Get Mystery Box with random crypto!

#የወር_አበባ_በሄደ_በሚቀጠለው_ቀን_ግንኙነት_ባደርግ_ርግዝና_ይፈጠራል ና መሰል ጥያቄወች በብዛት | Feya Medical center Bale Robe

#የወር_አበባ_በሄደ_በሚቀጠለው_ቀን_ግንኙነት_ባደርግ_ርግዝና_ይፈጠራል ና መሰል ጥያቄወች በብዛት ይጠየቃሉ
አንድ ቋሚ የወር አበባ ያላት ሴት የወር አበባ በአማካይ በየ 28 ቀኑ ይመጣል ተብሎ ይታሰባል
ነገር ግን ከ21 __እሰከ 35 (ሲፈጥን በየ 21 ቢበዛ ደግሞ በየ 35 ቀንሊመጣይችላል) ማለት ነው
ስለዚህ ርግዝና የሚፈጠረው መቸ ነው የማይፈጠረውስ መቸ ነው ?
በአማካይ መደበኛ የሚባለውን ወስደን ስናይ የወር አበባ በየ 28 ቀን ይመጣል
የወር አበባ በጀመረ የመጀመሪያወቹ 5 ቀናት በአማካይ የወር አበባ የሚፈሰባቸው ቀናት ናቸው።
ከ 6ኛው _ 14 ኛው ቀን ያለው Follicular phase ይባላል።ይህም ኢስትሮጂን :FSH የሚባሉት ሆርሞኖች የሚጨምሩበትና የማህፀን ግድግዳ እየወፈረ የሚሄድበት ጊዜ ነው
14 ኛው ቀን ውፃት(ovulatio) ይባላል። እንቁላል ለፅንሰት ዝግጁ ሆኖ ይወጣል ማለት ነው።በዚህ ግዜ የግብረ ስጋ ግንኙነት ከተፈፀመ ርግዝና የመፈጠር እድሉ በጥም ከፍተኛ ነው
ከ 14 _28ኛው ያለው ቀን lutheal phase ይባላል።ርግዝና ከተፈጠረ ማህፀን ፅንሱን ለማሳደግ ዝግጁ የሚሆንበት ጊዜ ካልተፈጠረ ደሞ የዳበረው የማህፀን ወለል በመፈራረስ በወር አበባ መልክ የሚፈስበት ጊዜ ነው።
ሰለዚህ 14 ኛው ቀን ላይ ርግዝና ይፈጠራል።ነገር ግን የወንድ ስፐርም የሴትብልት ላይ እስከ 5 ቀን ድረስ ሳይሞት ይጠብቃል
እንቁላልም ከወጣች ጀምሮ እስከ 24 ሰዓት ሳትሞት ትጠብቃለች።
ስለዚህ ከ 14 ኛው ቀን 5 ቀን ወደ ፊት ና 3 ቀን ወፈ ሗላ ርግዝና የሚፈጠርባቸው ቀናት ናቸው።
የወር አበባ በየ 28 ቀን የማይመጣ ከሆነ ና ቋሚ ከሆነ ከ14 ኛው ቀን እሰከ 28 lutheal phase ያልነው ቋሚ 14 ቀን ስለሆነ ተመሳሳይ ሰሌት በመጠቀም ማወቅ ይቻላል።
FEYA MEDIUM CLINIC BALE ROBE