Get Mystery Box with random crypto!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የምርጫ ቦርድን ሪፖርት ማዳመጥ ጀመረ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ | Fast mereja

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የምርጫ ቦርድን ሪፖርት ማዳመጥ ጀመረ

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬ ዉሎው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ቀድሞ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ያካሄዱትን ሕዝበ ውሳኔ አስመልክቶ ያቀረበውን ሪፖርት እያዳመጠ ይገኛል፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ ሲሆኑ፤ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ6ኛው የፓርላማ ዘመን በ1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ ነሐሴ 12 ቀን 2014  ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሕዝብ ውሳኔ አስፈጽሞ ሪፖርት እንዲያደርግ መታዘዙን አስታውሰዋል፡፡

በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሕዝብ ውሳኔውን በማስፈጸም ያዘጋጀው ሪፖርት እንደሆነም ምክትል ሰብሳቢው ገልጸዋል፡።

በቀጣይ በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት እንደሚደረግ አዲስ ማለዳ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።
ተዋሕዶ  ቤተክርስቲያን እንደሆነ ቢነገርም፤ ግብጻውያኑም የይገባኛል ጥያቄ በማንሳት ለዘመናት ዉጥረትን የሚያስተናግድ ቦታ ነዉ፡፡
አምባሳደር አለልኝ ቀደም ባለዉ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አባቶች በገዳሙ ዉስጥ እንዲጠለሉ አንድ የግብጽ መነኩሴ በማስጠጋታቸዉ ግብጾቹ የእኛነዉ የሚል እሳቤ እንዳደረባቸዉና ከዚያ በኋላ የይገባኛል ጥያቄ ማንሳት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