Get Mystery Box with random crypto!

]☞#የኩላሊት እና #የሽንት_ቧንቧ ኢንፌክሽን!❞ የሽንት ቧንቧ ከኩላሊታችን እስከ ሽንት መዉጫ | Feya Medical center Bale Robe

]☞#የኩላሊት እና #የሽንት_ቧንቧ ኢንፌክሽን!❞

የሽንት ቧንቧ ከኩላሊታችን እስከ ሽንት መዉጫ ያሉት ሁሉንም የሽንት ቱቦዎች እና ማጠራቀሚያወችን የሚያካትት ሲሆን የሚይዛቸዉ
ኩላሊትን፣
ዩሬተር (ከኩላሊት ወደ ሽንት ማጠራቀሚያ ፊኛ ሽንት የሚያስተላልፍ ቱቦ ነዉ)፣
የሽንት ማጠራቀሚያ ፊኛ እና
ዩሬተር (የዉሃ ሽንት ማስወገጃ ቱቦ) ናቸዉ።
•---•---•

#የኩላሊትና_የሽንት_ቧንቧ_ኢንፌክሽን_ምንድ_ነዉ?
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የምንለው ከኩላሊት እስከ የውሃ ሽንት ማስወገጃ ጫፍ ድረስ የሚከሰተውን የኢንፌክሽን ዓይነት ነው፡፡
በአብዛኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሚያጠቃው የውሃ ሽንት የሚከማችበት የሽንት ፊኛ በመባል የሚታወቀውን የአካል ክፍላችንን ነው፡፡
•---•---•

#በብዛት_ተጠቂዎች_እነማናቸዉ?
በአብዘሀኛዉ ወጣት ሴቶች ላይ የሚከሰት ነዉ። ምክንያቱም በተፈጥሮ የሴቶች ሽንት ማስወገጃ ቱቦ ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር በማጠሩ ነዉ። ስለዚህ ከወንዶች ይልቅ ተጠቂነታቸው እንደሚጨምር ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በሽታን የመከላከል አቅማቸው የቀነሰ እንደ የስኳር ሕመምተኞች እና እርጉዝ ሴቶች ላይም በብዛት ይከሰታል፡፡
•---•---•

#እንዴት_ሊከሰት_ይችላል?
ባክቴሪያ ከሽንት ማስወገጃ ጫፍ ወደላይኛው የሽንት ቧንቧ አካል ሲገባ እና ይህም ሊከሰት የሚችለው በአካባቢው የሚገኘው የሠገራ ማስወጫ በባክቴሪያ የተበከለ ስለሆነ ነው፡፡ በመሆኑም
በምንፀዳዳበት ጊዜ የግል ንጽህናን ባለመጠበቅ (ባለመታጠብ)፣
በግብረሥጋ ግንኙነት ጊዜ እና
በተለያየ ምክንያት ሽንትን ለማስወገድ የሽንት ቱቦ በሚገባበት ወቅት ሊከሰት ይችላል፡፡

ሌለኛዉ መከሰቻ መንገድ ደግሞ በደም ስር የሚዘዋወሩ ባክቴሪያወች በተበከለዉ ደም አማካኝነት ኩላሊት ጋ ሲደርሱና ኢንፌክሽን ሲፈጥሩ ነዉ፡፡ እነዚህ ባክቴሪያዎች ኢንፌክሽን ለመፍጠር የሚያፋጥኑ ነገሮች የኩላሊት ጠጠር እና የፕሮስቴት እጢ ያሉት ሕመሞች ተፈጥሮአዊ የሆነውን የውሃ ሽንት አወጋገድን በማስተጓጎል ወይም በመከልከል ለባክሪቴያዎቹ መራባት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ለኢንፌክሽን ሊዳርጉ ይችላሉ፡፡ በደም ውስጥ የሚገኝ ባክቴሪያም ይህንን ኢንፌክሽን ሊያስከትል ይችላል፡፡
•---•---•

#ምልክቶቹ_ምንድን_ናቸው?
የውሃ ሽንት በምንሳወግድበት ጊዜ የማቃጠል ስሜት መሰማት፣
የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት፣
ከእንብርት በታች የሕመም ስሜት መሰማት፣
ደም የቀላቀለ ወይንም መጥፎ ጠረን ያለው ሽንት መኖር፣
ትኩሳትና ብርድ ብርድ የማለት ስሜት መሰማት፣
የማቅለሽለሽ ስሜትና ማስመለስ ናቸው

እነዚህ ምልክቶች በተለይ የስኳር ሕመምተኛ ፣ እርጉዝ ሴት ፣ የኩላሊት ሕመም ተጠቂ የሆኑ እና በእድሜ በገፉ ሰዎች ላይ ከተከሰቱ ጉዳታቸዉ የከፋ ስለሆነ ጊዜ ሳይሰጡ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ያስፈልጋል፡፡
•---•---•

#እንዴት_መከላከል_ይቻላል?
በብዛት ፈሳሽ መውሰድ ባክቴሪያ በሽንት ቧንቧ ውስጥ እንዳይቀመጥ በማድረግ ይከላከላል፣
ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በኋላ እና ከተፀዳዱ በኋላ የግል ንጽሕናን መጠበቅ እና
ምልክቶቹ ከተከሰቱ ፈጥነዉ አካባቢዎ በሚገኝ የህክምና ማዕከል መታከም ነዉ።

___
FEYA MEDIUM CLINIC
BALE -ROBE