Get Mystery Box with random crypto!

#Update ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ ጠየቀ። በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተ | Fast mereja

#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ ጠየቀ።

በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ፦

- ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመሰጠቷ፣

- በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ክልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና መላው #ሕዝበ_ትግራይን በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ፣

- ጦርነቱ ቁሞ በአገር አቀፍ ደረጃ እርቀ ሰላም ከወረደበት ጊዜ ጀምሮ ለደረሰው ጉዳት በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ በውሳኔው መሠረት በወቅቱ ማድረስ ባለመቻሏ፣ በዚሁም የተነሣ በቤተ ክርስቲያኗና በመላው ሕዝበ ትግራይ መካከል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።