮለታል።
➣ ጌታች በፊሊጶስ ቄሳር ሰዎች ማን እንደሚሉት በጠየቀ ጊዜ አንዳንዶች ሙሴ አንዳንዶች ኤልያስ ብለው ነበርና አምላከ ሙሴ አምላከ ኤልያስ እንደሆነ ሊያሳያቸው አምጥቷቸዋል።
➣ አይሁድ ፈሪሳውያን ጌታችንን እንደ ሕግ ተላላፊ አድርገውት ነርና ሕግን የሰራው ሙሴን ና ለሕግ ቀናተኛው ኤልያስን በማምጣት ሕግ አለማፍረሱን አረጋግጦላቸዋል።
➣ አምላካችን እግዚአብሔር በሙታንና በሕያዋን ላይ ስልጣን መኖሩን ለማጠየቅ ሙሴን ከብሔረ ሙታን ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን አምጥቷቸዋል።
ፍጻሜው ግን

1, ታቦር ተራራ የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ነው

ተራራን በብዙ ችግር እንደሚወጡት መንግስተ ሰማያትም በብዙ ድካም እንደሚገቡባት ለመናገር
➣ በታቦር ከብሉይ ኪዳን ነቢያትና ከሐዲስ ኪዳን ሐዋርያት እንደተገኙ መንግስተ ሰማያት ነቢያትም ሐዋርያትም በአንድ ላይ ይወርሷታልና።
➣ በታቦር ተራራ ሞተው ከተቀበሩት ሙሴ በብሔረ ሕያዋን ከሚኖሩ ኤልያስ እንደተገኙባት በመንግስተ ሰማያትም በሞተ ሥጋ የተለዩ ሕያው ሆነው እንደ ኤልያስ ፣ እንደ ሄኖክ የኖሩትም በአንድ ላይ ይገቡባታልና
2. ታቦር የቤተክርስቲያን ምሳሌ ነው።
በብሉይ ኪዳን የክርስቶስን መገለጥ የተናገሩ ነቢያት በሐዲስ ኪዳን የተገለጠውን የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅነት የሰበኩ ሐዋርያት በአንድ ላይ የተገኙባትና ያመሰገኑባት ናትና።በየዓመት ውጥስ ነሐሴ 13 ቀን ቤተክርስቲያናችን የምታከብረው ከዘጠኙ ዐበይት የጌታችን የመድኃኒታችን በዓላት አንዱ የሆነው የደብረ ታቦር በዓል የዚህ ታሪክ መታሰቢያ ነው።በዚህም ዕለት ሕፃናት ጅራፋቸውን ገምደው ያስጮሀሉ። ይኸውም ጅራፍ ሲጮህ እንደሚያስደነግጥ ሁሉ ከጌታ ጋር የነበሩ ሦስቱ ሐዋርያት አብ በደመና ሆኖ ሲናገር የመደንገጣቸው የመውደቃቸው ምሳሌ አንድም የጅራፉ ድምጽ ከሰማይ የተሰማው የእግዚአብሔር አብ ድምጽ ምሳሌ እንዲሁም ሙልሙል መጋገሪ(መሰጠቱ) ችቦ የመብራቱ በዚያን ጊዜ የሚጠብቁ እረኞች የመለኮትን ብርሃን ሲበራ ገና ያልመሸ መስሏቸው በዚያው ሲቆዮ ቤተሰቦቻቸው ችቦ አብርተው እንዲሁም ሙልሙል ዳቦ ይዘው ሊፈልጓቸው የመውጣታቸው ምሳሌ።

➣ አዘጋጅ ፦ መሠረት ዳኜ

#ዐምደ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህረትቤት
https://t.me/Amde_Tewahedo_SS
215 views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 05:19:18
401 views02:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 05:19:18 #ጾመ ማርያም (ጾመ ፍልሰታ)
ጾመ ማርያም ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት እንድንጾማቸው ከታዘዙት ሰባቱ አጽዋማት አንዱ ነው ። (ፍትሐ ነገስት አንቀጽ 15) ይህ ጾም በክርስቲያኞች በተለይ በህጻናቱ ዘንድ ተናፋቂ ጾም ሲሆን ቤተክርስቲያን ጾሙን ልዮ በሆነ ሥርዓት ታሳልፈዋለች ። ጾሙ ምንጊዜም በየዓመቱ ነሐሴ 1 ይገባና ነሐሴ14 የሱባኤው ማብቂ ሲሆን የጾሙ ፍቺ በ 16 ይሆናል ። ጾመ ፍልሰታ ጥንተ ታሪኩ እንዲ ነው ። አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ባረፈች ጊዜ ሐዋርያት ሥጋዋን ለመቅበር ወደ ጌቴ ሴማኒ ይዘው ሲሔዱ ለቅናት የማያርፉት አይሁድ ተነሡባቸው < ከዚህ ቀደም ልጇ ሞተ ፣ ተነሣ ፣ ዐረገ እያሉ ሲረብሹን እንደነበር አሁን ደግሞ እሷን ሞተች ፣ ተነሣች፣ ዐረገች እያሉ ሊረብሹን አይደለምን > ብለው ከተማከሩ በኃላ ሥጋዋን ቀምተው ሊያቃጥሉት ወሰኑ ።
ከዚህ ሥጋዋን ከሐዋርያት ለመቀማት ሲነሱ ከእነሱ መካከል ታውፋንያ የተባለ ሰው አስቀድሞ በመድረስ የአልጋውን ሸንኮር በመያዝ ሊጥላት ሲሞክር የእግዚአብሔር መልዓክ ሁለት እጆቹን ቆርጦት እጁ የአልጋው ሸንኮር ላይ ይቀራል ። ይህን ያዩ አይሁድ ጥለውት ፈርተው ሸሹ (መዝ117፥10-12) ታውፋንያም እያለቀሰ ሐዋርያትን ለመናቸው ሐዋርያት ወደ እርሷ እንዲለምን ነገሩት እርሷን ቢለምን የሚራራ ልብ ያላት እመቤታችን ለሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ '' በእናቱ ምልጃና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተፈወስ ብለህ እጆቹን ከቦታቸው አድርጋቸው አለችው ፤ ቅዱስ ጴጥሮስም ያለችውን አደረገ ታውፋንያም በተዓምር እጆቹ ወደ ነበሩበት ተመለሱ ። መልአኩም ሥጋዋን ። ነጥቆ ይወስድና በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጣት (መፍረስና መበስበስ፣ መቀዝቀዝ ሽታ ሳይኖረው ሥጋዋ እስከ ትንሣኤዋ ትኩስ በድን ሆኖ ለ 250 ቀናት ቆይቷል)
ከዚያም በኃላ ሐዋርያት ሥጋዋን አግኝተው ይቀብሩ ዘንድ ባረፈች በስምንተኛው ወር ከ ነሐሴ 1 ጀምሮ እስከ ነሐሴ 14 ቀን ሁለት ሱባኤ ይዘው በ14ኛው ቀን ሥጋዋ በእግዚአብሔር ፈቃድ ተመልሶላቸው ፣ በደስታ በጌቴ ሴማኒ አሳረፉት ። በሦስተኛው ቀንም ከ12 ሐዋርያት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ስታርግ ያያታል እርሱም ትንሣኤዋን የደበቀችው መስሎት 'በፊት የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሣኤ ሳላይ ብሎ ሲያዝን ትንሣኤዋን ከእርሱ ቀድሞ ያየ እንደሌለ ትነግረውና ለሐዋርያት ሲነግራቸው እንደ መረጃ እንዲያሳያቸው ሰበኗን ሰጥታው ዐረገች። ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በዕለተ ቀብሯ አልተገኘም ነበርና ለሐዋርያቱን ምንም ነገር እንዳላየ የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ ይላቸዋል እነርሱም ሥጋዋን አግኝተው (ተቀብለው) እንደቀበሯት ይነግሩታል እረሱም አውቆ እንዳላመነ ሲሆንባቸው መቃብሯን ሊያሳዩት ወደ መቃብሯ ስፍራ ሔደው መቃብሩን ቢከፍቱት መቃብር ውስጥ ሥጋዋ የለም ። እርሱም እንዳረገች የሆነውን ነገር ይነግራቸዋል ። ለመረጃ የሰጠችውን ሰበኗንም ለሐዋርያቱ ይሰጣቸዋል እነርሱም ለበረከት ተከፋፍለው እራሳቸው ላይ ያስሩታል ። በዓመቱ ሐዋርያት ተሰብስበው ለቅዱስ ቶማስ የተገለጸለት የትንሣኤዋ የእርገቷ ነገር እንዲገለጽላቸው ድጋሚ በዓመቱ ሱባኤ ይገባሉ ። የትንሣኤዋና የዕርገቷ ነገርም ይገለጽላቸዋል ።
ቤተክርስቲያናችን ይህን ጾም ከእመቤታችን ምልጃዋን ረድኤቷን ፣ በረከቷን ፤ የሐዋርያቱ በረከት ይደርሰን ዘንድ ከአዋጅ አጽዋማት በማስገባት እንድንጾም ታዘናለች ።
ጾመ ማርያም ሌሊት ከስድስት ሰአት ጀምሮ እስከ ንጋት ሰአታት ተቁሞ ፣ ቀን ላይ ስብሐተ ነግ (የተባለ ) በቅዱስ ያሬድ የተደረሰ የዜማ ምስጋና ከውዳሴ ማርያም ዜማ ጋር ይደረሳል ። ከቅዳሴ በፊት ደግሞ የዕለቱ ውዳሴ ማርያም እና ቅዳሴ ማርያም ይተረጎማል ። እግዚአብሔር አምላካችን ጾሙን የበረከት የእርቅ አድርጎልን ሀገራችንን ሰላም ያደርግልን ዘንድ ፈቃዱ ይሆኑ !!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር
አሜን !!!
ዋቢ መጻሕፍት
➣ በእንተ ጾም
➣ የእመቤታችን የሕይወት ታሪክ እና ዘለዓለማዊ ክብሯ
https://t.me/Amde_Tewahedo_SS
826 viewsedited  02:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 07:18:33 +እንዘ ሰለስቱ አሃዱ +

