Get Mystery Box with random crypto!

ደም ማነስ / Anemia የደም ማነስ የሚከሰተው በቂ ቀይ የደም ሴሎች ሳይኖሩ ሲቀር ነው:: የደ | Feya Medical center Bale Robe

ደም ማነስ / Anemia

የደም ማነስ የሚከሰተው በቂ ቀይ የደም ሴሎች ሳይኖሩ ሲቀር ነው:: የደም ማነስ የሚባለው የሂሞግሎቢን መጠን ለወንዶች ከ13.5 ግራም/ደሊ በታች፣ ለ ሴቶች ደግሞ ከ12.0 ግራም/ደሊ በታች ሆኖ ሲገኝ ነው::

ብዙ ሰዎች በተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ በአንጀት መታወክ፣ ሥር በሰደዱ በሽታዎች፣ በኢንፌክሽን እና በሌሎች ሁኔታዎች ምክንያት ለደም ማነስ የተጋለጡ ይሆናሉ። በወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች፣ እርጉዞች እና ሥር የሰደደ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች ለዚህ በሽታ በጣም የተጋለጡ ናቸው።

የተለያዩ የደም ማነስ ዓይነቶች ቢኖሩም እያንዳንዳቸው የሚመሳሰሉበት ነገር አላቸው:: እርሱም በደም ዝውውር ውስጥ ያሉ ቀይ የደም ሴሎች ቁጥር የሚቀንስ መሆኑ ነው::

የደም ማነስ ምልክቶች እነዚህን ያካትታል

● የድካም ስሜት
● ራስ ምታት
● የትንፋሽ ማጠር
● የቆዳ መገርጣት እና መድረቅ
● የልብ ምት መጨመር
● በታችኛው እግር ላይ ያልታሰበ እንቅስቃሴ
● ቀዝቃዛ እጅ እና እግር
● በአንዱ ወይም በሁለቱም ጆሮዎች ላይ ያልተለመደ ድምጽ ወይም ጩኸት

የደም ማነስ ካለብዎት የአይረን መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን እንደ የበሬ ሥጋ፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ለውዝ፣ የወተት ተዋጽኦዎች፣ የፎሊክ አሲድ ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦች እንደ ሎሚ እና ብርቱካን፣ እና ጥራጥሬዎች መመገብ ይመከራል::

Anemia occurs when there are not enough red blood cells. Anemia is when the hemoglobin level is below 13.5 g / dL for men and 12.0 g / dL for women. Many people are at risk for anemia due to malnutrition, intestinal disorders, chronic diseases, infections and other conditions. Menstruating women, pregnant women and people with chronic health problems are at increased risk.

Although there are different types of anemia, each one has something in common. This is to reduce the number of red blood cells in the bloodstream.

Symptoms of anemia include the following

● Feeling tired or fatigue
● Headache
● Shortness of breath
● Pale and dry skin
● Increased heart rate
● Unexpected movement of the lower leg.
● Cold hands and feet
● An unusual sound or noise in one or both of your ears(tinnitus)

If you have anemia, it is recommended to eat foods high in iron, such as beef, green leafy vegetables, nuts, dairy products, foods high in folic acid, such as lemons, oranges, and grains.