Get Mystery Box with random crypto!

# ቅዱስ ጳውሎስ ጳውሎስ ማለት ነዋይ ህሩይ ማለት ነው። |ሐዋ 9:15| አንድም ብረሃን ማለት ነ | {ብሒለ አበው ወ ሕይወት መንፈሳዊ}

# ቅዱስ ጳውሎስ

ጳውሎስ ማለት ነዋይ ህሩይ ማለት ነው። |ሐዋ 9:15| አንድም ብረሃን ማለት ነው
የቀደመ ስሙ ሳዖል ነው ሳዉል ማለት ጸጋ እግዚአብሔር የበዛለት ማለት ነው። ትውልዱም ከ ነገደ ብንያም ነው።(ፊሊ 3:5)አባቱም ዮስአስ ይባላል
የተወለደውም ጌታ ከተወለደ በ 5 ዓመት ሲሆነው በጠረሴስ ነው። ከ 5 ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም ተቀምጦ ከመምር ገማልያ ህገ ኦሪት ተምሯል።በወንጌል ያመነውም ጌታ በዐረገ በ10 ዓመት ነበረ ። ሳውል ክርስቲያኖችን የሚያሳድድ ነበር
ጌታም በደማቅ መበረቅ ተገልጦለት ሳዉል ሳዉል ስለምን ታሳድደኛለህ ብሎ ተናግሮታል ፤ እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ፦ ጌታ ሆይ፥ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ? አለው። ጌታም፦ ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል አለው።
፤ ከእርሱም ጋር በመንገድ የሄዱ ሰዎች ድምፁን እየሰሙ ማንን ግን ሳያዩ እንደ ዲዳዎች ቆሙ። ሳውልም ከምድር ተነሣ፥ አይኖቹም በተከፈቱ ጊዜ ምንም አላየም፤ እጁንም ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አገቡት።
ሳያይም ሦስት ቀን ኖረ፤ አልበላምም አልጠጣምም። በደማስቆም ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ፥ ጌታም በራእይ፦ ሐናንያ ሆይ፥ አለው። እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ እነሆኝ አለ።ጌታም፦ ተነሥተህ ቅን ወደ ሚባለው መንገድ ሂድ፥ በይሁዳ ቤትም ሳውል የሚሉትን አንድ የጠርሴስ ሰው ፈልግ፤
፤ እነሆ፥ እርሱ ይጸልያልና፤ ሐናንያ የሚሉትም ሰው ገብቶ ደግሞ እንዲያይ እጁን ሲጭንበት አይቶአል አለው።
፤ ሐናንያም መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ በኢየሩሳሌም በቅዱሳንህ ላይ ስንት ክፉ እንዳደረገ ስለዚህ ሰው ከብዙዎች ሰምቼአለሁ፤በዚህም ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን አለው አለ።፤ ጌታም፦ ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤ ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው እኔ አመለክተዋለሁና አለው።፤ ሐናንያም ሄዶ ወደ ቤቱ ገባ፥ እጁንም ጭኖበት፦ ወንድሜ ሳውል ሆይ፥ ጌታ፥ እርሱም በመጣህበት መንገድ የታየህ ኢየሱስ ነው፥ ደግሞ ታይ ዘንድና መንፈስ ቅዱስ ይሞላብህ ዘንድ ላከኝ አለ።
፤ ወዲያውም እንደ ቅርፊት ያለ ከዓይኑ ወደቀ፥ ያን ጊዜም ደግሞ አየ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ፥ ጌታችንም ከ 72 አርድእት አንዱ አድርጎታል ከዚያም በኃላ በ ክርስቶስ እመኑ እያለ አስተምሯል። ብዙዎችንም በክርስቶስ ሰም አስተምሮ አጥምቋኣቸዋል (ሐዋ14:10-18) በእስር ቤት በነበረበት ወቅትም ብዙ ሰዎችን አሰተምሮ አሳምኗቸዋል። ቅዱስ ጳውሎስ 14 መልዕክታትን ጽፏል ።
ከብዙ ተጋድሎ በኃላ በ 69 ዓ.ም ሲያስተምር ሄሮን ቄሳር አስጠሩት ሲል አዘዘ በንጉስ ፊት ሲቀርብ መሰቀሉን ይዞ ቀረበ ፤ንጉሱም ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡ አለ!!! በመጎናጸፊያውም ሸፍኖ ሰይፎታል ። ቅዱስ ጳውሎስም ሲያርፍ የ 72ዓመት አረጋዊ ነበረ። ከቅዱስ ጴጥሮስም ጋር ሰማዕትነት የተቀበሉትም በ አንድ ቀንና በአንድ ቦታ ነበር ። ይህም እለት ወርሃ ሐምሌ ቀን 5 ነበር ። የነዚህን ቅዱሳን በዓል ጾመ ሐዋርያት የሚፈታበት እንዲሆን አባቶች ሥርዓት ሠርተውልናል ። በዓላቸውም ታቦታቸው ባለበት ቦታ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ። ስለ እነዚህ ቅዱሳን ምልጃ ጸሎት ብሎ እግዚአብሔር ምሕረቱን ይላክልን!!!

ምንጭ፦➣ገድለ ሐዋርያት፣
➣ ዜና ሐዋርያት፣
➣ ነገረ ቅዱሳን ቁጥር
➣ መዝገበ ታሪክ ክፍል 2
➣ መጽሐፍ ቅዱስ

https://t.me/Amde_Tewahedo_SS