ግጥምና ዜማ :-ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
በዘማሪ:-ሊቀዲያቆን ወንደሰን በላይ

+እንዘ ሠለስቱ+

ዓለምን በጥበብ ለፈጠረ ጌታ
ዘወትር እናቅርብ የክብር ሰላምታ
መላእክት በፍርሃት ለሚያመሰግኑት
ለሥላሴ እናቅርብ አኮቴት ስብሐት

ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እንዘ ሠለስቱ አሐዱ

በሃሳቡ ብቻ ዓለምን ለሠራ
በአምላካዊ ቃሉ ብርሃንን ላበራ
ሰውን በምሳሌው በአርኣያው ፈጥሮ
ከአፈር አበጀው ከሁሉ አክብሮ

ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እንዘ ሠለስቱ አሐዱ

የሰው ልጅ ሲበድል አምላክ ልሁን ብሎ
የሰይጣንን ምክር አምኖ ተቀብሎ
አዳም አዳም ብሎ ፍለጋ ለወጣ
ለይቅር ባይ ጌታ ምስጋናን እናምጣ

ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እንዘ ሠለስቱ አሐዱ

ወደ ዓለም ልኮ አብ አንድ ልጁን
ወልድም በፈቃዱ መጣ ሰው ሊሆን
በመንፈስ ቅዱስ ግብር ተጸንሶ ተወልዶ
አክሊል አቀዳጀን በመስቀል ተዋርዶ

ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እንዘ ሠለስቱ አሐዱ

እንዴት ላመስግንህ የቅዱሳን አምላክ
በልቤ ጉልበትም ለአንተ ልንበርከክ
ዓይኔን ከእጄ ጋር ወደ ላይ አንሥቼ
እዘምርልሃለሁ እንደ አባቶቼ

ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እንዘ ሠለስቱ አሐዱ

ዝማሬ : ሊቀ ዲያቆናት ወንድወሰን በላይ
ግጥምና ዜማ: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
602 views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 08:48:05
538 views05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 08:46:35 # ቅዱስ ጳውሎስ

