Get Mystery Box with random crypto!

' ዝግጅቱ ተጠናቋል ' - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች | Fast mereja

" ዝግጅቱ ተጠናቋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዝግጅት #መጠናቀቁን አስታወቀ።

ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

በሚኒስቴሩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፤  " የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎችን እውቀትና ብቃት ለመለካት የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ዝግጅት ተጠናቋል " ብለዋል።

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የትክክለኛ ተፈታኞችን ቁጥር እንዲያጣራ በማድረግ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 95 ሺህ 755 እንዲሁም ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 74 ሺህ 776 ተማሪዎች ለፈተና  ይቀመጣሉ ሲሉ ገልጸዋል።

ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎቸ ዲግሪ እንደማይሰጣቸው እና የትምህርት ሚኒስቴር በሚያዘጋጀው የፈተና ጊዜ መሰረት ድጋሚ እንደሚፈተኑ አመልክተዋል።

ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ከተማሯቸው የትምህርት ዓይነቶች መካከል መሰረታዊ የሚባሉ ከ12 እስከ 17 የትምህርት ዓይነቶች ፈተና እንደሚወጣ ገልጸዋል፡፡

ለዚህም የፈተና ንድፍና የብቃት መመዘኛ መስፈርቶች መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ከግንቦት 15 ጀምሮ ለ211 የትምህርት ፕሮግራሞች የፈተና ጥያቄዎች በማውጣት ለፈተናው ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ እንዲሆን መደረጉን ተናግረዋል።

ፈተናው በኦንላየን የሚሰጥ በመሆኑም አስፈላጊ የቴሌኮም እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ዝግጁ ለማድረግ እየተሰራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

በሀገሪቱ ካሉ 325 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 161 እና ከመንግስት ደግሞ 44 ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እንደሚያስፈትኑ ጠቅሰዋል።

ዶ/ር እዮብ ፤ " ገበያው የሚፈልገውን ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የመውጫ ፈተናው ከ2015 ጀምሮ በሁሉም የትምህርት መስኮችና መርሐ ግብሮች መስጠት እንዲቻል ስራዎች ከአንድ ዓመት በላይ ሲሰሩ ቆይቷል " ሲሉ አስታውሰዋል።

#ኢዜአ