ጳውሎስ ማለት ነዋይ ህሩይ ማለት ነው። |ሐዋ 9:15| አንድም ብረሃን ማለት ነው
የቀደመ ስሙ ሳዖል ነው ሳዉል ማለት ጸጋ እግዚአብሔር የበዛለት ማለት ነው። ትውልዱም ከ ነገደ ብንያም ነው።(ፊሊ 3:5)አባቱም ዮስአስ ይባላል
የተወለደውም ጌታ ከተወለደ በ 5 ዓመት ሲሆነው በጠረሴስ ነው። ከ 5 ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም ተቀምጦ ከመምር ገማልያ ህገ ኦሪት ተምሯል።በወንጌል ያመነውም ጌታ በዐረገ በ10 ዓመት ነበረ ። ሳውል ክርስቲያኖችን የሚያሳድድ ነበር
ጌታም በደማቅ መበረቅ ተገልጦለት ሳዉል ሳዉል ስለምን ታሳድደኛለህ ብሎ ተናግሮታል ፤ እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ፦ ጌታ ሆይ፥ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ? አለው። ጌታም፦ ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል አለው።
፤ ከእርሱም ጋር በመንገድ የሄዱ ሰዎች ድምፁን እየሰሙ ማንን ግን ሳያዩ እንደ ዲዳዎች ቆሙ። ሳውልም ከምድር ተነሣ፥ አይኖቹም በተከፈቱ ጊዜ ምንም አላየም፤ እጁንም ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አገቡት።
ሳያይም ሦስት ቀን ኖረ፤ አልበላምም አልጠጣምም። በደማስቆም ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ፥ ጌታም በራእይ፦ ሐናንያ ሆይ፥ አለው። እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ እነሆኝ አለ።ጌታም፦ ተነሥተህ ቅን ወደ ሚባለው መንገድ ሂድ፥ በይሁዳ ቤትም ሳውል የሚሉትን አንድ የጠርሴስ ሰው ፈልግ፤
፤ እነሆ፥ እርሱ ይጸልያልና፤ ሐናንያ የሚሉትም ሰው ገብቶ ደግሞ እንዲያይ እጁን ሲጭንበት አይቶአል አለው።
፤ ሐናንያም መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ በኢየሩሳሌም በቅዱሳንህ ላይ ስንት ክፉ እንዳደረገ ስለዚህ ሰው ከብዙዎች ሰምቼአለሁ፤በዚህም ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን አለው አለ።፤ ጌታም፦ ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤ ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው እኔ አመለክተዋለሁና አለው።፤ ሐናንያም ሄዶ ወደ ቤቱ ገባ፥ እጁንም ጭኖበት፦ ወንድሜ ሳውል ሆይ፥ ጌታ፥ እርሱም በመጣህበት መንገድ የታየህ ኢየሱስ ነው፥ ደግሞ ታይ ዘንድና መንፈስ ቅዱስ ይሞላብህ ዘንድ ላከኝ አለ።
፤ ወዲያውም እንደ ቅርፊት ያለ ከዓይኑ ወደቀ፥ ያን ጊዜም ደግሞ አየ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ፥ ጌታችንም ከ 72 አርድእት አንዱ አድርጎታል ከዚያም በኃላ በ ክርስቶስ እመኑ እያለ አስተምሯል። ብዙዎችንም በክርስቶስ ሰም አስተምሮ አጥምቋኣቸዋል (ሐዋ14:10-18) በእስር ቤት በነበረበት ወቅትም ብዙ ሰዎችን አሰተምሮ አሳምኗቸዋል። ቅዱስ ጳውሎስ 14 መልዕክታትን ጽፏል ።
ከብዙ ተጋድሎ በኃላ በ 69 ዓ.ም ሲያስተምር ሄሮን ቄሳር አስጠሩት ሲል አዘዘ በንጉስ ፊት ሲቀርብ መሰቀሉን ይዞ ቀረበ ፤ንጉሱም ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡ አለ!!! በመጎናጸፊያውም ሸፍኖ ሰይፎታል ። ቅዱስ ጳውሎስም ሲያርፍ የ 72ዓመት አረጋዊ ነበረ። ከቅዱስ ጴጥሮስም ጋር ሰማዕትነት የተቀበሉትም በ አንድ ቀንና በአንድ ቦታ ነበር ። ይህም እለት ወርሃ ሐምሌ ቀን 5 ነበር ። የነዚህን ቅዱሳን በዓል ጾመ ሐዋርያት የሚፈታበት እንዲሆን አባቶች ሥርዓት ሠርተውልናል ። በዓላቸውም ታቦታቸው ባለበት ቦታ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ። ስለ እነዚህ ቅዱሳን ምልጃ ጸሎት ብሎ እግዚአብሔር ምሕረቱን ይላክልን!!!

ምንጭ፦➣ገድለ ሐዋርያት፣
➣ ዜና ሐዋርያት፣
➣ ነገረ ቅዱሳን ቁጥር
➣ መዝገበ ታሪክ ክፍል 2
➣ መጽሐፍ ቅዱስ

https://t.me/Amde_Tewahedo_SS
748 viewsedited  05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 08:46:35 # ዝክረ ቅዱሳን ሐምሌ 5

ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ በሰማዕትነት አረፉ

# ቅዱስ ጴጥሮስ
ቅዱስ ስምዖን የተወለደው በገሊላ ባህር ዳር በምትገኘው ቤተሣይዳ ነው።
(ማቴ 16:18) ጴጥሮስ ብሎ ስም ያወጣለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። ስሙ ፦
በግእዝ ➣ ኰኲሐ ሃይማኖት
በዕብራይስጥ ➣ ኬፋ
በግሪክ (በጽር ቋንቋ )➣ ጴጥሮስ ማለት ሲሆን የሁሉም ትርጉም 'አለት' (መሠረት) የሚለውን ትርጉም ይይዛል (ማቴ 16 ፥ 18) ። የ አባቱ ስም ዮና ሲሆን ትውልዱም ከ ነገደ ሮቤል ነው።ዮና ከ ነገደ ስምዖን የምትሆን አንዲት ሴትን አግብቶ ቅዱስ ጴጥሮስን ወለደ ። ቅዱስ ጴጥሮስም ከተወለደ በኃላ እንደ ኦሪት ትእዛዝ መሠረት በስምንተኛው ቀን ወደ ግዝረት ቤት አግብተውት ሰሙን በ እናቱ ነገድ ስም ስምዖን ብለው ሰይመውታል።
ዕድሜውም አምስት ዓመት ሲሆን እነደ አይሁድ ሥርዓት ህገ ኦሪትን እየተማረ እንዲያድግ በቤተ ሳይዳ ወደ ምትገኘው ቅፍርናሆም ላኩት ። በዚኑ በባህር ዳር በምትገኘውና ታላቅ የንግድ ቦታ በሆነችው ቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረው ኢያኢሮስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት አሠርቶት በነበረው ምኩራብ እየተማረ አደገ ከዚያም በኃላ በዚያ ከተማ ቤት ሠርቶ ኮንከርድያ (ጴርጴቱዋ)የምትባል ሴት አግብቶ እነደ አባቱ ዮና ይተዳደርበት በነበረው ሥራ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሳ በማጥመድ እና በመሸጥ ይተዳደር ነበር ።ጌታችን ዓሳ ከሚያጠምድበት ተጠርቶት ሐዋርያ ሐዋርያት አድርጎታል ማቴ 4:19 ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኃላ መዲናቸው ኢየሩሳሌም አንድ ዓመት ካስተማሩ በኃላ ወንጌል ካልደረሰበት ለማድረስ ዓለምን በዕጣ በተከፋፈሉ ጊዜ ርዕሰ ሐዋርያ ነውና ሮምን ደርቦ ደርሶቶታል። በሮምም ለ 25 ዓመታት አስተምሯል ከዚያ በፊት ግን በሠማርያ፣በልዳ፣በኢዮጴ ፣በአንጾኪያ፣ ጳንጦስ፣ በገላቲያ፣ በቀላጳዶያና እና በቢታንያ እስተምሯል።በ ትምህርቱም ሙታንን ከሞት አስነስቷል ።(የሐ ሥራ 9:32-34) ያስተማራቸው ምእመናንም ከሀይማኖታቸውእንዳይወጡ 2 መልክታትን ጽፎላቸዋል ።ንጉሱ ኔሮን ቄሳር የተባለ የሮም ንጉሥ ጣዖት አምላኪ ስለነበረ ። ለጣዖት እንዲሰግድ በአሰገደደው ጊዜም ለጣዖት አልሰግድም በማለቱ ንጉሱ ሊያስገድለው ከሮሜ መኳንንት ጋር ተማክሯል ። ይህን የሰሙ ምዕመናን እንዲወጣ ይነግሩታል እርሱም እንዳሉት ሲወጣ ጌታችን መስቀል ተሸክሞ ወደከተማው ሲወጣ ያገኘዋል ። እርሱም 'ጌታዪ ወዴት ትሔዳለህ ' አለው ። ' ዳግመኛ ልሰቀል ወደ ሮሜ ከተማ እሔዳለሁ ' ብሎ መለሰለት ቅዱስ ጴጥሮስም ' ዳግመኛ ትሰቀላለህን' አለው ። ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌ ሳለ የነገረ ነገር አስተውሎ ወደ ከተማው ተመልሶ የሆነውን ለምዕመናን ይነግራቸዋል እነርሱም ይወዱት ነበረና እጅግ አዘኑ ።
ንጉሥ ኔሮን እንዲሰቅሉት አዘዘ ። ቅዱስ ጴጥሮስም ወታደሮችን እንዲህ ብሎ ይለምናቸዋል ' ጌታዬኢየሱስ ክርስቶስ ወደላይ ተሰቀለ እኔ ወደላይ ልሰቀል አይገባኝም ቁልቁል ልሰቀል ይገባኛል ' ብሎ ይለምናቸዋል ። እነርሱም እንደነገራቸው አድርገው ሰቀሉት ። በዚህች ዕለትም የሰማዕትነትን ክብር ተቀበለ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ጸሎት ይማረን ።
380 views05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 13:34:48 https://youtube.com/shorts/jULgnJPmP-w?feature=share
421 views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